>

"ወያኔ ለወረራ ሰራዊቱን ያስጠጋል የአገዛዙ ኮልኮሌዎች "በጀግና አቀባበል" የፎቶ ስነስርአት ተጠምደዋል...!!!" (አቻምየለህ ታምሩ)

ወያኔ ለወረራ ሰራዊቱን ያስጠጋል የአገዛዙ ኮልኮሌዎች “በጀግና አቀባበል” የፎቶ ስነስርአት ተጠምደዋል…!!!”
አቻምየለህ ታምሩ

አገዛዙና በየደረጃው የተኮለኮሉት ባላደራዎች ካለፈ ካገደመው ጋር ፎቶ በመነሳት፣ “የጀግና አቀባበል” በማድረግና በዓል በማክበር ላይ ተጠምደዋል። ውሉን የማይረሳው ናዚ ኦነግ ግን በወለጋና በሸዋ ከአማራ የጸዳ አካባቢ ለመፍጠር ከነሽመልስ አብዲሳ ጋር ጥምረት ፈጥሮ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራ ግፉዓንን ሲጨፈጨፍና የንጹሐንን ደም ሲያፈስ ይውላል።

ትልቁ ኮብራ ፋሽስት ወያኔም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ወራሪ አንበጣ ሠራዊቱን ወደ ተከዜ አስጠግቶ ጎንደርን ለመውረርና በምድር ላይ አለ የተባለን ሁሉ ግፍ ሊፈጽም እንዲሁም ከሱዳን ጋር ለመገናኘት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በልሳኖቹ ነግሮናል።
 በየቀኑ የምናየው በየከተማው እየተደረገ ያለው “የጀግና አቀባበል” እና በዓል ለማክበር የሚደረገው ሽርጉድ ግን የወረራ ስጋት ፈጽሞ እንደተወገደ፣ ካሁን በኋላ ጥይት የማይጮህበት ገነታዊ ምድር እንደተፈጠረና ዘላቂ ሰላም እንደሰፈነ እንጂ ፋሽስት ወያኔ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አረመኔያዊ ወራሪ አንበጣ ሠራዊቱን አሰማርቶ ጎንደርን ሊወርርና በምድር ላይ አለ የተባለን ሁሉ ግፍ ሊፈጽም ዝግጅቱን የጨረሰበት፤ በወለጋና በሸዋም በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግፉዓን የአማራ ሴቶችና ሕጻናት በናዚ ኦነግ በጅምላ እየተፈጁ የሚውሉበት ጊዜ  ላይ የምንገኝ አይመስልም።
Filed in: Amharic