>

በትግራይ ቲቪ በህዝብ ስም የለየለት የጦርነት ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው!!! (በብሩክ አበጋዝ)

በትግራይ ቲቪ በህዝብ ስም የለየለት የጦርነት ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው!!!
በብሩክ አበጋዝ
*በዚህ ሰዓት ህገ-መንግስት የሚባል የለም። (የህዝብ አሰተያየት)
* ዶ/ር አብይ አህመድ ከኢፌድሪ የመጡ ናቸው ብየ አላምንም። (የህዝብ አስተያየት)
*ሃገሪቷ ወዳልተለየለት ጦርነትና ትርምስ ገብታለች (የህዝብ አስተያየት) 
*ዶ/ር አብይ በ3 ወር ውስጥ ምንም የሰሩት ስራ የለም(የህዝብ አስተያየት) 
* ዶ/ር አብይ በዚህ ሰዓት በትግራይ ህዝብ ላይ እሳት እየለኮሰ ይገኛል(የህዝብ አስተያየት)
.
የደርግ ትራፊዎች፣ የፋሽሽት አባላት(ጃዋርና ግ 7) ሰብስበክ ሀጋሪቷን በሰላም መምራት አይቻልም። ዶሩ በአፍ የትግራይ ህዝብ እንቁና ወርቅ ናችሁ ይለናል በተግባር ግን የለየለት የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው(የህዝብ አስተያየት) የዶ/ር አብይ አካሄድ ሃገሪቷ ላይ እሳት የሚያቀጣጥል ነው ልናስቆመው ይገባል።
.
ትግራይን ሳትይዝ ኢትዮጵያን መገንባት አይቻልም። (ኢንጅነር ግደይ ዘርዓፅዮን)።
 ንፁህ የትግራይ ልጆች ጣና በለስ ተሰውተው እሱ አሁንም ስለ ውሸት አንድነት ይሰብካል
(የህዝብ አስተያየት)
 በንፁሃን የትግራይ ወንድሞቻችን የተፈፀመው ግድያን ተከትሎ ህወሃት ያደረገው ደማቅ አቀባበል ምስጋና ይገባዋል(የህዝብ አስተያየት) ምፅ ብያለሁ።
.
በሌሎች ክልሎች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች መንግስት ከለላ ሊያደረግላቸውና ለተሰዉቱም ካሳ ሊከፈላቸው ይገባል(የህዝብ አስተያየት) የዋጃዎቹንስ ያጠቃልል ይሆን ብየ ጠየቅኩኝ። ዶ/ር ስመኘው በአሸባሪዎች ተሰውቶ አሁንም ሃገር ለሃገር እየዞረ ይጎበኛል(ህዝብ አስተያየት)። ከጉብኝታቸው እንደተመለሱ የመሃንዲሳችን ገዳዮች ይፋ ካላደረጉ በጠቅላይ ሚንስተርነታቸው የመቀጠል ዕጣ ፈንታቸው አስቸጋሪ ደርገዋል(የህዝብ አስተያየት)።
.
የውስጥና የውጭ ሃይሎች ንፁሃን ትግራዮችን በመግደል ትግራይን ማንበርከክ አይቻልም(የዓዲግራት ከንቲባ)። ትግራይ ትንሽቷ እስራኤል ነች እንደ እስራኤላውያን ልጆቿን ከጠላት ትጠብቃለች(አባይ ፀሃየ)። ትግራይን ያላሳተፈ ኢትዮጵያዊነት መገንባት አይቻልም(የስሃሪ ሳምረ ከንቲባ)። ለ27 ዓመታት የገነባነውን ፍቅር፣ አንድነት፣ አብሮ የመኖር እሴቶቻችን እያፈረሱት ይገኛሉ(አባይ ፀሃየ)። ለ27 ዓመታት የህዝቦችን እኩልነትና መብት ያስከበረ ህገ መንስት እየጣሱት ይገኛሉ(ኢንጂነር ግደይ ዘርዓፅዮን)።
.
የትግራይ፣ የኤርትራና የኣፋር የውይይት መድረክ ጉዳይ በአስቸኳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል(ኢንጅነር ግደይ)። ትግራይን ሳታሳትፍ ኢትዮጵያዊነት ብትሰብክ ታጥቦ ጭቃ መሆኑን ሊረዱት ይገባል( አዳነች)። በኢትዮፕጵያችን ፀረ-ሰላም ሃይሎች ተበራክተዋል(ስሙን መያዝ አልቻልኩም)። የትግራይ ህዝብ ልጁን ገብሮ ያመጣው ነፃነት ትግራይን ሳታሳትፍ ኢትዮጵያዊነት ብትሰብክ መሰረተ የሌለው መሆኑ ሊረዱት ይገባል(ከተሳታፊዎቹ)።
አካሄዱ ህወሃትና ዓረነ በታትኖ የራሱ ድርጅት ለማቋቋም የቀረው ግዜ አጭር ይመስላል(ተሳታፊዎቹ)። ማህበራዊ ሚድያ ቀዳዳ እንዲፈጥሩብን አድርገዋል(ኢንጅር ግደይ) ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ ሲታሰሩና ሲገደሉ የነበሩ ህዝባችን በ27 ኣመት እፎይታ ያገኙትን ሊቀለብሱት ይፈልጋሉ(ተሳታፊዎቹ)።
.
የታሰሩት እንፍታና ከህዝባችን እንታረቅ ያልናቸው እኛ ነበርን(ጌታቸው ረዳ)። ትግራይን አግልለው ሃገሪቷን እንደፈለጉ ሲዘውሯት ይውላሉ(ተሳታፊዎቹ) ይህ ሁሉ ችግር የተፈጠረው ተሳትፎአችን የትግራይን ወጣት ላሳተፈ ስለነበር ነው(ኢ/ሩ)። የፈለጉትን ብርና መሳርያ ቢኖራቸውም በጋራ ከቆምን ልናበረክካቸው እንችላለን(አባይ ፀሃየ)። የራሳችን ስትራተጂካዊ ትግል ስርዓት/ስልት ዘርግተን ካልተንቀሳቀስን መደናበራችን አይቀሬ ነው(ተሳታፊዎች)።
.
ትግራይ እንዲጠላ፣ በትግራዋይነቱ እንዳይኮራ የክፋት ሴራ ተሰርቶበታል-የትግራይ ወጣቶች ሊደራጁ ይገባል (ከተሳታፊዎቹ)። ትግራይ የኢትዮጵያ መወለጃ መሆንዋን ሊቀበሉት ይገባል(አብርሃ ደስታ)። ኢትዮጵያን ለማዳን ትግራይን ማዳን አለባቸው(አብርሃ ደስታ)። ትግራይ የኢትዮጵያ መወለጃ ከሆነች፣ ኢትዮጵያም ትግራይን የማጥቃት ዓላማ ካላት፣ ችግሩ ያለው ከኢትዮጵያ ነው ማለት ነው-ደማቅ ጭብጨባ( አብርሃ ደስታ)።
.
በሰም ብቻ የምናውቃቻው ጀግኖቻችን፣ የትግራይ ምሁራኖቻችን እንድንሰባሰብ ምክንያት ሆነዋል(ሁሉም ተሳታፊዎች በሚባል መልኩ)። በዚህ ሰዓት ትግራዮች እየተሰባሰብን እየታደስን እንገኛለን(አብዝሃኞቹ ተሳታፊዎች)። በዚህ ሰዓት የሚያሳስበን የትግራይ ህዝብና ህዝብ ብቻ ነው፣ በተጠንቀቅ ልንቆምለት ገይባል(አብርሃ ደስታ)።
.
እነዚህ ጥቂቶቹ ብቻ የዘረዘርኳቸው ነጥቦች ከህዝብ የተሰጡ አስተያየቶች፣ ደብረ ፅዮን የሚመራው የህወሃት ቲም አባላት፣ ልሂቃን ነን ባዮች፣ ድሮ ታጋዮች፣ በውስጥና በውጭ ሃገር የሚገኙ የትግራይ ምሁራን ነን ባዮች፣ ፖለቲከኞች መቀሌ ላይ ተገናኝተው ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ እኔን ያስገረመኝ የዶር ደብረ ፅዮን ቲም ያነሱት ነጥቦች ሳይሆን በትግራይ ህዝብ ስለተነሱት ሃሳቦች ናቸው የትግራይን ህዝብ ምን ያክል እየበረዙት እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ እነሱማ ሁሌም ልማዳቸው ነው፡፡ ከሁሉም በላያ ያሰገረሙኝ ደግሞ የኣረና ሊቀ መንበረ አብርሃ ደስታ ያነሳት ነጥብ ተንተርሶ አንድ ተሳታፊ ያነሳትን ነጥብ ነች አብርሃ እንዲህ አለ ‘’ትግራይ የኢትዮጵያ መወለጃ መሆንዋን ሊቀበሉት ይገባል’’ ተሳታፊውይሄንን ተንተርሶ ‘’ትግራይ ብቻ አይደለም ሌላኛዋ ትግራይስ ማለቴ ኤርትራንስ?? ያኔ ትግራይና ኤርትራ እኮ አንድ ነበሩ ስለዚህ በአንድ ተጠቃለው ሊጠሩ ይገባል’’ ሲል ገለፀ ከተሳታፊዎቹ ደማቅ ጭብጨባ ተቸረው፡፡ አንድ አንዶቹ ነጥቦች እጅግ ሴንሲቲቭ ከመሆናቸው የተነሳ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እኛንም ወደ ገደል እንዳይከቱን ሊንጠነቀቅባቸው ይገባል፡፡ ሰዎቹም ለሃገሪቷም ህልውናም አስጊ ሊሆኑ ይችላሉና እንቅስቃሴያቸው ቅርብ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል፡፡
Filed in: Amharic