>

የጌታቸው አሰፋ መነሳት ማለት ለኢትዮጵያውያን..... (ኤርሚያስ ለገሰ)

የጌታቸው አሰፋ መነሳት የተደራጀ ሌብነትና ዝርፊያ፣ ዘረኝነት፣ ዘር ማጥፋት፣ የስልጣን መባለግና በእርስትነት መቆጣጠር፣ መሀይምነት፣ ወንጀል፣ ግፍና የአንድ ቡድን የበላይነትን የመፀየፍ “ምልክት” ( ሐውልት) ተደርጐ የተወሰነ ከሆነ የሚያስመሰግን ነው። ይሄን እንዲያረጋግጥ ደግሞ ጌታቸው በጡረታ መሰናበቱ ይፋ ሊሆን ይገባል። አለበለዚያ በተነገረም ሆነ ባልተገለፀ ሁኔታ የአሁኑን የአባዱላ ቦታ ( የደህንነት አማካሪ) ተክቶ ካየነው በጣም አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭ ይሆናል።
እናም እኛ የቶማስ ልጆች ጠቅላይ ሚኒስትራችንን የጌታቸውን መዳረሻ የት አደረግከው ብለን መጠየቅ እንፈልጋለን። ሞጋች ደጋፊዎችም አይደለን!!
# የግርጌ ማስታወሻ፣
 ጌታቸው አሰፋ የህውሓት ፓሊት ቢሮ እና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ነው። በዚህ ሰው ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ውሱን ነው። ከፍተኛ ስልጣን ያለው ህውሓት ነው። እናም ምንአልባት የትግራይ ክልል ከፍተኛ ስልጣን ላይ የመገኘት እድሉ ሰፊ ይመስለኛል። ባደረገው! …አሊያም የጠቅላዩ የደህንነት አማካሪ በመሆን በእውነተኛ ስልጣን ደህንነቱን፣ መከላከያውንና ፌደራል ፓሊስን ” በፀጥታው ምክር ቤት” ሽፋን በቀጥታ የሚያዝበት ሁኔታ ይፈጠራል።
Filed in: Amharic