>
5:16 pm - Wednesday May 24, 4862

 አቶ በረከት ከመቀሌው አንጃ ጋር ምን እያሴሩ ይሆን? ምልልሱ በዝቷል?!? (ፋሲል የኔአለም)

ምናልባት አንዳንዶቻችን በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የውስጥ ትግል የተጠናቀቀ ሊመስለን ይችላል ፣ ግን አይደለም::  ልክ ነው ህወሃት እጅግ ተዳክሟል፥ በፌደራል ደረጃ ብዙ ስልጣኖችንም አጥቷል:: ነባር ታጋዮቹም ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ሸሽተዋል፥ ቢሸሹም ግን መዶለታቸውን አላቆሙም:: የዱለታው ማእከል ደግሞ በረከት ስምኦን ነው:: በረከት ባለፉት ሳምንታት በተከታታይ ወደ መቀሌ ሲጓዝ ከቆየ በሁዋላ በመሃል አቋርጦ ለህክምና ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ነበር:: ትናንት ህክምናውን ጨርሶ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰ ከሰአታት በሁዋላ ወዲያውኑ ወደ መቀሌ በሯል:: ወደ ቦሌ ሲሄድ መኪናውን እራሱ እያሽከረከረ፣ ያለ አጃቢ፣  መሄዱን ከሁነኛ ምንጭ ሰምቻለሁ:: “ለምን? ”ብዬ ስጠይቅ ያገኘሁት መልስ “ጥላውን ሁሉ ማመን አቁሟል” የሚል ነው::  በረከት ለውጡን ለመቀልበስ ቀዳዳ እየፈለገ ያለው ብአዴን ውስጥ ነው፥ ብአዴን ደግሞ ቀዳዳውን ሁሉ እየደፈነ   “አናስገባም ሰርገኛ” ብሎአል፥ የበረከትና የህወሃት ደጋፊዎችን ሁሉ ከአመራር ቦታዎች ላይ ጠራርጎ እያስወጣ ነው:: የሃምሌው የብአዴን ጉባኤ  የተበላ እቁብ እየሆነ ነው፣አንዳች ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር የእነ በረከት ቡድን ሃምሌ ላይ አሸንፎ ሊወጣ አይችልም:: እነ በረከት ቶሎ ጡረታ ካለወጡ ወይም አርፈው ካልተቀመጡ ያልጠበቁት ነገር ሁሉ ሊገጥማቸው ይችላል:: ምናልባት  ትግራይ ስለመሸጉ ሴራቸው የማይታወቅ መስሎአቸው ከሆነ፣ የተሳሳቱ ይመስለኛል::በዚህ አጋጣሚ ትግሉ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ የሚመስላችሁም ሰዎች እንደገና አስቡበት:: እነዚህ ሰዎች እጅ እስኪሰጡ ድረስ እጅን ሰብስቦ መቀመጥ አይገባም:: የታጠፈ እጅ ካገኙ ዜሮ እድልም ይዘው ሊነሱ ይችላሉ::
በረከት እና ስብሐት ከማንኛውም ወያኔ ከሚሰራቸው የተለያዩ ሴራዎች ጀርባ በቀጥታ እና በዋነኝነት እጃቸው እንዳለብት ይታውቃል ስለዚህ የዚህን እጅግ አደገኛ ፍጡሮች እንቅስቃሴ ዱካ በትኩረት መክታተል አስፈላጊ ነዉ።ከህይወት ልምዳቸው እንኳ ብንነሳ ተንኮል ሴራ ክፋት መግደል ማስገደል ማጋጨት ማፋጀት ብቻ ስለሆነ አሁን በዝረራ ሊወድቁ የመጨረሻው ደቂቃ ሁነውም በፍፁም እንደማያርፉ ታውቆ ከፍተኛ ጥንቃቂ ያስፈልጋል ።
ቅዳሜ  ለእነበረከት ግልጽ መልእክት የሚተላለፍበት ቀን እንደሚሆን እጠብቃለሁ ::
Filed in: Amharic