>

መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ በቁጥጥር ሥር መዋለ!! (ዘመድኩን በቀለ)

መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ በቁጥጥር ሥር መዋለ!!
ዘመድኩን በቀለ
ጃዋርንና ቲሙን የመሰለ ፀረ ለውጥ ኃይል አስቀምጠህ፣ ለእነ ጂጂ ኪያ ጠባቂ ፖሊስ መድበህ፣ እነ መሪጌታ ብርሃኑንና መሰሎቹን ታስር ዘንድ ” የመደመር ” ካልኩሌለተሩ ያዛል። ግድ ነው
*  ” ናፍቆት ” በሚል መሪ ቃል የግንቦት 7 መሪዎች ወደ ሀገር ቤት በሚመለሱ ጊዜ በዋና አስተባባሪነት ሠርቶ አዲስአበባን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላም ያጥለቀለቀ ጀግና ነው። [ ያኔ ነው ጥርስ የተነከሰበት ] ።
~  አያጅቦ ሳያመሃኝ መብላት ጀምሯል ማለት ነው።
~ ብርሃኑን ወንጀለኛ የሚያሰኘውና ለእስርም የሚዳርገው ተብሎ ከሚገመቱት ” ወንጀሎቹ ” መካከል በዋነኝነት፦ ልጁ
፩፥ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መውደዱ፣
፪፥ ኢትዮጵያዊ መሆኑ፣
፫፥ እሱ ባይፈልገውም ዐማራ መሆኑ፣
፬፥ ላመነበት ነገር እስከሞት የታመነ መሆኑና፥
፭፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንቅቅ ያለ መሪጌታ መሆኑ ናቸው መሪጌታውን የሚያስስሩት። ። 
መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ እነ ጠ/ሚ/ዶኮ ዐብይ አህመድ ይዘው የመጡትን የመደመር ቀመር ሳያላምጥ የዋጠ ሰው ነው። ” ናፍቆት ” በሚል መሪ ቃል የግንቦት 7 መሪዎች ወደ ሀገር ቤት በሚመለሱ ጊዜ በዋና አስተባባሪነት ሠርቶ አዲስአበባን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላም ያጥለቀለቀ ጀግና ነው። [ ያኔ ነው ጥርስ የተነከሰበት ] ።
መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ ከለውጡ በኋላ ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ የተያዘ፣ ቤቱና ንብረቱም የተበረበረ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነው። ብርሃኑ አራት ኪሎ ከመንገድ ላይ በፖሊሶች ተያዘ፣ የለበሰውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጃኬት ፖሊሶቹ እንዲያወልቅ ቢያዙትም በፍጹም አላደርገውም በማለቱ ግብግብ ተፈጥሮ እንደነበርም ተነግሯል። [ አሁን ጉዳዩ እየተገለጠ ነው ማለት ነው ] ።
መሪጌታ ብርሃኑ ከሁለት ሰዓታት የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ በኋላ በደኅነቶችና በፖሊሶች ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመምጣት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባልያዙ ፖሊሶች መኖሪያ ቤቱ ሲበረበር ውሏል። ፖሊስ ባደረገው ፍተሻም በብርሃኑ መኖሪያ ቤት ምንም ያገኘው ነገር እንደሌለና ብርሃኑም ፖሊሶችን ምን ፈልገው እንዲያ እንደሚደክሙ ደኅነቶቹን ቢጠይቅም ፖሊሶቹ  ” በቤትህ የጦር መሳሪያና ገንዘብ እንዳለና የተባለውን መሣሪያና ገንዘብ ይዘን እንድንመጣ ነው ታዘን የመጣነው፤ ነገር ግን የተባለውን ነገር አላገኘንም በማለት እንደመለሱለትና ይህንን ቃላቸውንም ፖሊሶቹ በቃለ ጉባኤያቸው ላይ አስፍረው በአይን እማኞችም ፊት ፊርማቸውን ከሶስት ምስክሮች ጋር አኑረው ብርሃኑን መልሰው ” በአዲስ መልክ ሥራ ወደጀመረው ማዕከላዊ ወኅኒ ቤት ይዘውት ሄደዋል።
በአንጻሩ በሌላ በኩል ደግሞ ሐጂ ጃዋር መሀመድና ቲሙ እንደልባቸው እየተናገሩ እንደፈለጉ ሳይጠየቁ የሚኖርባት ኢትዮጵያም ተፈጥራለች። ዘር ከዘር ሲያባሉ፣ ሲያፋጁ የነበሩት እነ ጂጂ ኪያ ጭራስ አዲሱ ” ኢትዮጵያ ሱሴ ” መንግሥታችን የፖሊስ ጥበቃ መድቦላችው በነጻነት ሲንቀሳቀሱ ሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎችን መነቅ እና ማሸማቀቅ በግልጽ መጀመሩን እያየን ነው።
እስሩ ቀጣይ ነው። ያልተደራጀ አካል ቀድሞ በተደራጀ ኃይል ይበላል። የተደራጀ ኃይል ምንጊዜም በላተኛ ነው። ሳይንሱ ይኸው ነው። ኋላ ላይ ደግሞ ” መግደል ፣ ማሰር፣ መሸነፍ ነው ” ትባልኛለህ ። አሁን ብርሃኑ ተክለያሬድን ግንቦት ሰባት ያድነው እንደሁ እስቲ እናያለን። ደግሞ እናያለን ነው ያልኩት። አቦ ማን ነበር ” የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ” የለው?  ሌኒን እንዳልሆነ ግን እርግጠኛ ነኝ።
አሁን ማን ይሙት የሚታሠር ሰው ጠፍቶ ነው ብርሃኑ ቅድሚያ የሚታሰረው ? እኔ ማንም ሰው ካጠፋ መታሰር የለበትም ባይ አይደለሁም። ነገር ግን ብርሃኑ መታሰር ካለበት እንኳ ተራው መጨረሻ ላይ ነው መሆን የነበረበት።
እነ አቦይ ፀሐዬን የመሳሰሉ አረጋዊ የሀገር አውራ አስቀምጦ እነሱን ሳያስቀድሙ አንድፍሬ ጎረምሳ ማስቀደም በእውነት ይሄ ነውር ነው። ወላጆችን፣ አረጋውያንንም ያለማክበር ነው። በእውነት ፌር አይደለም።
ታዬ ደንደአ ግን እንደዛተ አልቀረም። ይኸው የአንድነት ኃይል ነኝ ባዩን ሁሉ እየለቃቀመ በፊት እሱ የቀድሞው ሥርዓት ያሳደገበት ማዕከላዊ እሱም ጊዜ ሰጥቶት ባለ ሥልጣን ሲሆን በተራው የአይኑ ከለር ያላማረውን ሁሉ እየለቀመ ይዶልልህ ጀምሯል። ተደማሪዎች ቻሉት እንግዲህ።
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic