አዳነ አጣነው
ዛሬ አዲስ አመራር ነው ተብሎ ለህዝብ ይፋ የሆነው የህወሀት ከፍተኛ ስልጣን ያለው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ነብሰ ገዳዩ ጌታቸው አሰፋ መጠቃለሉ፣ እብሪተኛው ህወሀት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀት ያለጥርጥር ማሳያ ነው፡፡
ህወሀት የኢትዮጵያ ህዝብ ጌታቸው አሰፋን ለፍርድ ለማቅረብ በሚጥርበት በአሁኑ ሰአት በማንአለኝበት ለአመራር ማምጣቱ፣ በዋናነት ህወሀት ተመልሶ የበለይነቱን ለመያዝ የቀን ቅዠት ውስጥ መግባቱን የሚያሳይ ምልክት ከመሆን አልፎ ፣ አሁንም የ27 አመታቱ ግፍ እና በደል ሳይበቃ ተጨማሪ የከፍ ደም ለማፍሰስ ህወሀት መዘጋጀቱን የሚያሳይ እርምጃ ነው፡፡
የትግራይ ህዝብ ሆይ !
—በወያኔ ስም ተደራጅተው በአንተ ስም የሚነግዱ የመንደር ፊውዳሎች ትእቢታቸውን ይቅር ልትለው አይገባም
—ለ27 አመታት ህዝብን ገደሉ አሰሩ፣ ለራስቸው እና ለቡድናቸው ከሚገባው በላይ በለጸጉ
—-ፍትህን አጓደሉ፣ ህዝብን ከህዝብ አጣሉ
—-ኢትዮጵያዊነትን አዳከመው አያቶቻቸው ያገለገሉትን የጣልያን የዘር ስርአት መሰረቱ
— የትግራይን ህዝብ የግል ንበረት አድርገው በአንተ ስም ለጦርነት እየተዘጋጁ ነው
—ህወሀት የመንደር የፊውዳል ጥርቅም እንጂ ለትግራይ ህዝብ ያልቆመ መሆኑን የትግራይ ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አሁን ልትረዳው ይገባል
—የሀገርን ሰራዊትን ወደ ግል ሰራዊት ተቑም ቀየሩ፣ የሀገር ኢኮነሚን ተቖጣጠሩ፣ ከነሱ በላይ ሌላ ሰው የለም ሲሉ ለፈፉ፡፡
–ጦርነትን የመፍጠር ፣ ተዋጊነትን እና የጦር ስልትን ጥበብ ከኛ ወዲያ ላሳር ሲሉ ደነፉ!
የትግራይ ህዝብ ሆይ !
ደግመህ ደጋግመህ የነስብሀት ነጋን እኩይ አላማ ልትመረምረው ይገባል፡፡ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ለስንት አመታት በናንተ ስም በመጡ ጎሰኞ የመንደር ፊውዳሎች ሊረገጥ ይገባል ትላለህ?፡፡
የትግራይ ህዝብ ወያኔዎችን በቃችሁ የምትልበት ሰአት አሁን ነው፡፡ ነገ አይደለም !፡፡ አሁንኑ አደብ እንዲገዙ ካላደርክ፣ በባዶ በትግራይ ህዝብ ክብር ስም እየጮኹ አጉል ጀብዱ ለመፈጸም ተዘጋጅተዋል፡፡ እነሱ ጠፍተው አንተንም ይዘው ሊጠፉ በብርቱ መክረዋል !! አደጋው ከፊትህ ተደቅኗል ! ልታየው ይገባል!
እውነታው፡- እነ እነስብሀት ነጋ ዘርፈው ያከማቹት ንበረት እና የጦር መሳሪያ ከጊዜ’ዊ ደረት ከማሳበጥ ውጭ በቑሚነት የኢትዮጵያን ህዝብ በውጊያ አሸንፎ በቕሚነት ሊቀጥል
እንደማይችል ከቶም ቢሆን መገንዘቡ ተገቢ ነው፡፡ ጦርነት እየመጣች ነው !! ጦርነት ዞሮ ዞሮ ጫሪውን ታጠፋለች !!
ህወሀት ጦር ለመስበቅ ለመዘጋጀቷ ሌላው ማሳያ:-
የማከብረው ጋዜጠኛ ህወሀት “የጦር ቁሳቁሶች ማከማቻ እና ከአደጋ መከላከል” የሚችል “የጦር ዋሻ” መገንባታቸውን በተመለከተ ያገኘውን መረጃ ለህዝብ አካፍሏል፡፡
ከዚህ በታች ያለው መረጃ በዋሻው ዙሪያ ክትትሉን አስፍቶ ማየት ይችል ዘንድ እንዲረዳው በማሰብ አንዳድ ሰዎች የጦር ዋሻውን በሚመለከት ያላቸውን መረጃ ለማካፍል ያክል የቀረበ ነው፡፡
አንዳድ ሰዎች ስለ የጦር-ዋሻው አለን የሚሉት መረጃ፡-
—የጦር ዋሻው የተሰራው በሽሬ አውራጃ አድ-ዳሮ በሚባል አካባቢ የሚገኝ ተራራ ስርን በመሰርሰር ነው
–ይህ ዋሻ የጦር ተሽከርካሪዎችን ታንክን፣ መድፍን እና ከፍተኛ ተወንጫፊ መሳሪያዎችን ከአደጋ ይከላከላል
–እኒህ እንውቃለን የሚሉ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የጦር አውሮፕላን ጨምሮ ዋሻው መጠለል ይችላል ይላሉ
—ዋሻው የታቀደው እና የተሰራው ከኤርትራ ጝጭት በኻላ ነው
—በዚህ የጦር ዋሻ በጣም ጠቃሚ የሆኑ የጦር መሳሮያዎች ከመሀል አገር የተወሰዱ እና የተገዙ አዳዲስ መሳሪያዎች መደበቂያ ነው
—ወያኔ ልምዱን ያገኘው ሳሀል ሻእብያ ከቆፈረው የጦር ዋሻ ነው ይላሉ
–ዋሻው ለብዙ ጊዜ ሊያገለግል የሚችል የምግብ ክምችት አሉበት
–ውሀ እና 24 ኤለትሪክ የሚሰጥ ጀኔሬተር በዋሻው ውስጥ እንደሚገኝ ..ያትታሉ
አንድ ህዝብ አንድ አገር !!