የምናምንቴ ልጅ ጭንጋፍ!

ከይኄይስ እውነቱ

 

ሕወሓት የተባለ ምናምንቴ ቡድን በኢትዮጵያ ምድር ጐሠኛነትን ሲተክል አብሮ የተከለብን ጭንጋፍ ነቀርሳ ብአዴንነው፡፡ የምናምንቴ ልጅ ጭንጋፍ ከመሆን ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ይህ የወያኔ ትግሬ የእጅ ሥራ የኢትዮጵያን ፍዳ መከራ እየራዘመ ነው፡፡ ስለዚህውዳቂ ፍጡርብዙ ተብሏል፡፡ ብአዴን በሚባለው በሽታ የተለከፈ ሰው መዳኛ ያለው አይመስልም፡፡ ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ የሚሆነን በማንነቱፍናፍንታምጠባይ ይዞ የሚገኘው አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለ ጉድ ነው፡፡ ምን ዓይነት መርገም ቢሆን ነው ይህ የብአዴን አውራ በኢትዮጵያ ባጠቃላይ÷ በዐምሐራ ሕዝብ በተለይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ደማችንን እንዲመጥ የምንፈቅደው? ዐለማወቅ ነው ወይስ ሞኝነት? ይህ አንዳርጋቸው የተባለ የርጉም ዐቢይ መሼጦን ዓላማ ሳይገባን ቀርቶ ነው? ግልገል መሼጦዎቹ እነ ዘመነዐሥረስወዘተ በፋኖዎቻችን ውስጥ የመሸጉ በዓላማ የአንዳርጋቸው የመንፈስ ግርፎች መሆናቸው አይገባችሁም?

Screenshot

ሌላው ሰሞኑን እየሰማንው ያለ ‹‹ፅምዶ›› የሚል ማጭበርበሪያ ነው፡፡ አንዳርጋቸውየምሐራ ነገድ ወኪልሆኖ በሻእቢያ የተሰየመበት ጉባኤ፡፡ ወገን እባካችሁ በሚሰጠን አጀንዳ ሁሉ አትነዱ፡፡ ከሚነፍሰው ጋር አብረን አንንፈስ፡፡ ‹ፅምዶበሚል ሐሳብ ዙሪያ የተኰለኰለው ስብስብ ለኢትዮጵያ የሚተርፍ ቁምነገር ቢኖረው ፀረ ኢትዮጵያዊውን አንዳርጋቸው የስብስቡ ዕድምተኛ አያደርገውም ነበር፡፡ ኧረ እባካችሁ እኛ ኢትዮጵያውያን በተለይም የዐምሐራው ነገድ በዝርወት የምንኖረውም ሆነ በመላው ኢትዮጵያ የምንገኘው በርካታ የቤት ሥራዎች አሉብን፡፡ ከዓላማችንና ያንን ለማሳካት ከሚጠበቅን የተግባር እንቅስቃሴዎች ለሚያናጥቡን ማናቸውም ኃይሎችና እንቶፈንቶዎ ልቡናችንንም ሆነ ዦሮአችንንም ልንሰጥ አይገባም፡፡ በቀደም በወንድማችን አበበ በለው አዲስ ድምፅ ሚዲያፅምዶስለተባለው ሐሳብና ርጉም ዐቢይምርጫብሎ ስለሰየመው ፌዝለመነጋገር ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የሚባሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ጋብዞ ነበር፡፡ እኚህን ከሶማሌ ነገድ የበቀሉ ኢትዮጵያዊ በተለያየጊዜ በሚሰጡት ቃለ መጠይቅ ሐሳባቸውን በመጠኑም ቢሆን ለማዳመጥ ዕድሉን አግኝቼአለሁ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንደሚያውቅእንደሚከታተልና ትንተና እንደሚሰጥ ባለሙያ የብአዴን ቁንጮ የሆነውን አንዳርጋቸውን ያጡታል ብዬ አላስብም፡፡ የገረመኝና ያሳዘነኝ  ‹ፅምዶበሚለው ሐሳብ ባንድ ኤርትራዊ ተጋብዘው የስብሰባው ተከፋይ መሆናቸው አይደለም፡፡ ይኸው የጋበዛቸው ኤርትራዊ አንዳርጋቸው የዐምሐራ ነገድ ወኪል ሆኖ በስብሰባው እንደተገኘ ሲናገር በቦታው ነበሩ፡፡ ወንድማችን አበበ በዚህ ረገድ ላቀረበልዎት ቀጥተኛ ጥያቄ የሰጡት መልስ ማድበስበስና አለማስተዋል እንደሆነ ነው፡፡ ወንድማችንም በአክብሮት ታዝብዎት እንዳለፈ እገምታለሁ፡፡ አንድምሁርከተባሉ ሰው የሰጡት መልስ የሚታመን ነው? በጭራሽ፡፡ ፕሮፌሰር በዚህ ንግግርዎለመሆኑ ራስዎን ያዳምጣሉ›?

ሐሳቤን ደጋግሜ በምናገረው ማሳሰቢያ እቋጫለሁ፡፡ የዐምሐራ ፋኖዎች በተለይም በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ያላችሁ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ህልውናው ፈተና ውስጥ ያለውን የዐምሐራ ሕዝብ እና የሀገራችንን ኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እያሰባችሁየምትከፍሉት መሥዋዕትነት ፍሬ እንዲያፈራ የሕወሓት ጭንጋፍ የሆነውን ብአዴን ያላንዳች መወላወልና ምሕረት በቅድሚያ ከውስጣችሁ ቀጥሎም ከምትቆጣጠሩት የአስተዳደር መዋቅር በሙሉ ማስወገድ ይኖርባችኋል፡፡ የብአዴንዘመድወገንወዳጅየጎጥየአካባቢሰውካህንሼክ ወዘተ.› የሚባል የለም፡፡  በመወላወላችሁ ያሳለፋችሁት ጊዜ እጅግ አስከፍሏችኋል፡፡ ዓላማን ከግብ ለማድረስ ሊቃውንት እንደሚሉት ጥብዐት (ለበጎ መጨከን) ያስፈልጋል፡፡ ጥብዐትን ያዙና በወታደራዊውም ሆነ በፖለቲካው የሚበጇችሁንየምታከበሩአቸውንና የምትታዘዙአቸውን አመራሮች መርጣችሁ በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ግዴታችሁ ነው፡፡ ዝርው ሆኖ የተሳካ ድል የተገኘ ነፃነት የለም፡፡ ምናምንቴ የሆነው የርጉም ዐቢይ አገዛዝ ህልውና የቆመው በሠራዊቱ ብዛትና ጥንካሬ ሳይሆን በእኛ ድክመት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እኛ ብአዴንን አዝለን በማስታመማችንና ሕዝብ ግብር የሚከፍልበትን መደበኛ ሚዲያዎች ተቆጣጥሮ ለቅጥፈቱ እንዲጠቀምበት ስለፈቀድንበወሬ ስለምንፈታእንደ ሕዝብ ባለን ፍርሀትአለመተማመንና የባርነት መንፈስበሆድና ጊዜያዊ ጥቅም ተገዝተን አገር ለሚያጠፉ÷ ሕዝብ ለሚጨፈጭፉ መሼጦ መሆንን ስለመረጥን የባርነት ዘመናችን አለቅጥ ረዝሟል፡፡ በሰበብነት ጣታችንን የምንቀስርባቸው በርካቶች ቢኖሩም ዕቅጩን ለመናገር  ግን እንደ ሕዝብም ከተበላሸን የቆየን ይመስለኛል፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል ብንማትር እንደኛ ከግማሽ ምእት በላይ በድንዛዜ ውስጥ የቆየ የምናገኝ አይመስለኝም፡፡ ግፍ በቃ! ጭቆና በቃ! ባርነት በቃ! ብለን ክቡር እንደሆነ እንደ እግዚአብሔር ፍጡር የምንኖርበት ጊዜ ቀጠሮአችን መቼ ይሆን?

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.