>
5:21 pm - Sunday July 20, 8098

ይህ ሰው ንጹሕ ሰው ነው ፍቱት.....!!!  (መምህር ታሪኩ አበራ)

ይህ ሰው ንጹሕ ሰው ነው ፍቱት…..!!! 
መምህር ታሪኩ አበራ

★ ዓቢይ አህመድ ስማ!  ኢትዮጵያን የሚያዋርደውንና ስሟን የሚጸየፈውን ነውረኛ ሰው ፓርላማ አስቀምጠህ አሜሪካዊ ዜግነቱን ንቆ ስለ ኢትዮጵያዊነት ክብር በጽናት የቆመውን እስክንድርን በእስር ማሰቃየትህ ልብህ በዘረኝነት ቆሻሻ የረከሰ ክፋና አስመሳይ ዘረኛ ሰው መሆንህን በግልጽ የሚያሳይ ነው።ፍትሕ አጓድለሃል ደሃ በድለሃል። አስር ጊዜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የምትለው ለሥልጣንህ ማራዘሚያ ሕዝብን ማደንዣ ተራ ብልጣብልጥነት  ነው እንጂ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ፍቅር በልብህ ኖሮ አይደለም።አስመሳይ ውሸታም ሰው ነህ።የእግዚአብሔር የቅጣት  ክንድ በአንተ ላይ ይከብዳል።እየፈጸምክ ባለው የሸፍጥ ፓለቲካ ታሪክና ትውልድ ሁሌም ሲወቅስህ ይኖራል።★
★ ዓቢይ አህመድ እስክንድር ነጋን ያሰረው በሃይማኖቱ ጠንካራ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኑና በፓለቲካ አቋሙም የመንግሥትን ስህተት በግልጽ የሚቃወም ጠንካራ ሰው በመሆኑ ብቻ ነው።★
★ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ሰው እንጂ ሌላ የክፋት አጀንዳ እንደሌለው ንጹሕ  ኢትዮጵያዊ ልብ ያለው ሰው ሁሉ የሚመሰክረው ሐቅ ነው።★
★ በዘመነ ህወሓት ዘጠኝ ዓመት በእስር ሲማቅቅ የነበረን ሰው ድጋሚ በግፈኛው ዓቢይ አህመድ አረመኔያዊ ውሳኔ  ከዓመት በላይ በእስር  እንዲሰቃይ ማድረግ ከግፍ ሁሉ የከፋ ግፍ ነውና እስክንድርን  ልቀቁት እርሱም እንደማንኛውም ሰው የግሉ ሕይወት ያለው በፍቅርና በናፍቆት የሚጨነቁለት ቤተሰብና ልጅ ያለው ሰው ነው።ዓቢይ አህመድ ከነቤተሰብህ በሞቀ ቤት ውስጥ  ተቀምጠህ በዚህ ሰው ላይ የምትፈጽመው ግፍ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ የከፋ በደልና የድፍረት ኃጢአት በመሆኑ ካንተ በፊት የነበሩ ግፈኛ ባለ ሥልጣናትን በአደባባይ አዋርዶ የቀጣ እግዚአብሔር አንተንም በከፋ ሁኔታ በውርደት ሞት እንደሚቀጣህ አትርሳ።እግዚአብሔር ፍትሐዊ ዳኛ እውነተኛም ንጉሥ ነውን
ለፍትሕ በጋራ እንቁም!!
Filed in: Amharic