በምንም ዓይነት ሁኔታ አብረሃቸው የማትኖራቸው ሰዎች!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ይህን ወረቀት ልጽፍ የቻልኩት በባሮቲዩብ አሁን እየሰማሁት ባለው እጅግ ዘግናኝ ገጠመኝ ተመሥርቼ ነው፡፡ ይህን መሰል አማራ ላይ እየደረሰ ያለ አሳዛኝ ታሪክ መስማት ኅሊናን ያቆስላል፡፡ አእምሮን ያደማል፡፡
ነገሩ ባጭሩ እንዲህ ነው፡፡ አሳዛኝ ታሪኩ የደረሰው በአንድ የአማራ ቤተሰብ ላይ ነው፡፡ የሽመልስ አብዲሣና የአብይ አብይ የቤተ ሙከራ ፍጡራን የሆኑት ኦነግ ሸኔዎች በወለጋ የሚኖርን አንድ አማራ ወንድም ከህጋዊ እስር ቤት አውጥተው ወደ ጫካ ይወስዱታል፡፡ አማራውን ወደ እስር ቤት ያስገቡትና ከእስር ቤትም አውጥተው ለኦነግ ሸኔዎች ያስረከቡት ደግሞ የኦሮምያ ፖሊሶች ናቸው፡፡ በኦሮምያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ሁሉ – በነገራችን ላይ – ልዩነት የለውም፤ አንድ ነው፡፡ ከዘርና ከነገድ ሌላ ትናንሽ ሰዎችን አጥብቆ የሚያቆራኝ ኃይለኛ ሙጫ ጥራ ቢሉኝ አልጠራም፡፡ ይህ ሸኔና አጠቃላዩ የኦሮምያ መለዮ ለባሽ የሚታዘዘው ከአንድ ማዕከል ነው፡፡ ያም ማዕከል አራት ኪሎ ያለው የአቢይ አህመድ ግራኝ ፌዴራል ተብዬ መንግሥት ነው፡፡ የኦሮሞ ልዩ ኃይልና የኦሮሞ ፖሊስ ከነሸኔዎቹ የሚተዳደረውና እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ከዘመናዊ የጦር አልባሳት ጋር የሚቀርብለት የኦሮሞ ብልጽግና ከኢትዮጵያ የተራቆተ ካዝና ከሚዘርፈው ሀብትና ገንዘብ ነው፡፡ ብዙ ጅላጅል ሰው አቢይንና ሽመልስን ከሸኔዎች ለይቶ የመመልከት መጥፎ አባዜ ይታይበታል፡፡ አክራሪ ኦሮሞ ሁሉም አንድ ነው፡፡ ፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የፈለገውን ሥልጣን ይያዝ የበከተ አእምሮ ባለቤት ምን ጊዜም የበከተ አእምሮ ባለቤት ነው፡፡
ያ ከህጋዊ መሰል እስር ቤት እንዲወጣና ከአንድ ዘመዱ ጋር ለሸኔ እንዲተላለፍ የተደረገው አማራ ወንድሙ ለሸኔዎች ይደውላል፡፡ ከዚያም ብር አራት መቶ ሽህ ከሰጠ ወንድሙ እንደሚለቀቅ ይነግሩታል፡፡ እርሱ እንደሚለው እንደማይለቁትም እያወቀ ከርሱ እንዳይቀር በሚል ብሩን በሦስት ሽማግሌዎች አሲይዞ ይልካል፡፡ ነገር ግን ሽማግሌዎቹንም ጨምረው አምስቱንም አማሮች አረዷቸው፡፡ በታራጆቹ አማሮች ደምም “የአማራ ዕጣ እንደዚህ ነው!” የሚል ሀተታ አጋንንት ጽፈው በአማሮች አላገጡ፡፡ ይህን ዓይነት የድርድር ውጤት ታይቶ አያውቅም፡፡
እንግዲህ ልብ አድርጉ፡፡ ወያኔዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ ታዘቡ፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎችም ከወያኔዎች ባልተናነሰ ሁኔታ አማራ ላይ ምን እየፈጸሙ እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ እነዚህ በጥላቻ ያበዱ ወገኖች ሰማይ ምድር የማይችሉትን ወንጀልና ኃጢኣት እንዲሁም በሰው ልጆች ያለፈም ሆነ የአሁን ታሪክ ያልተከናወነ ነውር በአማራ ላይ እያደረጉ ነው፡፡ ከነዚህ ከሰይጣን ከከፉና በሰው አምሳል ከተፈጠሩ ጭራቆች ጋር በአንዲት ሀገር ይቅርና በጉርብትናም መኖር በፍጹም አይቻልም፡፡ ቂም በቀልና ጥላቻው እየታደሰ ከሚሄድ ሰው ጋር መኖር ከባድ ነው፡፡ መፍትሔ ግን አለው፡፡
የመጀመሪያው መፍትሔ ከነሱው የወንጀል ድርጊት የሚፈልቀውና በቅርቡ እንደሚታዘዝ የሚጠበቀው መለኮታዊ ፍርድ መሆኑ ይያዝልኝና ሁለተኛው መፍትሔ ደግሞ የአማራው መተባበርና በዘርና በጎሣ አለመከፋፈል ነው – ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ መባባል ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም ማለቴ ነው በእግረ መንገድ፡፡ የፋሲካው በግ በገናው በግ እየሳቀ (እንደማይታረድ በማመን ወይም የመታረጃው ቀን ሩቅ መስሎት) አሁን ላይ ደርሰናል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ማንም አማራ ዕርዱ እንደማይቀርለት በማመን ሊተባበርና ኅልውናን ሊያስቀጥል ይገባል – “እንዶድ በየዋህነቷ ውኃ ወሰዳት” ብሎ የሚተርት ነገድ ለራሱ ካላወቀና ከአስከፊ ተሞክሮው መማር ካልቻለ ማንም ሊያስተምረው አይችልም፡፡ “እዚያ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ተጣራ፤ እዚህ ማዶ ሆኖ አንድ ሰው ወይ አለው፤ ጎበዝ ተጠራጠር ይህ ነገር ለኛ ነው” እያለ የሚፎክርን ወገን ስለጠላቶቹ ትብብርና ሊያጠፉት መነሳት ለማስረዳት መሞከር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ አማራ በጠላት መከበቡን፣ አማራ በአራጆች ሤራ ከላይ እስከታች መተብተቡን፣ አማራ ኅልውናው አደጋ ውስጥ መግባቱን ለመረዳት በግድ ሁሉም አማራ ታርዶ ምድሪቱ አማራ-አልባ እስክትሆን መጠበቅ አይኖርብንም፡፡ ይህን ምሥኪን ሕዝብ ከዕልቂት ለመታደግ አስበው በመነሳት ገና ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ ከመግባታቸው በአራት ኪሎው የቀን ጅብ የተዋጡ እነብርጋዴየር ጄኔራል አሣምነው ጽጌንና እነዶክተር አምባቸው መኮንንን የመሰሉ የክፉ ቀን ደራሽ ልጆች ነበሩን፡፡ ነፍሳቸውን ይማር፡፡ የነሱን ፈለግ በመከተል አማራን ከሚወርድበት የጠላት ናዳ ለማዳን ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉ አሁንም ድረስ ብዙዎች አሉና ከነሱ ጀርባና ጎን ቆመን ታሪክ እንሥራ፡፡ እነዚህን ወገኖቻችንን ዐውሬው እንዳይሰለቅጥብን ዙሪያቸውን ከብበን እንጠብቃቸው፡፡
አማራን የሚያርዱት ወገኖች እየተጠቃቀሱ ሠይፋቸውን በመሳልና ጦራቸውን በመስበቅ አማራን እገባበት ገብተው እየፈጁት ናቸው፡፡ ለጊዜው የቀናቸው ይመስላል፡፡ በነሱ አማራን የመከፋፈል ዘዴም ይሁን በሌላ ምክንያት አብዛኛው አማራም ለሽ ብሎ ተኝቶላቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ አራጅም አሳራጅም በመጨረሻው እንጦርጦስ መውረዳቸው እውነት ቢሆንም ለጊዜው እየሰማነው ያለነው ነገር በሰውኛ አስተሳሰብ በእጅጉ ያንገበግባልና አማሮች ለራሳችሁ ስትሉ ተባበሩ፡፡ ተባብራችሁም ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት እስከ ወለጋ ነቀምትና ደምቢዶሎ፣ ከመቀሌ እስከ ግብጽ ሱዳን፣ ከወልቃይት እስከ ኮረምና አላማጣ …. የተደገሰላችሁን የሚሰነፍጥ ድግስ ለመቋቋም ዐመላችሁን በጉያ፣ ስንቃችሁን በጆንያ ይዛችሁ ቀበቷችሁንም ጠበቅ አድርጋችሁ ይህችን የፈተና ወቅት በኅብረት ታገሉና እለፏት፡፡ እስስቱ አቢቹ በወታደራዊ አቅምና የውጊያ ሞራል የበላይነት የታየበትን ጦርነት በነባር የአማራ ይዞታ ላይ አላማጣ ዋጃ አካባቢ ያስቆመው አለነገር አለመሆኑን ተረዱ፡፡ “አማራ የተቀማኸው ርስት የለህም” እያለህ ነው በሾርኒ ሳይሆን ፊት ለፊት፡፡ ወልቃይትን ለመስጠትም ወያኔ ወታደራዊ ሥልጠናዋን እስክትጨርስ እየጠበቃት መሆኑን ተገንዘቡ፤ ጠርቶ ይሰጣቸዋል፡፡ እስካሁን ወልቃይትን ዝም ያለው በሱዳን በኩል የሚገባ የአቢይን የሸኔ መንግሥት የሚገዳደር ነገር እንዳይፈጠር ፈርቶ እንጂ ለአማራ ወይንም ለጎንደር ሕዝብ አዝኖ እንዳይመስልህ፡፡
አማሮች ተባብራችሁ ከተነሳችሁ የማታሸንፉት ጠላት የለም፡፡ እንኳንስ ለራሳችሁ ለኢትዮጵያም ሆነ ለመላዋ አፍሪካ የሚበቃ እምቅ ኃይል አላችሁ፤ በሰው ሀብት ረገድም ሆነ በተፈጥሮ ፀጋ ከማንም አታንሱም፡፡ እርግጥ ነው አማሮች ችግራቸው አማራነታቸውን በኢትዮጵያ መለወጣቸው መሆኑ የታወቀ ቢሆንም አማራነትና ኢትዮጵያዊነትን እንደትግል ሥልት ይዞ ለተወሰነ ጊዜ ጎን ለጎን በማስኬድ ኅልውናን ማስጠበቅ ነውር አለመሆኑን ተረዱ፡፡ “ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለሁም” ማለቱ በራሱ መጥፎ ነው ባይባልም ብዙዎቻችንን እየጎዳን ያለው ግን ይሄን መሰሉ የይሉኝታ ገመድ መሆኑን እንገንዘብና በቅድሚያ ራስን ማዳን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ለእኛ ጥፋት የተሰለፉ ሌሎች “ወንድሞቻችን” ኢትዮጵያዊነትን ጨምሮ ሁሉንም የይሉኝታና ሀፍረት ክሮች በጣጥሰው፣ ከሃይማኖትም ሆነ ከባህልና ከሞራላዊ ዕሤቶች እንዲሁም ከአምቻና ጋብቻ መስተጋብራዊ አጥሮች ፍጹም አፈንግጠውና ከሰውነት ተራ ወጥተው የትም ሀገር ባልታዬ ጭካኔ እያደረሱብን ያለውን ሰቆቃ ሳንወድ በግዳችን እያለፍንበት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ማንም አይወስደብንም፤ ኢትዮጵያዊነትን ደግሞ ሰጪም ነሽም የለም፡፡ ስለሆነም በመላው የሀገራችን ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት የሰረጸው አማራነት ከየትውም ኢትዮጵያዊ ይትበሃል ጋር አይጣረስምና አማራነትን አትፈሩበት፡፡ እርግጥ ነው ካለፉት 31 ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፍቺ አልባ ዕንቆቅልሽ ውስጥ በመግባቱ የሀገሪቱን በትረ ሥልጣን የሚይዙት ወገኖች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የካዱ ብቻ ሣይሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከየት እንደተላኩ በውል የማይታወቁ መሆናቸው እያስጨነቀን መገኘቱ የማይሸሹት ነባራዊ እውነታ ነው፡፡ የአሁኑ አቢይ የሚባለው ሰውዬ ደግሞ ከሁሉም የባሰ አጭበርባሪና አስመሳይ በመሆኑ ድርጊቱና ንግግሩ የሰማይ የምድርን ርቀት ያህል ይለያያል፡፡ በዚያም ምክንያትና በጥቅማጥቅም እንዲሁም በፍርፋሪ ሥልጣን ዜጎችን እየከፋፈለና እየደለለ ኢትዮጵያ ሰው እንድታጣ የሚያደርገው ታላቅ ሤራ ቀላል አይደለም፡፡ የዚህ ሰውዬ ከይሲነት ከማንም ሰው ከይሲነት ጋር የሚወዳደር አይደለም – በለበጣ በሚስቅበት ጥርሱና ሞኛሞኞችን በሚሸነግልበት ምላሱ ሥር የመሸገው ጭካኔው ከነሂትለርና ሙሶሊኒ ጭካኔ ጋር እንኳን ሊወዳደር የማይችል እጅጉን ስሑል ነበልባላዊ ነው፡፡ የት ይደርሳሉ የተባሉ ቁርጠኛ ኢትዮጵያውያንን በአንደርባዊ የፕሮፓጋንዳ ቱማታው መሬት ላይ ዘርሮ መሣቂያ መሣለቂያ አድርጓቸዋል፡፡ ወለጋና ሰሜን ሸዋ ድረስ በዘለቀ የወያኔ የጥፋት ጀሌና የኦነግ ሸኔ ጎራዴ በየቀኑ የሚታረደው አማራ የሃቀኛ ዜና ምንጮች የዜና መክፈቻ ሆኖ ሳለ ሥልጣንና ጥቅም ያሳወራቸው ብዙ አማሮች ግን እውነቱ ሊገለጥላቸው አልቻለም፡፡ ይህ እውነት የሚታያቸው ምናልባት – አይሆንም እንጂ እንደዚያ ቢሆን ማለቴ ነው – አማራ ላይ የሚዘንበው የመከራ ዶፍ በጠላቶች የድል ስኬት እየተጠናቀቀ መጥቶ እነሱ ብቻ ሲቀሩና ሠይፉ በቀጥታ ወደነሱ አንገት ሲዞር ነው፡፡ ወያኔም ሆነ ኦነግ ሸኔ በሥራቸው ኮልኩለው አማራን ለማጥፋት የሚተባበሯቸውን አማሮች አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ ወይንም መባነን ሲጀምሩ (ከአሁኖቹ አሽከሮች የሚባንን ይኖራል ተብሎ ባይጠበቅም) ወዲያውኑ አንገታቸውን ይቀሏቸዋል፡፡ ወያኔና ኦህዲድ ውስጥ ለባርነት የተቀጠረ አማራ አገልግሎቱን እንደጨረሰ ልክ እንደ አሮጌ አህያ ለጅብ ነው የሚሰጠው፡፡ የኢሕዲኑ ታጋይ ሙሉዓለም ለምን እንደተገደለ፣ የዛሬን አያድርገውና ታጋይ ታምራት ላይ – አማራ ባይሆንም እንኳን – ለምን እንደታሰረና እንደተባረረ፣ እነአምባቸውና አሣምነው ለምን እንደተገደሉ …. ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ከቀጣሪ ጌታህ አስተሳሰብና ፍላጎት ትንሽ ዘመም ካልክ መጨረሻህ ጥይት ነው፡፡ በስለላ ድርጅቶችና ኦነግ/ሕወሓት/ኦህዲድን መሰል ሸፍጠኛ ድርጅቶች ውስጥ የሚያገለግል ሰው ምሥጢር ይዞ እንዳይወጣና መጋለጥን እንዳያስከትል ሲባል በነሱው ቋንቋ “ኢሊሚኔት” ይደረጋል፡፡
እንደመንፈሣዊ ሣይሆን እንደሥጋ ለባሽ ሰው የኢትዮጵያን ችግሮችና መፍትሔዎች ሳስብ ጭንቅ ይለኛል፤ በእጅጉም ይደክመኝና ቁና ቁና መተንፈስ እጀምራለሁ፡፡ የወያኔን ጭካኔ፣ የኦነግን ዐረመኔነት፣ የኦህዲድን ጭራቅነት፣ የአቢይን ራስ ወዳድና እስስታዊ ተፈጥሮ፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬው በጥንታዊቷ ኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ላይ ያለውን አሉታዊ አመለካከት፣ … ሲታይ ኢትዮጵያ ከሙታን መሀል ተነስታ እንዴት እንደሀገር ልትቆም እንደምትችል ማሰቡ ይጨንቃል፡፡ በልጅነቴ የማውቃት ኢትዮጵያ፣ በወጣትነቴ የማውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት ተመልሶ እንደማየው ሳሰላስል አሉታዊ ጎኑ እየበረታብኝ በእጅጉ እጨነቃለሁ፡፡ ያን መልካም ዘመን ሊያመጡ የሚችሉ መልካም እረኞችን ከየት እንደምናገኝ ሳወጣ ሳወርድ ድክም ይለኛል፤ ሰውነቴ ይዝላል፡፡ መቀሌ ላይ ለተሰበሰበ የትግራይ ወገናችን “እንኳዕ ካባኹም ተፈጢርና” (እንኳን ከእናንተ ተፈጠርን!” የሚል መሪ ባየንበት ቤተ መንግሥት አቢይን የመሰለ በዘረኝነትና በገዳይነት ተወዳዳሪ የሌለው የኦሮሞ አክራሪ ተቀምጦበት በዕውር ድምብር እየተመራን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማሰብ ከህልም ያለፈ ቅዠት ወይም ቅብዥር መሆኑን ደግሞ ከጥቂቶች በስተቀር የገባው የለም፡፡ በትግርኛና በኦሮምኛ ሲያወሩ ትግርኛና ኦሮምኛ የሚያውቅ የሌላ ነገድ አባል ያለ በማይመስላቸውና የወከሉትን ጎሣ ያስደሰቱ መስሏቸው እንዳሻቸው የሚዘባርቁ ትናንሽ ሰዎች የሚመሯት ሀገር ደግሞ የትም እንደማትደርስ በግልጽ እየታዘብን ነው – “አማራን መንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሲለምን ማየት ደስ ይለኛል” ያለውን የመለስን ንግግር ሳንረሳ እነዚህ በሥልጣን ጥማት ያበዱ የአሁን ተረኞች ደግሞ ኤሊቶቻቸውን በጠፍ ጨረቃ ሰብስበው “ኦሮሞ ዝኆን ነው፤ ከአሁን በኋላ ዝኆን ያልፈቀደለት ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን መምራት አይችልም፤ አማራን ከነቋንቋው ለማጥፋት በቻልነው ሁሉ እየሠራንበት ስለሆነ ጥቂት ታገሱን ….” ማለታቸውን መርሣት አይገባም፤ ጊዜው እያረርንና እየተማረርን ብዙ የምንማርበት ነው፡፡
ከነዚህ ሁለት ጽንፈኛ የሀገር አውዳሚዎች ጋር ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት አብሮ ሊኖር እንደሚችል ሳስበው ታዲያ ማይግራይን የሚባለው ራስ ምታት የተጣባኝ ያህል ክፉኛ ራሴን ያመኛል፡፡ በሚሊዮኖች የሚገመት አማራ በትሪሊዮን ከሚገመት ሀብት ንብረቱ ጋር እየወደመና ሊደርስብን ቀርቶ ልንሰማው የሚዘገንን ዕኩይ ድርጊት በወገናችን ላይ እየደረሰ ባለበት ቅጽበት እዚህ አዲስ አበባ ላይ በደስታ ጮቤ የሚረግጥ መሪ ስታይ ካልጨነቀህ እንግዲህ ሰው መሆንህን ተጠራጠር፡፡ የአማራን ነፍስ እንደቁጫጭ “ነፍስ” የሚቆጥር፣ የአማራን ውድመት እንደብሥራት ቆጥሮ በሃሤት የሚረካ፣ ወለጋ ውስጥ ባደራጃቸው ሸኔዎቹ የአማራ አንገት ሲቆራረጥ በደስታ ሲቃ ተይዞ በገነባቸው የመናፈሻ ሥፍራዎች የደላቸው ዲያስፖራዎችን የሚያስጎበኝ እስፊኒክሳዊ መሪ ይዘህ “የኢትዮጵያ ትንሣኤ አሁን ጀመረ” ብትል ከሕወሓት ማሕጸን ዶክተር ኃይሉ አርአያን፣ ከኦነግ ማሕጻን ደግሞ ኮሎኔል አብዲሣ አጋን የምትጠብቅ ገልቱ ነህ፡፡ ማንም የሚወልደው መሰሉን ነው – መሰራረቅ እስከሌለ ድረስ፡፡ ስለሆነም ሻዕቢያ የወለደው ሕወሓት ሻዕቢያን እንጂ ሌላ ሊመስል አይችልም፡፡ ሕወሓት የወለዳቸው ብአዴንና ኦነግ/ኦህዲድ ሕወሓትን እንጂ ሌላ የመምሰል ባሕርያዊም ይሁን ተፈጥሯዊ ጠባይ እንዲኖራቸው አይጠበቅም፤ አይኖራቸውምም፡፡ እናም ከአቢይ አህመድ የኢትዮጵያን ትንሣኤ መጠበቅ የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብላ ቀኑን ሙሉ ስትንከራተት እንደዋለችው ሞኝ ቀበሮ መሆን ነው፡፡ አቢይን ማፍቀርና መደገፍ መብት ነው፤ ዕኩይ ሥራውን አለመቃወም ግን እርሱን መሆን ነው፡፡ ፍቅር ዕውር መሆኑ ብዙውን ጊዜ ቢነገርም ዐረመኔ ገዳይን የሚያስፈቅር መግነጢሳዊ ኃይል ሲፈጠር ግን በሰው ልጆች የተዛባ ተፈጥሮ መሳቀቅና በሰዎች የአስተሳሰብ ልዩነት መገረም የተገባ ነው፡፡
ብዙ የሚገርም ነገር አለ – ለአብነት ያህል፡- በሀገሩ መራቅና በሥራው እርካታ ማጣት የተነሣ አንዲት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ሀገር የሚጎርፈው ዲያስፖራ የሀገሩን ተጨባጭ ሁኔታ ለምን መረዳት እንዳቃተው ይገርመኛል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም – በነዚህ ወገኖቻችን ወደ ሀገር መምጣት ሰበብ፣ ጫማ ጠርገውና ትናንሽ ነገሮችን ሸጠው በሚያገኙት ትንሽ ገንዘብ የዕለት ጉርሳቸውን የሚሸፍኑ በብዙ ሽዎች የሚገመቱ ዜጎቻችን እንደቆሻሻ ተቆጥረው ከከተማ እንዲወገዱ መደረጋቸው የእነዚህን ዲያስፖራዎች ጦስና የመንግሥት ተብዬውን ድንቁርና የሚያሳይ በመሆኑ – ይህም ይገርመኛል፡፡ ሰው ማሰብ ሲያቆም ካላስገረመ ምን ሊያስገርም ኖሯል ዱሮስ፡፡ የጭፍግ ትያትር ሀገር፡፡
አዲስ ተዓምር ካልተፈጠረ በስተቀር ወያኔዎች ከአማራ ጋር ሊኖሩ አይችሉም – ይምረርህ እንጂ እውነቱ ይሄው ነው፡፡ ዓለም በቃኝ ያሉ መነኮሳትን ጨምሮ የ10 እና 12 ዓመት ሕጻናትን በሀሽሽ እያደነዘዙ ለአሥርና አሥራ አምስት መድፈርና ያም አላረካቸው ብሎ በጥይት ገድሎ መዝናናት ከሰው ለሰው አይደለም ከሰይጣን ለሰውም አይጠበቅም፡፡ ወያኔዎች በአማራ ላይ ከጥንት ጀምሮ የሠሩትን ግፍና በደል ስናይ ከነሱ ጋር በጉርብትናም መኖር በእጅጉ አስቸጋሪ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ከነሱ ጋር ለመኖር በቅድሚያ እነሱ ሰው እንዲሆኑ ከሰውነት ባሕርያት የጎደሏቸውን ማሟላት ያስፈልጋል – ያም ከተቻለ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አክራሪ ኦሮሞዎች ጋር አብሮ ለመኖር እነሱንም ሰው እንዲሆኑ ማስቻል ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከነዚህ ከሁለቱ ጋር ከመኖር ከለዬላቸው ጅቦችና ዐውሬዎች ጋር ተስማምቶ በፍቅር መኖር ይቀላል፡፡ አንድን አንበሣ አልምዶ ከርሱ ጋር በሰላም መኖር ሲቻል ከአንድ ወያኔ ወይም ወንድሙ አቢይ-ሸኔ ጋር ግን አንድ ሽህ ዓመትም አብረህ ብትኖር ክፋቱንና ኦነግ/ወያኔያዊ አማራ-ጠል ጠባዩን አይተውም፡፡ መረገም ነው፡፡ የሁለትዮሽ እርግማን – አማራም አማራ ጠሎችም እኩል የተረገሙ ይመስለኛል፡፡
ዘወትር የምለውን አሁንም ልደገምና ልሰናበት፡፡ መጪው ጊዜ ብሩኅ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ አሁን ግን ጨለማው ጥቅጥቅ ያለ በመሆኑ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች መጥፋታቸው ባይቀርም ሟች ይዞ መሞቱ ያለና የነበረ ነውና ለጥቂት ጊዜ መቸገራችን የሚጠበቅ ነው፡፡ ለማንኛውም በርትተን እንጸልይ፤ ከማንም ምንም አንጠብቅ፡፡ የነፃነታችንን ዋጋ የምንከፍለው እኛው ራሳችን እንጂ በሌሎች ተጋድሎና የሕይወትም ሆነ የገንዘብ መስዋዕትነት እንዲሆን አንጠብቅ፡፡ ሁላችንም በተቻለን ሁሉ ለማይቀረው ትንሣኤያችን እንረባረብ፡፡ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፤ ወደጥንታዊ ክብሯም ትመለሳለች፡፡ አሁን ወዲያና ወዲህ ዊኒጥ ዊኒጥ የሚሉትና ሀበሻን ያጠፉ የመሰላቸው ወገኖች ነገ የሚገቡበትን እንደሚያጡ ቀድመን እናውቃለን፡፡ ከነሱ ጋር የሚያሸረግዱትም ሁሉ ንስሃ ካልገቡና ከተዘፈቁበት የጥፋት ባሕር ወጥተው በቶሎ ካልተመለሱ ዱሮውንም እንደምንለው ሁሉ አሁንም ደግመን ደጋግመን እንላለን ዕጣቸው የጌቶቻቸውን እንደሚመሳሰል እነሱም፣ ጌቶቻቸውና ታዛቢዎችም ይረዱት፡፡ የተነፋን ኳስ ትንሽዬ እሾህ ታስተነፍሰዋለች – ያበጠ ትዕቢትንም ከየት መጣነቱ ያልታወቀ ትንሽ ሞገድ ደብዛውን ያጠፋውና እስከወዲያኛው ያስተነፍሰዋል፡፡ ትዕቢተኛው ጎልያድ በትንሹ እረኛ በዳዊት ወንጭፍ ተዋርዶ ወድቋል፡፡ ምን ሩቅ አስኬደኝ – በወታደራዊ ዝግጅቱ ምሥራቅ አፍሪካን ያሰጋ ነበር የተባለው የደርግ መንግሥት ሰባራ ክላሽ አንስተው የበረሃ ትግል በጀመሩ ሰባት ወያኔዎች ጦስ ብትንትኑ ወጥቷል፤ እነሱም በተራው ከዚህ መጣ ሊባል በማይችል ወጀብ ዋጋቸውን አግኝተዋል – እያገኙም ነው፡፡ አትፍረድ ነው፡፡ ፍርድ ደግ አይቀርም፡፡ ሽህ ጊዜ ብትሸሸው የሠፈርከውን አታጣም፡፡ እንዲህ ነበር- እንዲህም ይሆናል፡፡ ብቻ … ጠብቁ፤ እንጠብቅ፡፡ ሰላም ለሀገራችን፡፡