>
5:26 pm - Saturday September 17, 9346

"በምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈናቃዮች ሰቆቃ...!!!" DW

“በምስራቅ ወለጋ ዞን የተፈናቃዮች ሰቆቃ…!!!”

DW

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙና ጉቱ ጊዳ ወረዳ በነበሩት አለመረጋጋቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ለረዥም ጊዜ በነበረው መንገድ መዘጋትና የፀጥታ ችግር ምክንያት ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በኪራሙ ገጠራማ ስፍራዎች ተፈናቅለው በወረዳው ከተማ ከ50ሺ በላይ ተፈናቃዩች እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በስፍራው በቂ ጸጥታ ሐይል እንዲመደብላቸውም ጠይቀዋል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ፣ጉቱ ጊዳ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ በተለያዪ ጊዜያት በደረሰባቸው ጥቃቶች ተፈናቅለው በየወረዳው ከተማ የተጠለሉ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጠቸውን ተናገሩ፡፡  በኪራሙ ወረዳ 50ሺ የሚደርሱ ተፈናቃዩች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ በተለይም ሰብአዊ ዕርዳታ እንዲደርሳቸውም ጠይቀዋል፡፡  የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳር አቶ አለማየሁ ተስፋ ለዲዳቢሊው በሰጡት ማብራሪያ በዞናቸው ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሰሩ የሸኔ ቡድንና ጽንፈኛ ኃይሎች ያሏቸው ባደረሱት ጥቃት ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በዲጋ፣ኪራሙ፣ጉቱ ጊዳ እና ሐሮ ሊሙ ወረዳዎች የፌደራል መንግስት እና የዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር እርዳታ በመስጠት ላይ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡ በዞኑ መንግስት በየጊዜው እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነም አክለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙና ጉቱ ጊዳ በሚባል ስፍራዎች በነበሩት አለመረጋጋቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ለረዥም ጊዜ በነበረው መንገድ መዘጋትና የፀጥታ ችግር ምክንያት ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡ በኪራሙ ገጠራማ ስፍራዎች ተፈናቅለው በወረዳው ከተማ ከ50ሺ በላይ ተፈናቃዩች እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ በስፍራው በቂ ጸጥታ ሐይል እንዲመደብላቸውና ሰብእዊ እርዳታም እንደርሳቸውም ጠይቀዋል፡፡ በጉቱ ጊዳና ወረዳም እንደዚሁ ከቀአቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
በሐሮ ሊሙ፣ኪራሙና ዲጋ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት በደረሰ ጥቃት ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበረ የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር አመልክቷል፡፡ በዞኑ የተለያዩ ስፋራዎች የጁንታ ተላላኪ ያሏቸው ቡድኖች በነዋሪው ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንና ማፈናቀላቸውን አብራርተዋል፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ በጉቱ ጊዳ ወረዳ 30ሺ ዜጎች ተፈናቅለው እንደበረ ገልጸው ከተፈናቀሉበት 11 ቀበሌዎች ውስጥ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡  የጸጥታ ሐይሉም በተቀናጀ መልኩ እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ መነስቡ ወረዳ መንዲ ከተማ የተጠለሉ ዜጎችም ለወራት እርዳታ እንዳልመጣላቸው አመልክተዋል፡፡ ሴዳል ከተባለ  የካመሺ ዞን ወረዳ ከስምንት ወራት በፊት ተፈናቅለው በምእራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ ተጠልለው የሚገኙት አቶ ምትኩ ምልከሳ  ሰብአዊ ዕርዳታ ከተቋረጠ ሶስት ወራት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  በመንዲ የተጠለሉ ዜጎች ያቀረቡትን ቅሬታ አስመልክቶ ከምዕራብ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር መረጃ ለማግኘት በስልክ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት የኢትየጵያ ቅርንጫፍ(ኦቻ) በነሐሰ ወር ባወጣው ዘገባው ነበር በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ከ51000 በላይ ተፈናቃዩች ተጠልለው እንደሚገኙ የገለጸው፡፡

Filed in: Amharic