>

ከእኛው በዘረፉት ሀብት፤ ... በፕራይቬታይዜሽን ስም መልሰው ሊገዙን ተመቻችተዋል!!! (ሳሙኤል ሀይለሥላሴ)

=> ተሓህት (ህወሀት)፤  . . . እነሱ የአክሱም ኦፕሬሽን በሚል ስያሜ የሚጠሩት፤ . . . ህዝብ ግን የአክሱም ሽብር በሚል ስያሜ በሚያውቀው ወንጀል፤ . . . ባንክ ዘርፏል።
ይህንን ወንጀሉን፤ በአደባባይ በትልቅ ስክሪን ለወጣቶች እያሳየ ተኩራርቶበታል።  . . . ዛሬም ታዲያ ይቺ ሌባ በመግለጫዋ፤ . . . “ነባሮቹ ሌቦቼ በደንብ አልተከበሩም” ብላ ስታለቃቅስ፤ . . . ይህንን ከመዐት አንዱን ወንጀሏን አስታወሰችኝ።
=>14ቱ የተሓህት (የህወሀት) ወንበዴዎች፤ . . . በአክሱም ሽብር ወቅት የነበራቸው የወንጀል ድርሻ፤ . . . !
•~ አባይ ፀሃየ እና ነጻነት፤ . . . አንድ ገጀራ እና ሽጉጥ ታጥቀው፤ ወደ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት አካባቢ በመጠጋት የስልክ መሥመሮችን እንዲቆራርጡ፤
* አባይ ፀሃየ የአክሱም ልጅ ስለነበረ ሕዝቡ እንዳያውቀው ከሹራብ የተሠራ ማስክ እንዲያጠልቅ ተደረገ::
•~ “አስገደ እና ግደይ ዘርዐ ጽዮን፤ . . . ግደይ የአእምሮ በሽተኛ መስሎ፤ . . . አስገደ ደግሞ ባለጉዳይ መስሎ፤ ኡዚ ታጥቀው፤ በፖሊስ ጣብያው አካባቢ እንዲንቀሳቀስ::
•~ ብርሃነ መስቀል እና ንርአ፤ . . . ደግሞ እንደምንም ብለው መኪና አግኝተው የተዘረፈውን ገንዘብ ይዘው በአስቸኳይ እንዲወጡ፤
•~ ሰበሮም እና አልዓሚን፤ . . . ባንክ ቤቱ ውስጥ ገብተው ቁልፍ ከሥራ አስኪያጁ በመቀበል ገንዘቡን ከካዝና እንዲያወጡ፤
•~ አረጋዊ በርሄ እና አውዓሎም፤ . . . ከሁለት ታጋዮች ጋራ ኾነው በባንክ ቤቱ አካባቢ የሚፈጠረውን ሁሉ እንዲከታተሉ፤
•~ ቀለበት፤ . . . ልክ እንደ ኦፕሬሽን ሙሴ ከተማ ውስጥ የማደናገር እና የማተራመስ ተልእኮ ተሰጠው::
•~ ሙሴ፤ . . . ደግሞ እነዚህን ሁሉ ተልእኮዎች በግንባር ቀደምትነት እየተንቀሳቀሰ እንዲያስተባብር፤
•~ ነሐሴ 19 ቀን 1967ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የአክሱም ሽብር ተካሄደ። በሽብሩ 350 ሺሕ ጥሬ ገንዘብ፣ 71 የተለያዩ መሣርያዎች እና 700 ጥይቶች ተዘረፉ። . . . 3 ፖሊሶችና 1 የባንክ ሰራተኛም ተገደሉ።
#ሌባ ሁላ ደግሞ አክብሩኝ ይላል እንዴ?፦) እንዲህ እንዲህ እያሉ፤ . . . ከኢትዮጲያና ከኣትዮጲያውያን ላይ በዘረፉት ሀብት፤ . . . በፕራይቬታይዜሽን ስም መልሰው ሊገዙን ተመቻችተዋል።
Filed in: Amharic