>

ባድመን ለኤርትራ የሸጡ ባንዳዎች መቀለ ተሰብስበዋል፤ ከእነዚህ ሀገር ሺያጮች ምን ትጠብቃላችሁ?!? (ስዩም ተሾመ)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርስ ስምምነትን ለመቀበል መወሰኑን አስመልክቶ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከትላንት ጀምሮ መቀለ ላይ ስብሰባ መቀመጡን ሰምተናል፡፡ “በስብሰባው ምን ዓይነት ውሳኔዎች ሊተላለፉ ይችላሉ?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከመሞከራችን በፊት “ተሰብሳቢዎቹ #እነማን ናቸው?” ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ በ1993 ዓ.ም ታህሳስ ላይ የተፈረመውን የአልጄርስ ስምምነት ተከትሎ ህወሓት ውስጥ በተነሳው ሽኩቻ “የኢትዮጲያን ጥቅምና ሉዓላዊነት ይጎዳል” በማለት ስምምነቱን የተቃወሙት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከድርጅቱ ተባርረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተረፈው ብቸኛ ሰው #ፀጋዬ_በርሄና #አባይ_ፀሓዬ ሲሆኑ እነሱም ጥፋታቸውን አምነውና ይቅርታ ጠይቀው ነው፡፡ ከዚያ  በተረፈ በወቅቱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያልነበሩት እንደ ዶ/ር ደብረፂዮን እና ጌታቸው ረዳ ካልሆኑ በስተቀር፣ አሁን መቀለ ላይ የተሰበሰቡት የህወሓት መስራቾችና አመራሮች በሙሉ (ከመለስና ቴድሮስ በስተቀር) የአልጄርስ ስምምነትን ደግፈው የተቀበሉ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ባድመን ለኤርትራ አሳልፈው የሸጡ #ባንዳዎች መቀለ ላይ ቁጭ ብለው ስለ አልጄርሱ ስምምነት በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ሀገር ሺያጮች ምን ትጠብቃላችሁ?

Filed in: Amharic