>

ፖለቲካ ቼዝ ነው ይሉሃል እንዲህ ነው !! (ሀብታሙ አያሌው)

በቼዝ ጫወታ አሸናፊ የሚያደርግህ ወዴት መሄድ እንዳለብህ ማወቅህ ብቻ ሳይሆን ተጋጣሚህ ወዴት ሊሄድ ለእንደሚችል የመተንበይ ብቃት ሲኖርህ ነው። ህወሓት ኢህአዴግ  በአራቱም ማዕዘን ግፍ እና ሰቆቃ በማብዛት ኢትዬጵያዊነትን ለዘመናት ዋጋ ከከፈሉለት  ከኢትዬጵያውያን  እጅ ለማስጣል ማንነትን መስረት ያደረገ ጥቃት መፈፀምን ዋነኛ ስልቱ አደረገ።  ብሶት የወለዳቸው የብሔር ነፃ አውጪዎች ወደየ ብሔራቸው  መንጎዳቸውን ሲያረጋግጥ እራሱን የኢትዬጵያ አዳኝ አድርጎ ብቅ አለ። የብሔርተኝነትን አስከፊ ገፅታ ለማሳየትም :-
  ጉጂ     እና    ጌዲዬ 
  ጉራጌና  እና    ቀቤና 
  ሲዳማ   እና    ወላይታ
  ኦሮሞ    እና    ሶማሊያ
  አማራ    እና    ቤንሻንጉል 
  አፋር     እና     ትግራይ 
  ቁጫ      እና     ጋሞ 
ዛሬም በዘር ፖለቲካ እሳት እየነደዱ ነው። ኢህአዴግ ደግሞ በዶክተር አብይ ሙሴነት ዘረኝነትን እያወገዘ የአንድነት ሃይልና የኢትዬጵያ አዳኝ ሆኖ ተከስቷል።  ተቀባይነት ማትረፍ የጠላትህን አሰላለፍ አይተህ ንግስቷን ይዘህ ቼዝ ማለት እንደዚህ ነው።
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው 
ወይ ጠባቂ መልዐክ ወይ አበጀ በለው 
መጥቶ ከቀንበሩ የማይገላግለው
ድል ያልሰመረለት ትግል ሳይቸግረው
           ብሎ እንደገጠመው መሆኑ ነው።
ኢህአዴግ ከዘር  የፖለቲካ አደረጃጀት ወጥቶ አንድ ህብረ ብሔራዊ ድርጅት የመሆኑን ጉዞ እያሳለጠ ስለመሆኑ የታችኛዋ ደብዳቤ ትናገራለች። አሁን ዶክተር አብይ በርታ ማለት ግንጥል ጌጥ ነው።  ከሆነ አይቀር ኢህአዴግ በርታ በማለት መስማማት የተሻለ ይሆናል።  የመስመሩ ውጤት ይልሃል እንዲህ ነው።
             ግልባጭ ለነ እከሌ
Filed in: Amharic