አሸብር በቀለ
√… እድሜያችን ሃምሳ ውስጥ የገባነው ኢትዮጵያውያን (ሁላችንም) የደርጉ አስተዳደር ውጡና ሻቢያንና ወያኔን ተቃውውሙ ብሎን በቀበሌ ተገደን የወጣንበትን ቁጥር ስፍር የሌላቸው ቀናትን እናስታውሳለን ።
√ … አሁን በቅርቡ ደግሞ የትግራይ ህዝብ በህወሓት ተገዶ ወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን ላይ አምዖ የተቃውሞ ሰልፍ ወጥቷል ።
••• በዛኛውም ሆነ በዚህኛው ሃይል ያለ ውዴታችን ልንሰለፍ ተገደናል ሆኖም በኔ አስተሳሰብ የትግራይ ህዝብ ተገዶ ወጣ ቢባልም … ይህንን ሰልፍ የትግራይ ህዝብ ወዶም ሆነ ተገዶ ሊወጣ ባልተገባው ነበረ እላለሁ ።
………………………
••• ደርግን በተመለከተ
*** በቀይ ሽብርም ሆነ ሌሎች ጥፋቶች ብዙ ወጣቶች ፡ ዜጎች ደማቸው ያለአግባብ በመፍሰሱ ህዝባችን ደርግ ላይ ቂም ቋጥሮ ነበረ ።
*** በተለያዩ ምክንያቶች ጦርነቱ ስለረዘመና ስለተንዛዛ የህዝቡ በጦርነቱ ሙሉ አቅሙን የማሳተፉ ጉዳይ ፈፅሞ የማይታሰብ ነበረ ።
√√√ ••• ምንም እንኳ መሪያችን ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ከፊታችን ሃገር ሊያጠፋ ታላቅ እቅድ አንግቦ እየገሰገሰ ያለ ከአንበጣ መንጋ የበዛ ሰራዊት እየመጣ እንዳለ ደጋግሞ ቢያስታውቀንም ከላይ በተጠቀሱት ጥቂት ምክንያቶች የተነሳ ህዝባችን ህወሓትንና ሻቢያን ለመዋጋት ወኔው ፈፅሞ ጠፍቶ ነበረ ።
ኮሎኔሉ ከፊቱ እየመጣ ስላለው አደጋ የነገሩት ሁላ እውነትነቱ ለህዝባችን ግልፅ ብሎ ቢታየው ኖሮ ። ስለ ሻብያና ህወሓት አውሬነት በደንብ ቢገባው ኖሮ
ሀ/… ህዝባችን ሰልፍ በግዳጅ ሳይሆን በራሱ አነሳሽነት ቀን በቀን በወጣ ነበር
ለ/… መንግስቱ ኃ/ማርያም ሳይለምነው ÷> በጦር በጎራዴ ታንክ የማረከው ህዝባችን መሳሪያ ቢያጣ እንኳ አካፋና ዶማ ይዞ ሆ ! ብሎ ወጥቶ ሻቢያንና ወያኔን በቀበራቸው ነበር ።
አሁን ብዙዎች ያላዝናሉ >>> ደርግ በግዳጅ ሰልፍ አስወጣን እያሉ ። እኛ ነበርን ደርግን ማስገደድ የነበረብን ። ሃገራችንን አድንልን እያልን መጮህ የነበረብን ። ያንን ስላላደረግን ግን የደረሰውን ፡ እየደረሰ ያለውን ፡ የአልምጥነታችንን ውጤት እያየነው ነው ።
ጥልቅ የሆነ ብሄራዊ ወርደት
………………
√√√ ••• በህወሓት አስገዳጅነት የትግራይ ህዝብ ሰልፍ
*** በ17 ዓመቱ የነፃነት ትግል ወቅት ከደርግ ሰራዊት ጋራ ፊት ለፊት ከተደረገው ፍጥጫ ውጪ የትግራይ ልጆች በ06 በሌሎች በፅኑ ማሰቃያ ስፍራዎች በብዛት እንዳለቁ ከራሳቸው ከትግራውያን በብዛት ሰምተናል
*** ብዙዎች የትግራይ ወጣቶች የህወሓትን እኩይነት በመገንዘብ ለምንም አይነት ነፃነት አንዋጋም ብለው በማመፃቸው ደማቸው እንደ ጅረት እንደፈሰሰ ታሪክ አውርቶልናል ትግራውያን ወንድሞቻችንም አጫውተውናል ።
*** ደርግን ለማሸነፍ ሲል ህወሓት ብዙ እኩይ ስራዎችን ፋብሪኬት አድርጎ ብዙ ምስኪን የትግራይ ተወላጆችን እንደጨረሰ ትግራዮችም እኛም እናውቃለን ።
*** ከነፃነትም በኃላ የትግራይ ህዝብ በህወሓት መዳፍ ውስጥ በግላጭ ገብቶ ብዙ በደል እንደደረሰበት ነው የምንሰማው ።
*** ከዛ ውጪ የትግራይ ህዝብ ለሺህ ዘመናት አብሮት የኖሩት ፡ በሌላ ክልል የሚኖሩ ወንድምና እህቶቹ ከአብራኩ በወጡት እኩይ ልጆቹ እየደረሰባቸው የነበረውን የሚደርስባቸውን ግፍ በደል በደንብ አድርጎ አይቷል ያውቃል ።
*** አሁንም በዘመነ ዓቢይ አህመድ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ ሃገሪቱ ላይ ቅጥ የለሽ ዝርፊያ በማካሄድ ምን ያህል እንዳዋረዷት ፡ ወደማትወጣበት መቀመቅ እንደሰደዷት የትግራይ ህዝብ ጥንቅር አድርጎ ያውቃል ። በዚህም ሊቆጨው በተገባው ነበረ ።
እንግዲህ ወደ መደምደሚያው እንምጣ
√√√ ••• በዘመነ ደርግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሓትና ሻቢያ ማን መሆናቸውን በበቂ ማስረጃ አስደግፈው ቢያስረዱትና ቢያውቅ ኖሮ ሰልፍ እንዲወጣ ሊያስገድዱት ባላስፈለገም ነበረ ። ጦርነቱ በአንድ ቀን ባለቀም ነበረ ።
√√√ ••• ወርቆቹ ፡ ብሶት የወለዳቸው ፡ ተራራ የሚያንቀጠቅጡት የትግራይ ልጆች ህወሓትን
ሀ/… ካወላለዱ ጀምሮ ማን እንደሆን እያወቁት
ለ/… በ17 ዓመቱ ግብግብ ብዙ ጉዳት አድርሶባቸው ሳለ
ሐ/… ስልጣን ይዞም በቀዬያቸው አላኖርም እያላቸው ሳለ
መ/… ወንድሞቻቸው የሆኑ የሌሎች ብሄሮች ኢትዮጵያውያን ላይ ለማውራት የሚቀፍ የግፍ መዓት ማውረዱን ማሰቃየቱን ጃኖሳይድ መፈፀሙን እያወቁ ሳለ
ሠ/ … ሀገሪቱን እንጥፍጥፍ አድርጎ መዝረፍ ማዘረፉን እያወቁ ሳለ
ህወሓት አስገድዷቸውም ይሁን በውድ ወንድሞቻቸውን ኢትዮጵያውያንን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት አልነነረባቸውም እላለሁ ።
ይሄ በበሉበት ሰሃን ላይ መትፋት ይባላል ።