>

ከአፍሪካ በዘረኝነት (በህግ አልባነት) ቀዳሚው አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ (በዛዊት ዳኛቸው)

ከአፍሪካ በዘረኝነት (በህግ አልባነት) ቀዳሚው አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በዛዊት ዳኛቸው 
በቅርቡ ካለሽፍቱ ስራ ገብቶ እና አጭበርብሮ *ለትግራይ ልማት ማህበር ስብሰባ ነው የምሄደው* ያለን ከምርጦቹ ዘር የሆነን ግለሰብ በነጻ ወደ መቀሌ ያሳፈረን ሰራተኛ ከስራ በተሰናበተ በሳምንቱ ተወልደ ከፍተኛ ተግሳጽ እና ቅጣት ባባረሩት የስራ ክፍል ሀላፊዎች ላይ በማድረስ ወደስራው ተመልሷል።
 ከዚህ በፊት በማህበራዊ ሚድያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስር ቤት እንዳለው ይፋ የወጣበትን ጽሁፍ ሳነብ እኔም ከዚህም በላይ በዘረኝነት እና ኢፍታሀዊነት እንደተዘፈቀ የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀው ዘንድ እንሆ ብያለሁ።
ከአየር መንገዱ (የኢትዮጵያ የሚለውን የክብር ስም ከፊቱ ለማድረግ እቸገራለሁ) ለአመታት ካገለገልኩ በኋላ ምክንያቱን ባላወኩት ሁኔታ ከስራ እባረራለሁ። እኔም ይህንኑ በመቃወም ክስ ፍ/ቤት መስርቼ ለሁለት አመታት እስከ ሰበር ችሎት ከተከራከርኩ እና ከፍተኛ አንግልት ከደረሰብኝ በኋላ  ወደስራ ገበታዬ እንድመለስ ውሳኔ አገኘሁ። ከዚህ በኋላ ነው ታሪኩ የሚጀምረው ።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔው መሰረት ወደ ስራ እንድመለስ ትእዛዝ መስጠቱን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ስራዬ መመለስ እንደማልችል እና በምክንያትነትም ለሀገር ደህንነት የማሰጋ በመሆኑ ወደስራ ለመግባት የሚያስችል የይለፍ መታወቂያ (security pass) የኤርፖርት ደህንነት ቢሮ እንደማይሰጠኝ አሳውቆናል የሚል ደብዳቤ ለፍርድ ቤቱ ያቀርባል። ፍርድ ቤቱም ከደህንነት መስሪያ ቤቱ  እና ከህግ በላይ ከሆነው አየር መንገድ ጋር በመወገን ለአመታት የተንከራተትኩበት መብቴ ላይ ውሀ በመቸለስ መዝገቡን ዘግቶ አሰናብቶኛል።
እኔ አልፎ አልፎ በማህበራዊ ሚዲያ ከምለቃቸው ለፖለቲካ የቀረቡ ጽሁፎች በስተቀር ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማላደርግ በመሆኑ ነገሩ በከፍተኛ ሁኔታ ህሌናዬን ስለቆረቆረው አንድ አመት የፈጀ በግሌ ጥናት አድርጌ የደረስኩበት እንሆ ውጤቱ። በመጀመሪያ ደረጃ ከስራ የተሰናበትኩት በማህበራዊ ሚድያ በፃፍኩት ጽሁፎች መሆኑን በአሁኑ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ከስራ የተሰናበቱ የአየር መንገዱ የ SECURITY ክፍል የቀድሞ ባልደረቦች አረጋግጠውልኛል። እነዚህ ሰዎች በማስረጃ አስደግፈው እንዳብራሩልኝ በአየር መንደጉ SECURITY ክፍል የሰራተኞቹን የማህበራዊ ሚድያ እንቅስቃሴ የሚከታተል (MONITOR) የሚያደርግ እና በተወልደ የሚመራ ግብረሀይል ከ Zone 9 ክስተት በኋላ ተቋቁሞ እንደነበረ (የዞን ዘጠኝ አንዱ አባል ማለትም አቤል ዋበላ የአየር መንገዱ ሰራተኛ የነበረ በመሆኑ)  እና በዚህ ግብረሀይል አማካኝነት  ማንኛውም በማህበራዊ ሚዲያ የመንግስትን ስም በመጥፎ የሚያነሳ ወይም እንደ ጃዋር እና ኢሳት የመሳሰሉትን የሚከታተል(Like ያደረገ) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲባረር መመሪያ ወርዶ የነበረ በመሆኑ እና በዚህ መሰረትም እኔን ጨምሮ ከ 30 ያላነሱ ሰራተኞች የተለያየ ምክንያት እየተለጠፈባቸው መባረራቸውን ለማወቅ ችያለሁ።
በዚህ ህገወጥ ግብረሀይል ሰራተኞች እንዲባረሩ ከተደረጉ በኋላ እንደ እኔ ደፍሮ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት አቅርቦ ውሳኔ የሚያገኝ ካለ ደግሞ ተወልደ ለፍትህ እና ለህግ ካለው ንቀት የተነሳ 25 ኪሎግራም ወርቅ በመስረቅ ተጠርጥሮ  ነገርግን እንደሌሎች ተጠርጣሪዎች ክስ ሳይቀርብበት በጡረታ እንዲገለል ከተደረገው የቀድሞው የአየር መንገዱ SECURITY ክፍል ሀላፊ ከነበረው አቶ ብርሀነ መልካ በትግል ስሙ ወዲ ራያ ( በነገራችን ላይ ይህ ሰው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሀላፊ የነበረ እና በሌብነት እና ጉቦ ተገምግሞ ከተሰናበተ በኋላ በግል ከተወልደ ጋር ባለው ትውዉቅ በአየርመንገዱ የተቀጠረ ነው) ጋር በመሆን የኤርፖርት ደህንነትን በማነጋገር ፋይል ቁጥር ያልያዘ ደብዳቤ ለፍርድ ቤት security pass እንደማይሰጥ በመጻፍ ከፍተኛ የሆነ አሻጥር እንደሚፈጸም እና ፍርድ ቤቱም ይህን እያወቀ ወይም በግዴለሽነት ከ10 በላይ ሰራተኞች ጉዳይ በዚህ ሁኔታ መዝጋቱን ለማረጋገጥ ችያለሁ።( በነገራችን ላይ አሁን በዶክተር አብይ አስተዳደር የአየር መንገዱ የህውሀት አባላት ሰራተኞች ለምሳሌ ካለ ብቃቱ  manager HR customer service የሆነው እንደርታ መስፍን በአብይ አስተዳደር  ላይ ለስራ የተሰጠ ነጻ ኢንተርኔት እና ዴስክ ቶፕ በመጠቀም የሚጽፉትን የጥላቻ እና የፕሮፓጋንዳ መልእክት ሳይ አይ ይች ሀገር አብዛኛው የእንጀራ ልጅ ጥቂቱ የእናት ልጅ የሆነባት ያሰኘኛል)።
በነገራችን ላይ አየር መንገዱ የደህንነት መስሪያ ቤቱን እና  የአየር መንገዱን SECURITY ክፍል ለህገወጥ profiling መጠቀም የጀመረው ከ 2011 እ.ኤ.አ ጀምሮ (ማለትም ተወልደ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከሆነ ጊዜ) ነው። ማንኛውም የአየር መንገዱ ተቀጣሪ የጽሁፍ እና የቃለመጠይቅ ፈተና ማለፉ ከተነገረው በኋላ አይደለም በኢትዮጵያ በአለም ላይ የሌለ ሴኩሪቲ ቼክ የሚባል አሰራር ዘርግቷል። ይህም የተቀጣሪው የዘር ማንነት እና የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ የሚፈተሽበተ ሲሆን ፣ ተቀጣሪው በዚህ የግብዞች መለኪያ ካላለፈ ቅጥሩ ውድቅ ይደረጋል። በዚህ ሁኔታ ስንቶች ስራ አገኘን ካሉ በኋላ የውሀ ሽታ ሆኖባቸዋል።
በሌላ በኩል ፍርድ ቤቶች የአየር መንገዱን ጫና ተቋቁመው የተባረረ ሰራተኛ ወደስራ እንዲመለስ ከገፉበት እና ሰራተኛው የሚሰራበት ክፈል security pass የማያስፈልገው ከሆነ አየር መንገዱ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሰራተኛውን መልሻለሁ ብሎ ምሎ ከተገዘተ በኋላ በ 3ኛ ው ቀን ሰራተኛው የብሄር ማንነቱ እየተጣራ ስራውን ለመቀጠል ወደሚቸገርበት ቦታ እና የስራ መደብ ማዛወር በጣም የተለመደ ነው ። ለምሳሌ ኦሮሞ ከሆነ ወደ ሶማሌ ክልል አማራ ከሆነ ወደ ትግራይ ወይም አፋር ይመደባል። ይህ አሰራረ ያልተጻፈ ግን ያለማዛነፍ የሚተገበር መሆኑን እያንዳንዱ በፍርድ ቤት የተመለሰ ሰራተኛ ባለፉት 5 አመታት ወደ ቀድሞ የሰራ ገበታው ያልተመለሰ መሆኑን ማንም ሰው መለስተኛ ጥናት በማድረግ ማረጋገጥ ይችላል።
አየር መንገዱ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚታወቅ እና ማስቲካ በስራ ላይ አላመጥክ፣ ጸጉርህን አከክ እያለ ሰራተኛ እንደሚያባርር ይታወቃል። ነገር ግን ይህ የሚሰራው ከተወልደ ጋር አንድ አይነት ዘር የሌለህ ብቻ ከሆነ መሆኑን የሚከተሉት ማሳያዎች ፍንትው አድርገው ያረጋግጣሉ።
በቅርቡ ካለሽፍቱ ስራ ገብቶ እና አጭበርብሮ ለትግራይ ልማት ማህበር ስብሰባ ነው የምሄድ የምትል ሰው በነጻ ወደ መቀሌ ያሳፈረ ሰራተኛ ከስራ በተሰናበተ በሳምንቱ ተወልደ ከፍተኛ ተግሳጽ እና ቅጣት ባባረሩት የስራ ክፍል ሀላፊዎች ላይ በማድረስ ወደስራው ተመልሷል።
ከ 2 አመት በፊት በ ሰው ሃብት ቅጥር ክፍል የተመደበ ጀማሪ ሰራተኛ በአየር መንገዱ የጥገና ክፍል የሚሰራ ሌላ ማንነቱ ከወደ መቀሌ የሚመዘዝ ሰራተኛ ዘመዱን ለማስቀጠር በጉቦ መልክ ገንዘብ ሰጥቶኛል በማለት ለአለቃው ያሳውቃል። ብታምኑትም ባታምኑትም ይህ ሰራተኛ ከስራ ሲሰናበት ጉቦ ሰጭው በስራው ላይ ቀጥሏል።
የአክሱም ትኬት ሽያጭ ቢሮ ሰራተኛ የነበረ እና ከስልጠና ጊዜ ጀምሮ ሌሎች ሰልጣኞችን በመደባደብ እውቅና ያተረፈ ከአለቆቹ አቅም በላይ በመሆኑ እና ለተከታታይ 7 ቀናት ያለ አለቃው ፍቃድ ከስራ በመቅረቱ በማባረሩ ለተወልደ አቤቱታ አቅርቦ የይስሙላ አጣሪ ኮሜቴ በማቋቋም ወደስራው ለመመለስ በሂደት ላይ እያለ የአየር መንገዱ ሰራተኞች የያዘ መኪና ላይ ከ4 ወር በፊት ቦምብ አፈንድቶ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በእስር ላይ የሚገኝ ሲሆን( አንዳንዶቹ ተፈትቶ ወደስራ ተመልሷል ይላሉ) ጉዳዩ ወደህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ አየር መንገዱ አፍኖ መያዙ ለምንድ ነው?
በአጠቃላይ አየር መንገዱ ከቅጥር ጀምሮ እስከ ማሰናበት ድረስ መለኪያው ዘር እና ኢፍታሀዊነት መሆኑን ባደረኩት ጥናት ያረጋገጥኩ ሲሆን፣ ለዚህ እንዲረዳውም ተወልደ ከተሾመበት 2011እ.ኤ.አ ጀምሮ በምንም መመዘኛ የአየር መንገዱን መስፈርት የማያሟሉ ከአድማስ ኮሌጅ እና መሰሎቹ በተመረቁ በአብዛኛው የአንድ ብሄር ተወላጆች የቅጥር ክፍሉ እንዲመራ እየተደረገ ይገኛል( ከ2012- 2014 ደሳለኝ ከ 2014 -2017 እምባየነሽ አርአያ በአሁኑ ጊዜ ገብረዮሀን ወ ገብርኤል)።
ከ 7 ወይም 8 አመት በፊት የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮች VP and CXO የሚባሉት የሚያዙት ብቃት እና ብቃትን ብቻ መሰረት አድርጎ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ግን ከ 15ቱ አመራር 7ቱ የአንድ ብሄር አባላት ( ተወልደ ፣ ፍጹም MD Cargo( የተወልደ ተተኪ)፣ ኢሳያስ VP International Services፣ ዘላለም MD MRO( እጅግ በሙያው የተከበረውን አቶ ዘመነን በearly retirement በማባረር የተተካ)፣ ሚካኤል VP Customer services፣ ተክሌ MD Ground services እና አክሊሉ  MD Catering)፣ ቴዎድሮስ (Airport enterprise)  የተሰገሰጉበት እና አንድም የኦሮሞ ብሄር የሌለበት ስብስብ ሆኗል።
የአየር መንገዱ የቦርድ አባላትም ይህን እያወቁ ተወልደን በመፍራት እንዳላዩ በመምሰል አንድም ጊዜ ከሰራተኛው ጋር ተወያይተው የማያውቁ እና በየወሩ በመሰብሰብ እያጨበጨቡ አበል የሚበሉ የቀን ጅቦች ሆነዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴም አየር መንገዱ ከህግ በላይ ይመስል በታሪኩ አንድም ጊዜ እንኳን የአየር መንገዱን የስራ አፈጻጸም ገምግሞ አያውቅም። በመሆኑም አዲሱ የአብይ አስተዳደር በአፋጣኝ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ይህን ግፍ እና ዘረኝነትን ከፍ አድርጎ የሚያበር አየር መንገድ አደብ ሊያስይዘው ይገባል።
ከዚሁ ሳንወጣ:-
“የለውጡ ሂደትን በሀሳብ በመደገፌ ብቻ አውሮፕላን እንዳላበር ታገድኩኝ”
  ፓይለት ያለው ፈንታ
 
ሌላኛው ዘርን እና አመለካከትን ያነጣጠረ – የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደል – (ልዩ ትንታኔ) በታምሩ ገዳ
Filed in: Amharic