>
5:26 pm - Monday September 17, 8323

የጨነገፈ የ40 ዓመት ትግል!!!  (በሚሊዮን አየለች)

የጨነገፈ የ40 ዓመት ትግል!!! 
በሚሊዮን አየለች
ኦነጋውያን በትግል ወቅታቸው በንጉሱ ጊዜ፤ በደርግ ወቅት፤ በኢህአዲግ ወቅት አንድ ገዤ መሬት መያዝ የተሳናቸው ነፃ መሬት በኦነግ ስም የሚተዳደር ወረዳ ያለው ቀበሌ ያለው ግብር የሚከፈልበት መሬትን ከ 40 ዓመት በላይ በፈጀባቸው የትግል ወቅት ውስጥ ያልያዙትን ነፃ መሬት ዛሬ ላይ በመልካም ፈቃድ ከበረሀው ይልቅ በሀሳብ ታገሉ ተብለው የገቡ መሆኑን እንዴት ይረሱታል፡፡
ትግል ይወለዳል ያድጋል እንዲሁም ይሞታል፡፡ በተለያዩ ዓለማት የተለያየ ችግሮችን አንግበው የተነሱ ትላልቅ አብዮቶችን ፈጥረው ማለፍ የቻሉ ተሳክቶላቸው ላመኑበት ዓላማ ደማቸውን ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ገብረው ሰክሰስ ያደረጉ እንደ ዓይከን የምንጠራቸው ታጋዮች አሉ፡፡
 በአንፃሩ ደግሞ የተነሱበት ዓላማ በማህበረሰቡ የማይደገፍ ትንሹን ችግር አግዝፎ በማየት ባልተፈጠረና ባልነበረ ታሪክ ላይ አዲስ ታሪክ ቀምረው ለሚታገሉለት ማህበረሰብ የፈጠራ ታሪክ በመከተብ የግል ፍላጎታቸውን እና የስልጣን ጥማቸውን ለማሳካት የሚታትሩ ነገር ግን ለዘመናት ቢታገሉም ለውጥ ማምጣት አቅቷቻ ፌል ያደረጉ የዓለም ታሪኮችም ዓያሌ ናቸው፡፡
በሀገራችን የንጉሱን አገዛዝ በመቀጠልም ወታደራዊ የሆነውን የደርግን አገዛዝ ተቃውመው በሀገሪቷ ውስጥ አብዮት ለመፍጠር የተንሳቀሱ የወቅቱ አብዮተኞች አያሌ ነበሩ፡፡ የያዙት ዓላማ እና ለቆሙለት ማህበረሰብ የሚጠቅም ይሁን አይሁን እዚህ ላይ ሳንተቸው ለእኩይ አላማቸውም ለተቀደሰ ዓላማቸውም ተንቀሳቅሰው የሚፈልጉትን አብዮት ያመጡ እንዳሉ ሁሉ የከሸፈባቸው ከትግሉ ጨዋታ ውጪ የሆኑትም በርካቶች ናቸው፡፡
በቀደመው የንጉሱን አገዛዝ ተቃውመው ዱር ቤቴ ድንጋይ ትራሴ ብለው ወደ በረሀ ወርደው ከመሸጉት ከዋነኞቹ መካከል ጀበሀ ይጠቀሳል ይህ ድርጅት በአብዛኛው በሰሜን በኩል ያሉትን የኤርትራን ሙስሊም ተወላጆችን በመያዝ የትጥቅ ትግል ሲጀምር ዓላማው እና ርዕዩ የንጉሱን አገዛዝ ብቻ መቃወም ሳይሆን ሙሳሊማዊ አስተዳደርን መገንባትና ካልሆነ የሙስሊም ግዛት ነው ብሎ የሚያስባቸውን ቦታዎች በመያዝ ከሱዳን ጋር መቀላቀልልን ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡ ጀብሀይ ይደገፍ የነበረው በአብዛኛው በሳውድ አረቢያ እና በመላው አረብ ሀገራት አልጄርያን ጨምሮ ስለሆነ የገንዘብ ምንጩን በገፍ ለማግኘት አይከብደውም ነበር የእንግሊዝም የቀኝ ግዛት ውል ስምምነት ደቡባዊው ባህረ ነገሻ (ኤርትራ) ወደ ሱዳን ለማካለል ደፋ ቀና ትልም ስለነበር ለጀበሀ ድጋፍ አልተለየውም ነበር ያም ሆኖ በላዩ ላይ ሌላኛው የኤርትራ ነፃ አውጪ ጦር ሻዕቢያ ሲመሰረት ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም የተዋቀረ አድርገውት ነበርና መነሻ ሀሳባቸው እና መከራከሪያ ነጥባቸውም ለ 50 ዓመት ያህል  በጣሊያን ቅኝ ግዛት ስር ስንሆን ኢትዮጵያ አይታን አታውቅም የደረሰብን በደል ከፍተኛ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ እንደ አንድ ክፍል ቆጥራ ነፃ እንድንወጣ አላደረገችንም እና ሌሎች እነሱ ለትግላቸው መሰረት ይሆናሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ሀሳቦች በመያዝ የኤርትራን ነፃ ግዛት መመስረት አለብን በማለት መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡
ህውሀት፤ኢህአዲግን የመሰረቱት ድርጅች ለእኩይ ተግባራቸውም ቢሆን ተንቀሳቅሰው በብዙ መሰዋትነት በላዩም የኢትዮጵያውያን የጦር መኮንኖች በፈጠሯቸው ስህተቶች ግባቸውን ሊመቱ የቻሉ አብዮተኞች ናቸው፡፡
በአብዮተኝነት በኩል መታገልን እና ለውጥ ማምጣትን ከግብ አድርገው የተንቀሳቀሱትም በላዩም ይህንን ሀሳባቸውን በከተማ ጀምረው ወደ በረሀ የዘለቁ እዛም ያልተሳካላቸውና ትግላቸው መክሰሙን ያመኑ እና የተበታተኑ የኢህአፓ አባላትንም እንደ አንድ ኩነት ልናነሳ እንችላለን፡፡
በመሰረቱ በትጥቅ ትግል ለመፋለም ወስኖ የትጥቅ ትግልን ዋነኛው ግቡ አድርጎ በነፍጥ ለማሸነፍ የሚፈልግ አብዮተኛ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚታይና ሀሳቡን እና ዓላማውን ሊደግፉ የሚችሉትን ማህበረሰቦች ከጎኑ ለማሰለፍ ተጨባጭ ነገር ሊያሳይ ይገባዋል ይህ ባልሆነበት በረሀ ቤቴ ድንጋይ ትራሴ ብሎ በረሀ ለበረሀ በሸምቅ ትግል ለመዋጋት ገብቶ በስሙ እንኳ አንድ ነፃ ገዤ መሬት ሳይዝ በስሩ የሚተዳረሩ ሲሆንሰፊ ግዛት ያለው ዞን አልያም ወረዳ አልሆን ደግሞ ካለው አንድ ቀበሌ እንኳ በስሙ ማስተዳደር ያልቻለን ታጋይ ትግሉ ውስጥ ነበርኩ ለበርካታ ዘመን ቢለን ትግሎ በረሀ ተወልዶ በረሀ አድጎ በረሀ የሞተ ትግል ነው፡፡ ያ ማለት የሚያምነው ዓላማ ፌል አድርጓል ማለት ነው፡፡
ኦነግ ከላይ እንዳየናቸው ድርጅች ከንጉሱ ጀምሮ በደርግም እንደገና በኢህአዲግም ሶስት ሙሉ ትውልድን ሲታገል የነበረ ከሚፈልገው ጀሳብና ግብ መድረስ ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ የኦነግ አመራሮች በትግል ውስጥ ነበርን ብለው በሙሉ ልባቸው ለመናገር የሚያስችላቸው ሞራል የላቸውም፡፡ እንወክልሀለን ለነጣነትህ ስንታገል ነበር ለማለትም ድፍረቱም ብቃቱም የላቸውም በትግል ወቅታቸው አንድ ገዤ መሬት መያዝ የተሳናቸው ነፃ መሬት በኦነግ ስም የሚተዳደር ወረዳ ያለው ቀበሌ ያለው ግብር የሚከፈልበት መሬትን ከ 40 ዓመት በላይ በፈጀባቸው የትግል ወቅት ውስጥ ያልያዙትን ነፃ መሬት ዛሬ ላይ በመልካም ፈቃድ ከበረሀው ይልቅ በሀሳብ ታገሉ ተብለው የገቡ መሆኑን እንዴት ይረሱታል፡፡
በትግል ሄደት ውስጥ ዛሬ ላይ የያዝከው መሬት ነገ ላይ በሌላ ሀይል ልትነጠቅ ትችላለህ ነገር ግን እየታገልክ ለመሆኑ ማሳያ የሚሆነው ነፃ ግዛትህን ማስፋፋት አልያም ነፃ ግዛትህ ሲነጥቁህ መልሶ መያዝ መቻል ነው ፡፡ ነገር ግን ይህንን ትግል ውስጥ በምትገኝበት ጊዜ ያላደረከውን ከሆነ ትግሉ ከነ አካቴው ከፅንስሱ ጨንግፏል ማለት ነው፡፡
ዛሬ ላይ ተነስተው የኦነግ ደጋፊ ነን የሚሉ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ የኦሮሞ ደጋፊ መሆን ማለት ኦሮሞ መሆን ማለት አይደለም በሀሳብ የበላይነት ላለው ማንኛውም ድርጅት ገዢ ሀሳብ ይዞ ከመጣ የየትኛውም ድርጅት ደጋፊ ሊኮን ይቻላል ነገር ግን የኦሮሞን ትግል አልያም ፍላጎት አንድ መስመር ፈቀቅ ያላደረገን ከአባት ወደ ልጅ ከልጅ ወደ ልጅ ልጅ የተላለፈን የከሸፈ ትግል ባለቤት ነን ብሎ ማሰብ ግን ሞኝነትም ጭምር ነው ስለዚህ እኔ የኦነግ ደጋፊ ሆኜ እንኳ ቢሆን የ40 ዓመቱን የትግል ስልት አይቼ አንቅሬ እተፋው ነበር፡፡
የኦነግ እንቅስቃሴ ለመላው ኦሮሞ የሚበጅ ቢሆን እና ሁሉም የኦሮሞ ተወላጆች በኦነግ እምነት ቢኖራቸው ኑሮ የበረሀው ትግል ጭንጋፍ ሆኑ ባልቆየ ነበር ነገር ግን መላው ኦሮሞ የኦነግን መስመር ቀድሞ ስለተረዳው ልጁን እንኳ ለዓላማው እንዳይሞት ይገዝት ነበር የኦነግ አላማ የፈጠራ ታሪክ ያልተኖረበትን ህይወት ለመኖር የሚዳዳ በደማቸው እና በአጥንታቸው በነፃነት ያቆሟትን ኢትዮጵያውያን አባቶቻቸውን የካዱ ለፍሬ ያልተቋቋመ ትግል ነበር፡፡ አሁን እንደዛ ነው ትውልዱም መንቃት ያለበት ለምን የዚህን ዓመት ያህል እንጭጭ የሆነ ትግል ሆነ ? ብሎ ታሪክን ቢያገላብጥ አባቶቹን ቢጠይቅ መልሱን እንደሚያገኝ አልጠራጠርም፡፡
Filed in: Amharic