>
5:18 pm - Saturday June 15, 7230

ዶ/ር አብይ ከባድ ማስጠንቀቂያ ደረሳቸው!!! (ልጅ አቤል)

ከጊዜው ጋር ያልዘመኑ ወንዝ ማያሻግሩ ትዛዞች
– ከወደ መቀሌ ሰሞኑን የተሰማው ወሬ ሁሉን ኢትዮጵያዊ አስገርሞዋል።
– በጣም ጊዜውን ያልመጠኑ ወይም ለዚህ ዘመን አስተሳሰብ ይሆናሉ ከማይባሉ ዝቅ ያሉ ንግግሮች ተሰምተዋል።
– በተለይም አቦይ ስብሀት ያሉት ከማስገረም አልፎ ብዙዎችን አስቋል።
– ” ኢትዮጵያ ካለ ህወሀት ባዶ ናት” ንግግራቸው ብዙ እያስተቻቸው ነው።
– የመስፍን ንግግርም ምን አይነት ጉድ ነው አስብሎዋል፤  የሳቸው ንግግር። ” ጦርነት ላይ ነን” የሚል ነበር።
– ሆኖም የዶ/ር ደብረ ጽዮንን ንግግር ግን በተለይም ከኦሮሞና ከአማራ ብሄሮች በኩል ከባድ የመልስ ምት እየተሰጣቸው ይገኛል።
” በፍፁም የትግራይ ህዝብ ደስተኛ አይደለም የታሰሩት መፈታት አልነበረባቸውም ። የመከላከያ ሰራዊቱንም ያለ ህወሀት ፈቃድ ጠ/ሚ በግል ማሰልጠን አልነበረባቸውም የነፃ ሚዲያ ፈቃድ በተለይም አሸባሪ ናቸው የተባሉትን ወደአገር ግቡ ማለት አይችሉም። ጭራሽ የኮማንድ ፖስት መነሳት ድፍረት ነው ንቀት ነው። የኦሮሞ ህዝብ ወደስልጣን መምጣት የኦፒዲኦ ማንሰራራት አልነበረበትም ቀጣይ የታቀዱ እቅዶች ፀረ ሽብር ህጉ ህገ መንግስቱ መሻሻል የለበትም ትክክለኛ ህግ ነው ይህ ሁሉ የትግራይ ህዝብን በእጅጉ እያስቆጣ ነው” የሚሉ ንግግሮች ፅሁፎች የመድረክ ላፕ ክርክሮች በትግራይ ክልል በከባድ ውዝግብ ቀጥለዋል።
ከዚህ ባለፈ ዶ/ር ደብረ ፂወን ሰሞኑን አብይን በማስጠንቀቂያ መልክ የሰጡት ንግግር ብዙወችን በእጅጉ አስቆጥቱዋል።
” አብይ በዚህ ከቀጠለ የትግራይ ህዝብ ያልተፈለገ ነገር ያደርጋል ” በማለት ከባድ ንግግር አርገዋል።
ሆኖም ከወጣቱ የትግራይ ክፍል በኩል ከባድ ፍጥጫን አስነስቱዋል….
የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብን በውሸት እያጣላችሁ በሁዋላ ቀር አስተሳሰብ ስልጣን ላይ መቆየታችሁን ህዝቡ ነቅቱዋል ከእንግዲህ እንደዛ እያደረጋችሁ መቀጠል አትችሉም በሀሳብ ማሸነፍ ካልቻላችሁ በመሳሪካ ከእንግዲህ መቀጠል ከባድ ነው ጊዜው እጅግ ከእናንተ ቀድሞ ሄዶዋል የአማራና የኦሮሞን ህዝብ ውሸት እየዘራችሁ እስከዛሬ የመጣችሁበት መንገድ ይበልጥ የትግራይን ህዝብ እንዲጠላ ነው ያደረጋችሁት ከእንግዲህ በዚህ መንገድ እየሄዳችሁ እኛን ወደሁዋላ አታስቀሩን በእወቅት ከፍ ያሉ በአመራሩ መድረክ ከእናንተ እጅግ ለሚሻሉ ወጣቶች ስልጣኑን ስጡ የህወሀት መሪወች ውረዱ ቦታው በወጣት እና በተማሩ ዘመናዊ አስተሳሰብ ባላቸው የትግራይ ትውልድ ይተካ ዘመኑን ማየት አልቻላችሁም አሁን ኢትዮጵያ በደርግ ዘመን ያለችው አይደለችም ህወሀት አስተሳሰቡ ሊቀየር ይገባል የሌሎች ክልሎች ወጣቱ ትውልድ ሲዘመን የትግራይ ወጣት በህወሀት ሁዋላ ቀር አስተሳሰብ ወደሁዋላ እየቀረ ነው እስካሁንም ጦርነት ፀረ ሽብር የጫካ ትግል አስተሳሰብ በቃን ዘመኑ ተቀይሮዋል …..የአማራ እና የኦሮሞ ወጣቶች በአስተሳሰብ ከፍ ሲሉ ህወሀት የትግራይን ወጣት በጎጠኝነት አስሮ ይዞታል የጠ/ሚ አብይ ሀሳብ ለአገራችን ዘመኑን የመጠነ ሀሳብ ነው የትግራይ ወጣት ከዘመኑ ጋር ይራመድ ዘንድ ለወጣቱ ትውልድ አመራሩን ስጡ በፍፁም የእናንተ ሀሳብ ለትግራይ ቀጣይ ትውልድ ጎጅ ነው ወታደር መያዝ ከእንግዲህ ህዝብን አያቆመውም አለም እየተቀየረች ወጣቱን የትግራይ ክልል ማዘመን ከአለም ጋር እንዲራመድ ማድረግ ስትችሉ ኦሮሞ ጠላትህ ነው አማራ ጠላትህ ነው በሚል መርዝ ብዙውን ወጣት ወደሁዋላ እያስቀራችሁት ነው ባለመዘመናችሁ ምክንያት እስካሁን ከጫካ አስተሳሰብ አልወጣችሁም ጊዜው የእናንተ ዘመን አስተሳሰብ አይደለም የአማራ ህዝብ ጠላታችን አይደለም በውስጦ አቅፎ ያኖራቸው ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ የትግራይ ወንድሞቹን ነው ኦሮሞ ጠላታችን አይደለም በክልሉ ብዙ ትግራዮችን አቅፎ እያኖረ ነው….የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ጠላታችን ቢሆን ኖሮ አንድ ቀን አያሳድረንም ነበር የእናንተ መሳሪያ ሳይሆን የጠበቀን የህዝቡ አስተዋይነት ነው ኢትዮጵያዊነትን በጎጥ ከልላችሁ ህዝቡን ከፋፈላችሁት ይሳካል መስሎዋችሁ ብዙ ጣራችሁ አሁን የእናንተ ሀሳብ ውድቅ ሆኖ ኢትዮጵያ ወደሰላም ወደ አንድነት መታለች መለያየቱን ተውትና በሀሳብ የበለጣችሁን አብይን አክብሩ እምቢ ካላችሁም ከሱ መብለጥ የምትችሉት በሀሳብ ነው የተሻለ ሀሳብ አምጡ አለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የናንተን ክላሽ እና ወታደር የሚፈራበት ጊዜ አብቅቱዋል ህውሀት ያቀደው ሁዋላ ቀር ግድስ እራሱን ብቻ ሳይሆን የትግራይን ህዝብ ወደ ከባድ መንገድ ይከተዋል ያቁም የሚሉ ክርክሮች ጦፈዋል።
ሆኖም የህወሀት የቀድሞ ታጋዮች 
መስፍን ደብረ ፂወን አቦይ ስብሀት ….አብይ ላይ እጣታቸውን ቀስረዋል….ጦርነት ላይ ነንም ብለዋል።
ወጣቱም የትግራይ ክልል ህዝብ ግን እጅግ ሳላደንቅ አላልፍም በሳል ትውልድ በእውቀት የሰለጠነ ከስር ብቅ እያለ ነው በስልጣኑም መስመር ቢሆን በእውቀት ብቻ የሚያምን ትንሽም ቢሆን ብቅ ብቅ እያለ ከነ አቦይ ስብሀት ጋር ትንቅንቅ ላይ ሆኖ እያየን ነው።
Filed in: Amharic