>
5:16 pm - Monday May 24, 4827

ታጥቦ ጭቃ ፣ አድሮ ቃሪያ፣  ከርሞ ጥጃ የሆነ ድርጅት! አሁንስ እያሳዘነኝ ነው!!! (አንዷለም በከቶ ገዳ)

ከአንዲ ፈጌሳ በህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠው መግለጫ ላይ የተሰጠ መግለጫ
ህወሃት ማምሻውን የሰጠችውን መግለጫ ተከትሎ የተፈጠረውን ግራ መጋባት አስመልክቶ በውስጥ መስመር እየቀረቡ ያሉ የበርካታ(3 ሰዎች) ጠያቂዎችን ሃሳብ በማክበር የሚከተለውን የመግለጫውን ተዛማች ትርጉም ሰጥተናል፡፡
መግለጫውን በአጭሩ “አንፈርስም! አንታደስም!” የሚለው የአሌክስ የግጥም መድብል መጻፍ ርእስ የበለጠ ይገልጸዋል፡፡ መግለጫውን ለማዘጋጀት ህወሃት የተጠቀመቻቸው ኢንግርዲየንቶች…..2 ኪሎ አድርባይነት…ግማሽ ኪሎ አስመሳይነት እና ..4 የሾርባ ማንኪያ “ትርጉም አልባነት ” እና አንድ የሻይ ማንኪያ እብሪት ናቸው፡፡
ለምሳሌ …ባድመን በተመለከተ…..ምን እንዳለች ራሱ በትክክል ያልገባኝ ሲሆን የገባኝን እንኳን በአጭሩ ለመሞከር “ስምምነቱ ድሮም የነበረ ነው…..እንፈልገዋለን ..ብላብላ …..ግን ጥንቃቄ ይደረግ …..”……ምን ማለት ነው ይሄ!?….”ጥንቃቄ ይደረግ” ለማለት መግለጫ ማውጣት ያስፈልጋል?……ድሮስ የሀገር ጉዳይ… ያውም የድንበር ማካለል ጉዳይ ያለጥንቃቄ ሊሰራ ኖሯል?!….የምን አድርባይነት ነው?! ማንንስ ለማስጠቆር ነው!? “በአካባቢው ያለው ህዝብ ለከፈለው መስዋትነት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመተባበር እርዳታ ይሰጠው”…..ይሄስ ምን ማለት ነው ..?! በጉቦ ሀገሩን እና ማንነቱን ይሽጥ ነው….?!
“ለወሬ ቸኩለናል…..ለህዝቡ መናገር አልነበረብንም” ….አቶ ዘርአይ የሚባው ሰውዬ(ዘ ሃጫሉ ኬዝ ጋይ ) አሁንም አለቀቀም እንዴ !? የተሰበሰቡት ስለ ሀገራችን መሰለኝ! የወሰኑትን ማናቸውንም ነገር በፍጥነት ማወቅ መብታችን ነው …እስከ መቼ ህዝብ በገዛ አገሩ ጉዳይ እንዳላዋቂ እና እንደ ባዳ ይታያል……!? ሰላሳ ምናምን በአግባቡ ያልወከልናቸው ሰዎች ተሰብስበው በእጣ ፋንታችን እና በአንጡራ ሀብቶቻችን ላይ መወሰናቸው ሲያንስ ጭራሽ “ማውራት አልነበረብንም”?!
“ነባር ታጋዮች እውቅና ይሰጣቸው…”…….ይሄ ቀላል ነው ፡፡ስለ መለስ ሌጋሲ አብይ ለምን ዝም አለ ነው ነገሩ ፡፡ በሉ እንደፈረደብን አዝጉን ደግሞ !
“ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር አብረን እንሰራለን….”ይሄም ቀላል ነው……አረና ከአሁን ወዲያ ጀለሳችን ነው …..ኦህዴድ …ለእነ ኦፌኮ እና ኦዴግ ፊት ከሰጠ …ብአዴን አይኑ እያየ አ.ብ.ን ባህርዳር ላይ ሲቋቋም ዝም ካለ እኛም አረናን እንታገሰዋለን ነው ነገሩ ፡፡ይሄ ጥሩ ነው…ክፉ ጎረቤት እቃ ያስገዛል አይደል የሚባለው……በፉክክርም ቢሆን ዲሞክራሲያዊነት ይለምልም፡፡
“እነ ቴሌ እና መብራት ሲሸጡ የኢትዮጲያውያንን ጥቅም ባስቀመጠ መልኩ እንዲሆን ጥንቃቄ ይደረግ” …ይሄም ግልጽ ነው…..ኤፈርት ኢትዮጲያዊ ነው አይደል?…ሃሳቡ ይሄ ካልሆነ አሁንም “ጥንቃቄ ይደረግ” ለማለት መግለጫ ድረስ የሚያስደርስ ነገር አለ ብዬ አላምንም፡፡፡
“አመራሮቻች የሚነሱበት አግባብ ይመርመር”…..ቅድም ስንት ማንኪያ እብሪት ነበር ያልኩት?!
“የኢህዲግ ስራ አስፈጸሚ ምክር ቤት በአስቸኳይ ይጠራ”…ቆይ በቀደም እነሱም ባሉበት አይደል እንዴ የተወሰነው !? ነው ወይስ ተኝተው ነበር?! ማን አፋቸውን ይዟቸው ከስብሰባው ወጥተው ነው አሁን ይሄ ሁሉ አዋራ ማስነሳት?!…..ታጥቦ ጭቃ ፡አድሮ ቃሪያ፡ ከርሞ ጥጃ፡ የሆነ ድርጅት አሁንስ እያሳዘነኝ ነው፡፡
ለማንኛውም በሰፊው እንመለሳለን…..እስከዛው እነ አዌ ማኛ እና ሌሎች የቀድሞው ስርአት ናፋቂ የሆናችሁ የደቡብ ልጆች በሙሉ “ፍቼ ጫምባላላ” ብያለሁ!
ይመቻችሁ
Filed in: Amharic