>

"እየተራመድኩ ገብቼ አንካሳ ሆኜ እንዳልወጣ እሰጋለሁ"  (አስካለ ደምሌ )

“እየተራመድኩ ገብቼ አንካሳ ሆኜ እንዳልወጣ እሰጋለሁ” 

አስካለ ደምሌ 
ባልደራስ 
 
በእስረኛዋ ላይ የተፈፀመውን የድብደባ ሙከራ ፖሊስ እንዲያጣራ ፍርድ ቤት አዘዘ…!

በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የሴቶች አደረጃጀት ዘርፍ ሓላፊዋ ወ/ሪት አስካለ ደምሌ በቃሊቲ ወህኒ ቤት የፖሊስ አባል የድብደባ ሙከራ ተደርጎባቸዋል።
“እየተራመድኩ ገብቼ አንካሳ ሆኘ እንዳልወጣ እሰጋለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ማክሰኞ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ጉዳዩን ተመልክቷል።
ወህኒ ቤቱ በተወካዩ በኩል ችሎት ቀርቦ ድርጊቱን የካደ ሲሆን ጉዳዩ በፖሊስ እንዲጣራም ፍርድ ቤቱ አሳስቧል።
በተጨማሪም ወ/ሪት አስካለ ጉዳዩን ለዐቃቤ ሕግ እንዲያመለክቱ መክሯል።
የእስር ቤቱ ፖሊሶችና እስረኞች መብቶቻቸውን ተከባብረው በሰላም እንዲኖሩም ችሎቱ ምክርና ተግሳፅ ሰጥቷል።
ሆኖም የኅሊና እስረኞች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እና ወከባ እንዲፈፀም ከወህኒ ቤቱ አለቆች ግፊት እየተደረገ መሆኑን ውስጣዊ የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
ከዚህ በፊት አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ውስጥ መደብደባቸው እና ወህኒ ቤቱ ድርጊቱን መካዱ ይታወሳል።
በተመሳሳይ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ህክምና ሲከለከሉ የቃሊቲም ሆነ የቂሊንጦ ወህኒ ቤቶች ከምርመራ ውጤቱ በተቃራኒ የኅሊና እስረኛው ሕይዎት አደጋ ላይ የሚጥል መወሰናቸው አይዘነጋም።
Filed in: Amharic