>

በፖለቲካ Sucide  ራሷን በራሷ ያጠፋችውን ህውሃትን  ኑ እንቅበር!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የህውሃትን መግለጫ ምንም አዲስ ነገር የለውም የሚሉት ሰዎች ኢህአድግ የሚባለውን ድርጅት ባህሪይ ካለማወቅ የሚሰነዘር አስተያየት ነው።
ኢህአዴግ  ” ዴሞክራሲያዊ ማእከላዊነት ” በሚባል ጠርናፊ አስተሳሰብ የሚመራ ግትር ግራ ዘመም ፓርቲ ነው። አንድ ድርጅት የፈለገ የሀሳብ ልዬነት ቢኖረው  ኢህአድግ ከተባለው ጃንጥላ ወጥቶ ድርጅቱን የሚቃረን መግለጫ አያወጣም።
ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ ህውሃት ፣ኦህዴድና ዴኢህዴን ለሁለት እንደ ጣቃ ጨርቅ የተተረተሩት “ቦናፓርቲዝም ” በሚባል ተራ ፈረንሳይ ወለድ ተረት ተረት ነው። የአሁኑ የህውሃት መግለጫ ኢህአድግ የቆመበትን ዋና መሰረት (Base)  የደረመሰ ነው።ለምሳሌ የአልጄርሱን ስምምነት ኢህአዴግ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሲቀበል ህውሃት ግን ወደ ድሮው አቋሙ ተመልሶ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
የድርጅቱንም ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የአደረገውን ምደባ  በይፋ በመግለጫ ተቃውሟል
ይሄ  ከባድ ወንጄልና ህገመንግስቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የሰጠውን ስልጣንና ተግባር የሚቃወም ነው።
ህውሃት በተጨማሪም  በመግለጫው በ40 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጇል ። ህውሃት ትናንት ባወጣው መግለጫ ራሱን ወደ ሽብርተኛ ድርጅት አውርዶ በፌደራል ስርአቱ ላይ በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጇል።
የዛሬ 16 አመት ህውሃት  ለሁለት ሲሰነጠቅ ብአዴን የሚባል  በድን ድርጅት ኦክስጅን ቀጥሎላቸው መተንፈስና መትረፍ ችለዋል።
አሁን ሶስቱም ድርጅቶች ኦህዴድ ፣ዴኢህዴንና ህውሃት መግለጫ አውጥተዋል። ኦህዴድና ዴኢህዴን በአንድ መስመር ተሰልፈዋል ህውሃት አፈንግጧል። አሁን የሚጠበቀው የብአዴን ነው። ብአዴን አሁን ህውሃት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት በአወጀችበትና እናት ድርጅቴ በሚለው ኢህአድግ ላይ ባፈነገጠችበትና ህገመንግስቱን በተቃረነችበት በዚህ የሽብር ተግባሯ እንደ 1993ቱ ወደ ገደሉ በብርሃን ፍጥነት እየተምዘገዘገች ወዳለችው ህውሃት ጎን የሚቆምበት ምክንያት የለም።
የኢትዮጵያ ህዝብም ህወሃትን ለመቅበር ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለምና ከዶ/ር አቢይ አህመድ ጋር በመሆን በፖለቲካ Sucide  ራሷን በራሷ ያጠፋችውን ህውሃትን  ኑ እንቅበር ።
ተያያዥነት ስላለው ቀጣዩን ጽሁፍ ያንብቡ።

ሕወሀት በግድ ተሸንፏል ሞተ ማለት ግን አይደለም!!!

ፋሲል የኔአለም
የህወሃት መግለጫ የተምታታ ይሆናል ብዬ ገምቼ ነበር። ተሳስቻለሁ።  የተምታታ አይደለም። ግልጽ ነው። ህወሃት መሸነፉን ያመነበት መግለጫ ነው። በባድመም ሆነ በመንግስት ድርጅቶች ላይ የተወሰነውን ውሳኔ የተቀበለበት መግለጫ ነው። ተከታዮቹ ተሸነፈ እንዳይሉት  ብቻ ነው በአንድ በኩል “አትርሱኝ” እያለ እየተማጸነ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ “እታገላለሁ” የሚል ዲስኩር የሚያሰማው። ለዚህ መግለጫስ  እንኳን አስቸኳይ ስብሰባ፣ ስብሰባ የሚባል ነገር ከእነ አካቴው አያስፈልገውም ነበር፤  አበል ባይኖረው ኖሮ፣ እነ ደረጺዮን ውስኪ ቤት ቁጭ ብለው ሊጽፉት ይችሉ ነበር። ለማንኛውም የህወሃት ደጋፊዎች እርማችሁን አውጡ። ህወሃት ተሸንፏል። የአብይ ደጋፊዎች ደግሞ መደነስ ትችላላሁ። ግን አንድ ነገር ልብ በሉ፣ ህወሃት ተሸነፈ ማለት ሞተ ማለት አይደለም። ህወሃት ሞተ የሚባለው አስተሳሰቡ ሲሞት ብቻ ነው፤ የህወሃት ቫይረስ በተለያዩ ቦታዎች ተሰራጭቶ እንደሚገኝ መረሳት የለበትም።  የቫይረሱን ማጥፊያ መድሃኒት ደግሞ አብይ የፍቅር ፋርማሲ ውስጥ መግዛት የምትችሉ ይመስለኛል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም  እያሸነፈች  ትኑር!

ሶስቱ ፓርቲዎች በድርጅታቸው ህገደንብ መሰረት ህውሃትን በአስቸኳይ ማባረር አለባቸው

ቬሮኒካ 
ዛሬ ህውሃት ባወጣው ድርጅታዊ መግለጫ  የኢህአድግ አራት ድርጅቶች የሚያጣብቀውን  “ዴሞክራሲያዊ መአከላዊነት”  የተባለ ሙጫ  በማላቀቅ  ከእናት ድርጅቱ አፈንግጧል። ህውሃት በድርጅቱ ህግ መሰረት  በዲፋክቶ ከኢህአድግ ውጭ ሆኖ ወደ አጋር ወይም ተቃዋሚ ፓርቲነት ወርዷል።
ሶስቱ ፓርቲዎች በድርጅታቸው ህገደንብ መሰረት ህውሃትን በአስቸኳይ ማባረር አለባቸው።
መርህ ይከበር   !!!!!!
Filed in: Amharic