>
5:01 pm - Sunday December 3, 0051

የአማራ ትግል መጠለፉ ነው!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

እኔ እንዴት ዓይነት ባለጋራ እንደጣለብን አላውቅም!!! አማራ ለራሱ በሚፈለገው ደረጃ ለመንቃት ተስኖታል ጭራሽ ደሞ በዚህ ችግሩ ላይ ጠላት መንገዱ ላይ እየቀደመ የተወሳሰበ ሴራ እየተከለበት ይገኛል፡፡ አማራ ይሄንን ጠላት የሚያሴረውን የተወሳሰበ ሴራ እንዴት ተወጥቶት ራሱን ከጥፋት መታደግ እንደሚችል እግዚአብሔር ይወቀው!!!
በጣም ከጥቂቶች በስተቀር አሁን የአማራ ተቆርቋሪ መስለው መድረኩን ይዘውት የምታዩዋቸው ተዋንያን በሙሉ የወያኔ ተቀጣሪዎች ናቸው፡፡ ከመሃላቸው ታስረው የተፈቱ ሁሉ አሉ፡፡ እነማን ናቸው ንገረን? እንዳትሉኝ፡፡ ብነግራቹህም የምታምኑኝ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዶቹ ከሁለት ሦስት ዓመት በፊት “ወልቃይት የጎንደር አይደለም!” ብለው የተከራከሩኝ ሁሉ አሉ፣ አንዳንዶቹ ከስድስት ዓመት በፊት የጻፍኩትን “የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሒደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!” በሚለው ጽሑፌ ዘረኛ ያሉኝ ሁሉ አሉ፣ “ምን አማራ አማራ ትላለህ!” ይሉኝ የነበሩ ሁሉ አሉ፡፡
ዛሬ ግን ዋነኛ የአማራ ብሔርተኝነት ተዋናይ መስለው ታማኝነትም አግኝተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ድንገት ተገልብጠው የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኝ ሆነው መታየታቸው በራሱ የሚጠቁመው እውነት አለ፡፡
ብቻ ግን አንድ መለያ ልንገራቹህ፦ 
በአንድም በሌላም መንገድ ዐቢይን የለውጥ ሐዋርያ እና ለፍትሕ ለዕኩልነት የቆመ ቆራጥ መሪ አስመስሎ ሲናገር የምትሰሙት ሁሉ እሱ ያለምንም ጥርጥር ወያኔ የአማራ ብሔርተኝነትን ትግል እንዲጠልፍ ወያኔ አስርጎ ያስገባው ቅጥረኛ እንደሆነ እወቁ፡፡ ለጊዜው ይሄንን እንደመለያ ተጠቀሙበት፡፡
የዐቢይና የለማ አሥተዳደር “አማራ የት አለ?” እያሉ በመብራት እየፈለጉ እንደ አዲስ አማራን ማሳደድ፣ ማፈናቀል፣ መግደል በቀጠሉበት በዚህ ወቅት ዐቢይንና ለማን እንደ የለውጥ ሐዋርያት፣ ለፍትሕ ለዕኩልነት የቆሙ ቆራጥ መሪዎች አድርጎ የሚቆጥር፣ የሚያስብ፣ የሚያምን የአማራ ብሔርተኛ አለ ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ እጅግ ሲበዛ የዋህና ማስተዋል የተሳነው ነው፡፡
እንዲህም ስላቹህ ዐቢይ/ወያኔን አጥብቀው የሚቃወሙ የሚያወግዙ ሁሉ ትክክለኛ የአማራ ብሔርተኛ ናቸው ማለቴ አይደለም፡፡ እንደምታውቁት ወያኔና ሸአቢያ በግማሽ አማራ በግማሽ ትግሬና ኤርትራዊ የሆኑ ወገኖቻቸውን በአማራ ብሔርተኝነት ትግል አስርገው በማስገባት ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ስሜትን በአማራ ሕዝብ ላይ ለማስረጽ ሲሠሩ የቆዩ ቅጥረኞች እንዳሉ የምታውቁት ነው፡፡
እነኝህ ቅጥረኞች ለብሔረሰቦች መብት የቆሙና የሚያስቡ በመምሰል ተገንጣይ የጥፋት ኃይሎችን ሁሉ “መገንጠል መብታቸው ነው! ካልፈለጉ ልናስገድዳቸው አይገባም!” እያሉ ትግሬውን፣ ኦሮሞውን፣ ጋንቤላውን፣ ቤንሻንጉሉን፣ አፋሩን፣ ሱማሌውን ወዘተረፈ. አስገንጥለው አማራን ዙሪያውን በጠላት አስከብበው ከዓለም ጋር ያለውን የመገናኛ አውታሮች በመቁረጥ አዳክመው ዙሪያውን በከበቡት ጠላቶቹ በቀላሉ አስቀጥቅጠው ከምድረ ገጽ ተመንጥሮ እንዲጠፋ ማድረግ ነው ስውር ዓላማቸው፡፡
አማራ ሆይ! ፈተናህ እጅግ ውስብስብና እጅግ ከባድም ነውና እባክህን ንቃ! ንቃ! ንቃ!!!…. ንቃና ያለብህን ፈተና በሚመጥን ደረጃ ወገብህን አስረህ ለትግል ተነሥ!!! የዋህነቱን፣ ቅንነቱን፣ ይሉኝታውን….  ጣል እርግፍ አድርገህ ተውና ቁረጥ ጨክን!!!…
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
Filed in: Amharic