>
5:13 pm - Friday April 19, 0982

" የውክልና ጦርነት ተከፍቶብናል፤ ኦሮሞው ኦሮሞን እንዲገድል እየተደረገ ነው" - ኦቦ ለማ መገርሳ

” የውክልና ጦርነት ተከፍቶብናል፤
ኦሮሞው ኦሮሞን እንዲገድል እየተደረገ ነው”
ኦቦ ለማ መገርሳ

ኦቦ ለማ መገርሳ ዛሬ ለጨፌ ኦሮሚያ(ለኦሮሚያ ምክር ቤት )ከአንድ ሰዓት በላይ ካደረጉት ንግግር መሀል ስለፀጥታ ከተናሩት የተወሰነ ነገር ላቅርብካችሁ…

(ትርጉም:- በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)

1- ከዚህ በፊት ቀጥታ ሲዋጉን የነበሩ አካላት ዛሬ እስፓንሰር በመሆንና ገንዘባቸውን በመርጨት የክልሉት ፀጥታ ለመደፍረስ ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ከእስፓንሰሮቹ የሚሰጣቸውን ገንዘብ በመቀበል የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ዝግጁ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የእኛው ወንድሞች በመከላችን ይገኛሉ ብለዋል፡፡

2- ለዚህ ህዝብ እንሰራለን የምንል ከሆነ ሁላችንም ወደሀገር ተመልሰን በሀሳብ በመፋለም አንድ ላይ መስራት አለብን ብለን ጥሪ አድርገን ጥሪ ብቻ ሳይሆን ህዝባችንን አምነን ከሰሩት ወንጀልም ነፃ እንዲሆኑ አደረግን ..የፓለቲካ ታርጋ ተለጥፎባቸው በሰው ሀገር የተበተኑ ወገኖቻችን ተመልሰው ለሀገር እንዲሰሩ በራፉን ከፍተን እያለን… በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በፈታንበት ወቅት…የፓለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ ባለበት እና ብዙዎችም ያንን ጥሪ ተቀብለው እየገቡ ባሉበት ጊዜ … ….አይ የኦሮሞ ነፃነትን ለማስከበር ትክክለኛ የጦርነት መክፈቻው ጊዜ አሁን ነው ብሎ የኦሮሞ ህዝብ ስም የሚደረግ እንቅስቃሴ ትርጉሙ ምን እንደሆነ እኔ በግሌ አልገባኝም….ለኦሮሞ ነፃነት ለማስከበር የሚያስቡ ከሆነ እስከዛሬ ይሄን ሁሉ ዘመን የት ነበሩ…. ልጅ ፊት አባት ገድለው ሬሳውን አቃጥለዋል..በዚህ አይነት ሁኔታ ሬሳ በማቃጠል የህዝብ ነፃነት እንዴት መከበር እንደሚችል አላውቅም…? ኦሮሞ ኦሮሞን ነው እየገደለው ያለው…በምዕራብ ኦሮሚያ እየሆነ ያለው ነገር ይሄ ነው፡፡

3- ቄሮ የከፈለው መስዋዕትነት እና ለዓመታት የከፈለው ትግል ይሄንን አሁን እያየነው ያለነው ለውጥ እንዲመጣ ዋና መሪ ሆኖ ታግሎል ዛሬ መጣውን ውጤትም እንድንጎናፀፍ አድርጎል.. ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በቄሮ ስም ለመነገድ የሚሞክሩ ወጣቶች እዚህም እዛም በመዝረፍና አንዳንድ አካባዎችን በማወክ አዝማሚያ እያሳዩ ነው…. ቄሮዎች ግን ይሄ በታሪክ ማህደር ላይ የተከተበ የጀግንነትና ለህዝብ መስዋዕትነት የከፈሉት ደማቸው ባክኖ እንዲቀርባቸው ስለማይፈልጉ አሁንም እነዚህን ቅጥረኞች አደብ በማስገዛት እና ወደመስመር በማስገባ ትልቅና ምሳሌ የሚሆን ስራ በመስራ ላይ ይገኛሉ…ህዝባችንነም እንደዛው ….ይሄም በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮና ተስፋፍቶ መተግበር አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡

4- አንድ ቀን ታሪክ በትክክል ይሄንን ይመሰክራል ብዬ አምናለው.. አሁን እኔ እንደማምነው ..በክልላችን መዋቅር ውስጥ እንደኦሮሚያ ፖሊስ ለህዝቡ ዋልታና መከታ የሆነ አካል አኔ በግሌ አላውቅም፡፡በዛ በጭንቀትና በመከራ ወቅት ከጎናችን ቆሞ አይዞችሁ ሚለን ባጣንበት ጊዜ ደሙን እያዛራ እና ህይወቱን እየሰጠ ከህዝቡ ጎን ቆሞ ለዚህ ለዛሬው ቀን እንደንደርስ የሚችለውን ሁሉ ያደረገ የህዝብ አካል ነው፡፡የኦሮሚያ ፓሊሶች ለሚከፈላቸው ደሞዝ አየይደለም ፋቲኩን የለበሱት፡፡

እንደኦሮሚየ ፓሊስ በቁርጠኝነት የህዝብ የቆመ አላውቅም..ቁርስ በልቶ ምሳ ሳይደግም ፀሀይና ንፋስ ውስጥ መካራውና በማየት ከገዛ ስንቁ ለህዝቡ እየቀነሰ ሲሰቃይ የነበረ የህዝብ ወገን ነው..ለህዝባቸው ሲሉ ቤተሰባቸው በትነው በየቆላውና በየድንበሩ ስንቶቹ ህይወታቸውን አጥተዋል…. ታዲያ እንዲት ዛሬ በዚህ ጊዜ በኦሮሚያ ፓሊስ ላይ ልክ እንደህዝብ ጠላት ቦንብ ይጣልበታል…?እንዴት ዛሬም ይገደላል……?ምን ተፈልጎ ነውአሁን አንዳችን በላችን ላይ ቂም እንድናወጣታ ጥሪ እየተደረገ ነው….ኦሮሚያ ውስጥ አናርኪ ለመፍጠር ገንዘብ በመርጨት የሚሰራው ስራ አለ… እንስራለን ብለን ያቀድነውን ስራ ትተን ሌላውን ስራ እድንሰራ ነው እየተፈለገ ያለው …ዛሬም ቄሮዋች ችግር ውስጥም ቢሆን ከጎናችን ሆኖ እየታገሉ ናቸው ፡፡

5- አሁን የኦሮሞ ነፃ አውጪ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል አሁንም ቢያስቡበት እና ወደትክክለኛው መንገድ ቢመለስ መንገዱ ክፍት ነው …ይሄን ምንለው ለመንግስት ጉዳዩን መቆጣጠር ከባድ ሆኖበት አይደለም..የህዝንና የሀገሪቱን ፀጥታ ማስፈን የህግን የበላይነት ማስከበር የመንግስት ዋና ስራና ኃላፊነቱ ነው ግን ይሄን ለማድረግ በምንጠቀመው ኃይል ወደማንፈልገው መንገድ እንዳንገባ ነገሮች በሰላም እልባት ቢያገኙ ጥሩ ነው ብል ስለምናምን ነው፡፡

6- ጭቆና መሸከም አንችልም ብለን ታግለንና መስዋእትነት ከፍለን ወደ ነጻነት መንገድ መሸጋገር ጀምረናል..ዛሬስ ነፃነትንም መሸከም የማንችል ህዝቦች ነን እንዴ..?

መስዋእትነት ከፍለን ወደ ነጻነት መንገድ መሸጋገር ጀምረናል..ዛሬስ ነፃነትንም መሸከም የማንችል ህዝቦች ነን እንዴ..?
Filed in: Amharic