>

ወያኔ ዳግም እንዲወረንና እንዲገለን ቀርቶ እንዲኖርስ  እንፈቅድለታለን ???? ( ፊልጶስ)

ወያኔ ዳግም እንዲወረንና እንዲገለን ቀርቶ እንዲኖርስ  እንፈቅድለታለን ????

 

ፊልጶስ


 

የማንኛውም መንግሥት”ሀሁ’—– የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ነው።   የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ያልቻል አገዛዝ  ስልጣኑ “የዛፍ ላይ እንቅልፍ ”  ብቻ ሳይሆን፤ ለዘመናት በደምና በአጥንት የተገነባን  የአገርና የህዝብን አንድንተን ያፈርሳል፤ ኑሮና ህይወትን ያመሰቃቅላል።

በአንጻሩ መሰረታዊ መብቱን ከአባራኩ የወጡ ገዥዎቹን ታግሎ  ማስከበር የማይችል ዜጋ፤  ህልውናውም አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው።

የአገር ልዋአላዊንትና  የህዝብ ህልውና ፈተና ላይ ሲወድቅ፣ ዜጎች  በየቀኑ እደከብት ሲታረዱና የመኖር ዋስትና ሲጠፋ፤  አስተዳድራለሁና እመራለሁ የሚለውንመንግስት ነኝ ባይ፤  እንዴትና ለምን? ብሎ የማይጠይቅና የማይሞግት፤ ብሎም  ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ የማይረዳና ለራሱ ህልውና የማይታገልና የማይቆም ህዝብመጨረሻው፤

ሌዎ ቶልስቶይ እንዳለው ”ወላጆች ልጆቻቸውን ይቀብራሉ፤ ወላጆች ደግሞ ያለ ጧሪ ይቀራሉ፤ አገርም ባለቤት አልባ ትሆናለች።—”

በኢትዮጵያ ምድር እየሆነ ያለውም  እውነታ ይኽው ነው። ታዲያ አሁን ያለው የህልውና ጥያቄ የመጣው በአንድ ጀምበር  ሳይሆን፤ በሂደት መሆኑን ወደ ኋላ መለስብለን፤  ከትላንቱ የመማራ ክህሎት ብናገኝ   እንደሚከተለው ለማስታወስ እንሞክ።

1/ ወያኔ ወደ መቀሌ ሲኮበልልና የጠ/ሚኒስተር አብይ አህመድ ስልጣኑን በያዙ ማግስት፤ የታለመው ሥር-ነቀል ለውጥና መሰረታዊ የሰውልጅ መብት ”በተረኝነት” ሲተካ፤ ህዝብ ተደራጅቶ መብቱን ማስከበር ባለመቻሉና የህዝብንም ጥያቄ ያነሱ ወደ እስር ቤት ሲወረውሩ ”እንዴትና ለምን?” በማለት ባለመጠየቃችንናባለመታገላችን ፤ የኦነጋዊ ብልጽግና በማን አልብኝነት  እንዲፈነጭ ተፈቀደለት።

ይህ ብቻ አይደልም ፤ የኦሮሚያ ብልጽግና ለኦነግ ”ኦነግ ሸኔ” የሚል የዳቦ ስም አው’ቶ፤ እስከ ዚች ሰዓት ድረስ ባንኮችን ሲያዘርፍ፣  ከተማን ሲያወድም፣  በመተከልናበወለጋ   የሰው ልጅ በማንነቱ ሲያሳርድ፣ ልጅ አገርድ ተማሪዎች ታፍነው የደረሱበት ሳይታወቅ ሲቀር፣ ተጨባጭ የሆነ ትግል አላካሄድንም።

እነ አቶ ጃዋር ሙሃመድ የአሜሪካን ፓስፖርት ይዘው  ” ሁለት መንግሥት አለ” እያሉ ህዝብን ሲያርዱና ሲያሳርዱ፤ ገዥው ኋይል በስልጣኑ እስኪመጡበት ድረስ  አይነኬመሆናቸው፤ በአጠቃላይ የሚፈጸመው ግፍ ”ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ”፤  እንደ ህዝብ   ገዥዎቻችንን ለማስቆምም ሆነ ተጠያቄዎቹን ለመጠየቅ ባለመቻላችን አሁንላለንበት  መከራ በቅተናል ።

2/ በጠቅላይ ሚኒስተሩ አንደበት፤

– ”ዱቄት አድርግናቸዋል!”፤

– ድሞ ሌላ ግዜ “መለማመጃችን  ናቸው!”፤

–  ” በሳተላይት እየተከታተልናች ነው፤ ግን ልናጠፋቸው ያልፈለግነው ምርኮኞችንና ጻናትን ስለያዙ ነው።”—-የተባለው የሰባዊ- ፍጡር ሁሉ ጠላትና አጥፊ የሆነውወያኔ፤  ”የፓለቲካ ውሳኔ” በሚል ሸምጋይ ቃል መከላከያ ከትግራይ  የወጣው፤ ”የትግራይ ህዝብ እርሶ እንዲበላና የጥሞና ግዜ ለመስጠት ነው።” ተብሎ ሲነገራን፤

–        ለምን? እንዴት ? ብለን እልጠየቅንም።

–        መከላከያ ከኋላው የህዝብ ደጀን እለው፤ ታዲያ በትግራይ ድንበር  መሽጎ እንዲት ሊከላከል አልቻለም? ብለን እልሞገትንም።

–        መከላከያ ከትግራይ ነቅሎ ሲወጣ ለወያኔ ትልልቅ መሳሪያዎችን እና  በክልሉ ውስጥ ለጦርነት ፍጆታ የሚውሉትን ሁሉ እንዱንም ሳይነካ፣ እንዴት ለጠላትጥላችሁ ተወጣልችሁ? ብሎ  መንግስት ነኝ የሚለውን አካል የጠየቀና እውነቱን ለማወቅ የሞከረ የለም።

ይልቁንም መንግስት ያድነናል! ይከላከልልናል! ዝም ጭጭ በሉ! እየተባለ፤ ወያኔ ከከተማ ከተማ እያከታተለ  እየተቆጣጠና እየዘረፈ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥተሰምቶ የማያውቀን ግፍና ሰቆቃ አየፈጸመ ሲቀጥል፤ ራስን አደራጅቶና በጎበዝ አለቃ እየተመሩ ፣ ጎን ለጎን የኦነጋዊ-ብልጽግና ካድሪዎችንና የጭቃ ሹሞችንእይስወገዱ፤ እንደመክላከል፤ ከተቻለም እንደማጥቃት፤  ገዥው ” ስትራተጅካዊ ማፈግፈግ ነው።”  የሚለውን የምስለኔዋችን ቅስቀሳ እያመን፤ በተግባር እየሆነላለው”የዝሆን ጀሮ ይስጠን” ብለን፤ ንጹሁ እርሶ አደር ወገናችን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለትሰማውንና ያልታየውን መከራ ተቀብሎ አስተናገደ፤ ሂሳብተወረረደብት።

3/ አሁንስ?????????

ጠ/ሚኒስተሩ  ወያኔ  የቤተ መንግሥታቸውን በር ማንኳኳት ሲጀምር ፤  ህዝባዊ ጥሪ አቅርበው ሁሉም ኢትዮጵያዊ  በጋራ   ለህልውናው እየተጋደለ ባለበትወቅት፣ ስሜን ወሎ ራያና ሰሜን ጎንደር ያሉ የድንበር ወረዳዎችና ቀብሌዎች ገና እንደ ተወረሩ፤ ግራ የሚያጋባ ብቻ ስይሆኑ፤

”በ’ርግጥም  መንግሥት ወያኔን ማጥፋት አይፈልግም! አሁንም  በወሎ፣ በሰሜን ሸዋና በአፋር የደረሰው ጥፋት በቂ ስላልሆነ ፤ ወያኔ እንደግና ተጠናክሮ የቀረውን ሂሳብ ያወረርድ፣ የወልቃይትንም ”ኮሪደር” ያስከፍት።” የሚያስብሉ ፤ ርስ-በርሳቸው የሚጣረዙ  መግለጫዎች የመንግሥት ባለስጣናት መሰጠት ጀመሩ።

ለትዝብት ብሎም የምንሰማውን ሳይሆን የምናየውን እንድናምን እና  ምን ዓይነት ገዥዎች እንዳሉን ከትላንቱ ብንማር  እስቲ መግልጫዎቹን እንመልከት

ከዚህ ላይ የመከላከያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ብርሃኑ ጁላ   በታህሳስ 12/2014 ባደርጉት የአንድ የመድረክ ንግግር ላይ፤ ” —-ብረት እንደጋለ ነው መደብደብ ያለበት፤ወያኔንም እስከመጨረሻው እናሳድደዋለን ።—-” ነበር ያሉት፤  ነበር ባይሰበር።

ወያኔ ግዜ እንዲያገኝና  ዳግም እንዲወር የሚያበረታታው  ግን ከጦር ግንባር የተመለሱት  የጠ/ ሚኒስተር የአብይ አህመድ መግለጫ ነው።  መግለጫው፤ ጦርነቱበድል መጠናቀቁን እና   በወያኔ ተይዘው የነበሩ ሁሉ  በመከላከያ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አብሰረው ፤ በትግሉ ለተሳተፋ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አሁን ያለው የጦርነቱ እውነታ፤

በመሃል አገር ከውጭ አገር በገቡ ተጋባዥ ኢትዮጵያዊን ጋር ”አስረሽ ምችው !” ቀጥሏል። አዲስ አበባ እስከ አልተነካችና በኦነጋዊ ብልጽግና ስር እስከሆነች ድረስ፤የሰሜኑ ጦርነት የህዝብ ስቃይ ለፓለቲካ ፍጆታ የሚውል  ሆኗል። ለትዝብት እንኳን በማሃል አገር  በስብሰባና በየምክንያቱ ለድግስ የሚወጣው ወጭ   በሚሊዮንለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች  መዋል በተገባው ነበር።

ወያኔ  ከመንግሥት በተሰጠው ፋታ ራሱን እንደገና እያደራጀና እያሰባሰብ ብቻ ሳይሆን፤ በተለይም በወልቃይት፣ በማይጠምሬ፣ በራያ- ሰቆጣና በተለያዮ ግንባሮችጦርነት ከፍቷል። ዳግም ወረራ ለማካሄድ ብሎም ወልቃይትን ለመቆጣጠርና ከሱዳን ጋር ለመገኛኘት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረግ መሆኑን የሚነገሩንራሳቸው የምንግስት ብዙሃን መገናኛዋች ናቸው።  ታዲያ በዚች ወሳኝ  ሰዓት ገዥዋቻችን ምን እያደረጋችሁ ነው? ብሎ መጠየቅ  ያለበት ህዝብና  በተለይም  የወያኔ የሂሳብ ማወራረጃ የሚሆነው  ወገን ነው።

ወያኔ ከአሁን በኃላ ድጋሜ ቢወር ምን ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ራሱ ይዘገንናል። ነገር ግን አሁንም   የመንግሥትን አቋም ማስለውጥ ከተቻለ ግዜ አለ፤ ግዜውግን ነገ ሳይሆን አሁን ነው።  መንግሥት ሃስቡን ለወጠም እለወጠም ፤  ህዝብ ራሱን አደራጅቶና በጎበዝ አለቃ በመደርቃጀት መታገል የግድ ይለዋል።መንግሥትም እንደ ትላንቱ”ስልታዊ ማፈግፈግ” ቢል ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና በኢትዮጵያ ህዝብ ደም እየተጫወት መሆኑ ተገንዝቦ፤  ከጎኑ ያለውን ህዝብይዞ፤ ወያኔን ብቻ ሳይሆን አመለካከቱንም እስከመጨረቻው ድረስ ማጥፋት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ   የመኖርና ያለምኖር ጥያቄ  ነው።

”ስትሄድ የመታህ እንቅፋት ስትመለስ ከመታህ ችግሩ ከአንተ ነው።” እንደሚባለው፤  ህዝብም ያለፈውን ስህተት በፍጹም መድግም የለበትም። የደረሰው ጥፋትናእልቂት ከበቂና  ከእዕምሮ በላይ ነውና ። ስለዚህ ሁላችንም  መዳኛ የሆነችውን ኢትዮጵያችን ለመታደግ ገዥዎቻችንን መጠበቅ የለብንም።’’ መንግሥት አለ’’ብለን የደረሰውን ሁሉ አይተናልና።

አንድ ጀርመናዊ የጥንት ፈላስፋ፤

መግደልም ሆነ መገደል አልፈልግም፤ ግን ከሁለቱ እንዱን ምረጥ ከተባልኩሳላወላውል እገላለሁ—” ነበር ያለው

እኛስ???——– ወያኔ ዳግም እንዲወረንና እንዲገለን ቀርቶ  እንዲኖርስ  እንፈቅድለታለን ???

ቅድመ  አያቶቻችን፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን እልፈቀዱላቸውም፤ እኛም እንፈቅድላቸውም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

E-mail: philiposmw@gmail.com

Filed in: Amharic