>

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ!

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ!
ከድር እንድሪስ
ከዳዑድ ኢብሳ ኦነግ ጋር ከዓመታት በፊት በአስመራ የተለያዩት ብርጋዴር ጀነራል_ከማል_ገልቹ ቲም ለማን ተቀላቀሉ:: የኦሮሚያ አንድነትና ነፃነት ግንባር መሪ ብርጋዴር ጀነራል ከማል ከዳኡድ ኢብሳ ኦነግ ጋር ከተለያዩ በኋላ ከኤርትራ ወጥተው በኡጋንዳ እንደቆዩ ይነገራል:: “የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች የትጥቅ ትግል ፋሽን ያለፈበት በመሆኑ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሀገር ግቡ” በሚል የቀረበውን የዶ/ር ዓብይ ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩት ጀነራል ከማል:-
* ቲም ለማን በመቀላቀል
* የኦሮሚያ ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ሹመት አግኝተዋል::
በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሚያ አንድነትና ነፃነት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ኦዴፓን ይቀላቀላል ተብሎ በሰፊው ሲነገር የነበረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ድርጅቱ ዶ/ር ዓብይና ለማ መገርሳ ከሚመሩት ኦዴፓ ጋር ይቀላቀል-አይቀላቀል አልታወቀም፡፡ ነገር ግን ጀነራል ከማል ቲም ለማን ተቀላቅለው ይህን ትልቅ ሹመት አግኝተዋል:: ለጀነራል ከማል ገልቹ የተሰጠው ሹመት በተለይም የዳኡድ ኢብሳን ኦነግ እንደማያስደስት የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ::
Filed in: Amharic