>

የኢፈርት ሀብት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት እንጅ የትግራውያን ወይም የህውሃት ብቻ አይደለም!!!  (ቬሮኒካ መላኩ)

የኢፈርት ሀብት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት እንጅ የትግራውያን ወይም የህውሃት ብቻ አይደለም!!! 
ቬሮኒካ መላኩ
ህውሃቶች የመቶ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት  በሆነው የኢፈርት  ሀብት ላይ አዳራሽ ዘግተው ” የእኔን ።የአንተ አይደለም ” እየተባባሉ እየተጨቃጨቁ ነው ።
ይባስ ብሎ አቦይ ስብሃት ነጋ  ዛሬ ስብሰባቸው ላይ ”  በመቶ ሚልዮን የሚቆጠር ሃብት ኣለኝ። እሱንም ለልጆቼ ኣወርሳቸዋለው። ትእምት የህወሓት ነው። የትግራይ ህዝብ ኣምስት ሳንቲም ድርሻ የለውም።” ማለቱን ሰምተናል።
ከላይ እንደጠቀስኩት የኢፈርት ሀብት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት እንጅ የትግራውያን ወይም የህውሃት ብቻ አይደለም ። ዛሬ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ሀብት ያፈራው ኢፈርትን እንደ እርሾ ሆኖ ያስጀመረው ከሚከተሉት ምንጮች የተገኘ ገንዘብ  ነው።
1~ በ 1969 አም አካባቢ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አክሱም ቅርንጫፍ ሀየሎም አርአያ በመራው ኦፕሬሽን ባንኩን በመስበር ገንዘቡን በመዝረፍ  በተገኘ ብር ።
2~ በ1977 እንግሊዛዊው ቦብ ጊልዶፍና ቦኖ ባሰባሰቡት ለድርቅ ተጎጅ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን የተላከን በሚሊዮን የሚቆጠር ኩንታል ስንዴና ዘይት ለተረጅዎቹ ሳይደርስ ሱዳን በመሸጥ በተገኘ ዶላር ።
3~ ህውሃት ከ1980 በኋላ ወደ መሀል አገር ሲገሰግስ ከአማራ ፣ ከኦሮሚያ ፣ከደቡብ እና ከመላው ኢትዮጵያ እየነቀለ ከወሰዳቸው ጀነሬተሮች ፣ ፋብሪካዎች ፣ተሽከርካሪዎች እና ከባንክ የተዘረፉ ብሮች በተገኘ ቁሳዊ ሀብትና ገንዘብ
4~  ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ካለምንም ኮላተራል ተወስዶ በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ ” የተበላሸ ብድር ” በማለት በተሰረዘ ብድር ከተገኘ ገንዘብ  የተቋቋመ በመሆኑ ።
 በአጠቃላይ ኢፈርት ከውልደቱ ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ተወልዶ የወፈረ ድርጅት  በመሆኑ የኢፈርትን እጣ ፋንታ መወሰን ያለበት ህውሃት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብም በመሆኑ ፌደራል መንግስት ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወክሎ ንብረቱን ያስመልስለት ዘንድ እርምጃ ቢጀምር ጥሩ ይሆናል።
Filed in: Amharic