>
5:13 pm - Saturday April 18, 2578

ብሔርተኛ ሁሉ ጠላት ያለው ሲሆን መጨረሻው ደግሞ ውድቀት ነው!  (ስዩም ተሾመ)

ብሔርተኛ ሁሉ ጠላት ያለው ሲሆን መጨረሻው ደግሞ ውድቀት ነው! 
ስዩም ተሾመ
እንደ ኦነግ የ50 አመት ሽማግሌ ሆንክ እንደ አብን የ1 አመት ጨቅላ አክራሪ ብሔርተኛ እስከሆንክ ድረስ ከጥፋት በስተቀር መልካም አስተዋፅዖ ማበርከት አትችልም፡፡ ምክንያቱም ብሔርተኛ ስትሆን ጠላት ያስፈልገሃል፡፡ 
—-
አክራሪ ብሔርተኝነት በቁንፅል እሳቤ፣ ራስ ወዳድነትና ወገንተኝነት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ አመለካከት ነው፡፡ ኢትዮጲያው ስስጥ የብሔርተኝነት ትልቁ ግቡ #ህወሓትን መሆን ነው፡፡ ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አንቅሮ የተተፋ ቡድን ነው፡፡ አክራሪ የብሔርተኝነት አጀንዳ የሚያራምዱ የፖለቲካ ቡድኖች መጨረሻቸው ልክ እንደ ህወሓት ውርደትና ሽንፈት መከናነብ ነው፡፡
እንደ ኦነግ የ50 አመት ሽማግሌ ሆንክ እንደ አብን የ1 አመት ጨቅላ አክራሪ ብሔርተኛ እስከሆንክ ድረስ ከጥፋት በስተቀር መልካም አስተዋፅዖ ማበርከት አትችልም፡፡ ምክንያቱም ብሔርተኛ ስትሆን ጠላት ያስፈልገሃል፡፡ የምትጠላው ወገን ደግሞ አንተ በጠላህው ልክ ይጠላሃል፡፡ በብሔርተኞች ዘንድ የአንተ ስኬት ለሌላው ውድቀት ስለሆነ በእያንዳንዷ ደረጃ (Step) እንቅፋት ያበጅልሃል፡፡ ምንአልባት እንደ ህወሓት በአፈ-ጮሌነትና አጋጣሚ ቢሳካልህ እንኳን ብዙሃኑ ትክክለኛ ማንነትህን ያወቀ ዕለት መቃብርህን አርቆ ይምስልሃል፡፡ ከዚያ ምን እንዳጠፋህ እንኳን ሳይነግርህ ሊቀብርህ ይጣደፋል፡፡
ምክንያቱም አብሮህ እያለ “ልዩ ነኝ” ያልከው ሰው “ልዩ” መሆንህን የነገርከው የጋራ የሆነ ነገር ስላላችሁ እንደሆነ ዘንግተህዋል፡፡ የጋራ የሆነ ነገር የሌላቸው ሲጀመር መነጋገር አያስፈልጋቸውም፡፡ በአብሮነት እየኖረ፣ ስለ ጋራ ጉዳይ እየተናገረ፣ የራሱን ጥቅምና ተጠቃሚነት የሚያስቀድም ሰው ደግሞ ራስ-ወዳድ ነው፡፡
 እንዲህ ያለ ሰው ለራሱ ያደላል፣ ለራሱ ሲያደላ ደግሞ ሌሎችን ይበድላል፡፡ የተበደለ ደግሞ በዳይን በዚያው ልክ ይጠላል፡፡ በአጠቃላይ ብሔርተኛ ለራሱ ጥሩ ቢመስለውም በሌሎች ዘንድ እንደ ጠላት የሚታይ ነው፡፡ ለጠላት ደግሞ ሁሉም ሰው ጠላት ነው፡
Filed in: Amharic