>

እየጨፈርን የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!!! (ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ)

እየጨፈርን የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም!!!
ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ
ሁላችንም ዘር አለን፡፡ዘሩ ግን እኛ አይደለንም!እኛ ሰዎች ነን፡፡ሰውነት ከመፈጠር እንጂ ከመወለድ አይጀምርምና ፈጣሪ ዘራችንን ኢትዮጲያ በምትባል ምድር ላይ ዘራው፡፡ ሲዘራው ኢትዮጲያ ማለት ሰዎች መሆኗን አወቅን፡፡ መነጣጠል እስከማንችል ተዋሃድን፡፡ ትናንት የሆነ የሰው ዲስኩር አንዳችንን ካንዳችን ካልለየሁ እያለ ሥያሜ አበጀልን፡፡ ፈጣሪን ለማረም ይመስል እኛም ሆሆሆ ብለን ተቀበልን፡፡
በሕንድ 2032 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ በቻይና 499 ብሔረሰብ በሠላም እየኖረ ምነው እኛ (ሰማኒያዋን) መሸከም አቃተን?ተራ በተራ መግዛታችንን ለበላይነት ተጠቀምንበት?
ማንም ከማንም ጋር የሰውነት ጥል ሊኖረው አይችልም የዕውቀት ጥል እንጂ፡፡ገና ስንወለድ ዘር ምን ይሁን ቋንቋ ምን ይሁን የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡የዕውቀት ጥል ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም፡፡ምክንያቱም ይቅርታ እንጂ በቀል ታሪክን አያርምምና፡፡
ቋንቋ የሚባልን ነገር ከመካከላችን አውጥተን ማሰብ ብንጀምር ዘረኝነት ሃሳብ ላይ እንጂ ደም ላይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡እየጨፈርን የናድነውን ቤት እያለቀስን አንሠራውም፡፡ ሁልጊዜ ጥፋት ካደረስን በኀላ እንዳጠፋን ምንረዳ ከሆነ ዞሮ መልሶ አለማወቅ ይሆንብናል፡፡ በመቻቻል ሳይሆን በፍቅር እንኑር መቻቻል አንድ ቀን ያሰለቸናል፡፡ታገስኩህ ቻልኩህን ያመጣል፡፡ ፍቅር ግን እስከዖሜጋ ይሸከማል፡፡
ከሰውነት በላይ ምን ማንነት ኖሮ የሁሉም መገኛ ያው አዳም ነው ዞሮ የማይሻር ሽረን አይሆኑሽ ሆነናል የማይድን ስናክም የማይሞት ገለናል፡፡
አትዮጵያዊነት ከዘር በላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ  ለሁላችንም በቂ ናት!  እንወዳድ በፍቅር እንኑር፡፡
Filed in: Amharic