>
5:08 pm - Friday February 22, 0926

ከወርቅ ዝርፊያው ጀርባ የተደበቀ የኦሮሞ እናቶች ስቃይና ሰቆቃ!?! (ብርሀነ መስቀል አበበ)

የቢቢሲ የኦሮሚኛ ክፍል ለገደንቢ የወርቅ ዝርፊያና በዘራፊዎቹ መርዝ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ወንጀል፣እልቂትና ጥፋት አይቼ መጨረስ አልቻልኩ።
 አንድ ነገር ግን ግልፅ ነው። የኦሮሞ ህዝብ አገር የለውም። የኦሮሞ ህዝብ መሪ የለውም። የኦሮሞ ህዝብ መንግስት የለውም። የኦሮሞ ህዝብ በቁሙ የሞተ ህዝብ ነው። ይህን ወንጀል ለማስቆም ውል ሰርዙ፣ ውል አይታደስ የሚል ቀልድ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም።
ስለዚህ በዚህ ጉዳይና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን እርምጃዎችና አቋሞች መውሰድ ይገባል፣
1ኛ፣ የኦሮሞ ህዝብ የአገሩ ባለቤት ሳይሆንና በህይወት ሳይኖር የንብረቱ ባለቤት መሆን አይችልም። ህዝቡ የአገሩ ባለቤት ለመሆንና በህይወት ለመኖር የጀመረውን  ትግል አጠናክሮ  መቀጠል።  የልማት ወሬ የሚወራው በህይወት ስትኖርና አገር ሲኖሪህ ነው።
 2ኛ፣ ባለፉት 27 ዓመታት የተዘረፈው በብዙ መቶ ቢልዮኖች ብር የሚገመት ወርቅ ለማን ጥቅም እንደዋለና የት እንደገባ(የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ምንም እንዳላገኘ ይታወቃል) የክልሉ ፕሬዚዳንትና የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተር ለህዝቡ ቀርበው በአስቸኳይ  እንዲያብራሩ መጠየቅ።
3ኛ፣  የኦሮሞ ህዝብ አካለስኩል እየወለደ፣እየሞተ፣ከብቱና ሃብቱ ሁሉ እያለቀ፣ መጃጃሉን ትቶ የኦሮሞ ህይወት  ከሌቦቹና  ከዘራፊዎቹ  በሌብነት ከተገኘ ንብረት እንደሚበልጥ በተግባር ማረጋገጥ አለበት። የሰው ህይወትና የሰው ልጆች መብት ከንብረት ባለቤትነት መብት ይበልጣል።  በዚህም መሠረት ለኦሮሞ ህዝብ ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው  የነፈሰ ገዳዮቹ ንብረት ተይዞ በካሳ መክፈልና ሙሉ በሙሉ ተወርሶ ሌቦቹን ከኦሮሚያ ማባረርና ቀንደኞቹን በወንጀል ከሶ ለፍርድ ማቅረብ።   ያ ካልሆነ የዘረፋውንና በወንጀል የኦሮሞ ህይወት አጥፍቶ የተገኘውን  ንብረት መሉ በሙሉ ማውደም።
4ኛ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ  ኦሮሞ ህዝብ  የአገሩ ባለቤት ሳይሆን የለገደንቢም ሆነ ሌሎች ማአድኖች እንዲቆፈሩ ማድረግ የሌቦቹና የዘራፊዎቹ ስሳይ ማድረግ ብቻ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ከዚያ ጉዳት እንጂ ምንም ጥቅም አያገኝም። ስለዚህ ይህ ትውልድ ሁለት ምርጫ አለው። አንደኛ፣ ከቻለ ቶሎ ተደራጅቶና ታጥቆ የአገሩ ባለቤት በመሆን ወርቁንም ሆነ ሌሎች ሃብቶችን  ለራሱና ለልጅ ልጆቹ ጥቅም የሚያውልበትን ስረዓትና ህግ ዘርግቶ መጠቀም። ሁለተኛ የአሁኑ ትውልድ ተደራጅቶና ታጥቆ የአገሩ ባለቤት መሆን ካልቻለ የከረሰ ምድር  ሃብቱም ሆኑ ሌሎች ሃብቶች ተዘርፈው እንደያልቁ  ሌቦቹንና ዘራፊዎቹን አድኖ  በማባረር ሃብቱ ተጠብቆ  ማንም ሳይነካው ለሚቀጥለው  ትውልድ  እንዲተላለፍ  ማድረግ።
5ኛ፣ እስከ አሁን ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የአከባቢ መውደም የሌቦቹና የዘራፊዎቹ ንብረት በተገኘበት ተወርሶ ለካሳና አከባቢውን ወደ ነበረበት ለመመለስ  እንዲውል ማድረግ። ስለዚህ በየአከባቢው ያለው ሃብት ተጭኖ እንዳይሄድ አፈጣኝ እርምጃዎችን መውሰድ።
6ኛ፣ ከዚህ በኃላ ከሌቦቹ ጋር የሚሰራ ወይም የዘራፊዎቹ ተላላኪዎች ለመሞት ከልፈለጉ በስተቀር  በየትኛው የኦሮሚያ አከባቢ እንዳይንቀሳቀሱ በህግ ማገድና ህጉ ከተጣሰ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ።
 BBC Amharic reported this in December 2017
~~በተጨማሪም ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን ወልደው ከአካል ጉዳት ነፃ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ማርገዛቸውን እንደሚደብቁ፣ የአካል ጉዳት ያለበትን ህፃን የወለዱ እናቶችም ከሰው አይን ከልለው በቤት ውስጥ ደብቀው እንደሚያሳድጓቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
~~ለፋብሪካው ከሚደረገው ከፍተኛ ጥበቃ የተነሳ መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት ተጠቅመው በፋብሪካው ውስጥ ገብተው የቁጥጥር እና ክትትል ስራ ማድረግ እንዳልቻሉ የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቦሬ ጦና ይናገራሉ።
~~ሰራተኞችንም በሚቀጥሩበት ወቅት ህጉ በሚያዘው መሰረት እንደማያሳትፏቸውም ከድርጅቱ የሚያገኙት ምላሽም “እኛ በእናንተ ሳይሆን በፌደራል መንግስት ነው የምንመራው” የሚል እንደሆነም ይናገራሉ።
~~የስራ እድል ማግኘትን ጨምሮ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ የማእድን አምራች ድርጅቶች ጥቅም እያገኘን አይደለም፤ ከዚህም አልፎ ችግር እየደረሰብን ነው በማለት የወረዳው ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ሰልፍ ወጥተዋል።
ጃፋር ጉደታ
አረመኔው የህወሓት መንግሥት ጠባቂና ተቋርቋሪ ባልነበረው የኦዶ ሻኪሾ የኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፈፀማቸው ወደር የሌላቸው የሠቆቃ ወንጀሎች ጥቂቶቹ እነሆ እየተጋለጡ ይገኛሉ።
አቅሙና ሙያው ያላችሁ ፣ ለሠው ልጅ ፍጡር ክብርና ስዕብና ያላችሁ ወገኖች ይህን ለሰሚም የሚሠቀጥጥ በሰው ልጅ ላይ የተፈጠረ ኢ-ሠብአዊ ወንጀል ተጣርቶ ወንጀሎቹ ካሉበት ተፈልገው ቦታ ሁሉ  ለፍርድ እንዲቀርቡ ለተጎጂዎችም ካሣና እንክብካቤ እንዲደረግና ይህ ወንጀል ተጣርቶ ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ ጉዳቱን ያደረሰው ካምፓኒ ምድሮክ የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት እገዳ (temporary injunction) እንዲደረግበት ትረዱ ዘንድ እንጠይቃለን። በተለይም አዲሱ የኦቦ ለማ መገርሣ አመራር በዚህ አሣፋሪ ጉዳይ እነዚህን ወንጀለኞች ለፍርድ በማቅረብ ወይም ባለመቅረብና በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን  ረገድ ፈተና ውስጥ መውደቁን አጥብቀን እንጠቁማለን።
Filed in: Amharic