>
5:13 pm - Monday April 19, 8810

የኦሮምያው ፍጅት ምንጩ መቀሌ ነው!!! (ሀይል ገብርኤል አያሌው)

የኦሮምያው ፍጅት ምንጩ መቀሌ ነው!!!
ሀይል ገብርኤል አያሌው
 
አስገዳዮቹ ከሌላ ወገን ቢሆኑም ገዳይ ከራስ ብሄር ሲሆን ነገሮች ፈጥኖ የማለባበስና ገዳይም እኛ ሟችም እኛ ማንም አይስማብን አይነት የማለባበስ አካሄድ ለዜጎች ደህነትም ሆነ ለህግ የበላይነት አደገኛና አካሄድ መሆኑን መረዳት ይገባል!
 በኦሮሚያ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጭፍጨፉ ከልብ አዝነናል:: ከተራ ዜጎች አልፎ የጸጥታ አባላትን ጭምር ወደ ማጥቃት የተሸጋገረው የሽብር ዘመቻ አደራጅና ስፖንሰሩ መቀሌ ምሽግ ያደፈጠው አሮጌ የጅብ መንጋ ለመሆኑ ነብይ መሆን አይጠይቅም:: ትላንት ዶር አብይን ለመግደል ሞክሮ ከሸፈ :: በየአቅጣጫው የጎሳና የድንበር ግጭቶች በመለኮስ ሃገሪቷን በቀውስ አዙሪት ወጥሮ በየቦታው ወገኖቻችንን እያጣን ነው:: አላማው የተጀመረውን ፍትሕ የማስፈን ዘመቻ በማወክ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ከተቻለም ያጡትን ስልጣን ለማስመለስ  የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::
መንግስት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ይኖርበታል:: በወንጀልና በዝርፊያ ተጠርጥረው መጥሪያ የተላለፈባቸው ባለስልጣናት የፍትሕ ሂደቱን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም:: በተለይም መቀሌ የመሸገው የሕወሃት ቡድን በግልጽ ካቀረበው ተቃውሞ ባሻገር በምስለኔዎቹ አገሪቷን እንደምትፈርስ እያስነገረ በተዘዋዋሪ የሽብር ቡድኖችን እያደራጀ በየአቅጣጫው ሁከት አንግሷል:: የዶር አብይ አመራር በትግራዩ ስርዐት አልበኛ ጉጅሌ ላይ ከበጀትና አስተዳደራዊ እቀባ እስከ ሃይል ተጠቅሞ የአሮጌ ጅቦቹን ምሽግ ሊንድ ይገባል:: አልያ ይህ በሰው ደም መታጠብ የለመደ የሽብር ቡድን በተላላኪዎቹ በኩል ሃገሪቷን የብጥብጥ አውድማ አድርጓታል።
ጉዳዩን በሌላ አንግል ስናየው. አስገዳዮቹ ከሌላ ወገን ቢሆኑም ገዳይ ከራስ ብሄር ሲሆን ነገሮች ፈጥኖ የማለባበስና ገዳይም እኛ ሟችም እኛ ማንም አይስማብን አይነት የማለባበስ አካሄድ ለዜጎች ደህነትን ሆነ ለህግ የበላይነት አደገኛና አካሄድ መሆኑን እንደ ማሳያ ጃዋርን እና ለማን እንውሰድ:-
ጃዋር መሐመድ፣ለማ መገርሳና ሌሎችም በሶማሌ ክልል ተወላጆች የብሄራችን አባላት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል ባሉ ወቅት ምን አይነት ምላሽ እንደሰጡ ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው፡፡ኦቦ ለማ ከያኔው የግምባራቸው አጋር አብዲ ኢሌ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዴት በቁጣ ይንቀጠቀጡ እንደነበር ማንም የሚስተው አይመስለኝም፡፡
ጃዋር በበኩሉ በማህበራዊ ገጾች አናብስት ነበር፡፡ሌሎቹም የሱማሌ ክልልን ለመኮነን አቻ አልነበራቸውም፡፡ገዳዩ የሌላ ክልል ተወላጅ ነዋ፡፡ገዳዩ የራስ ብሄር ተወላጅ ሲሆንስ ?ለማ የለ ፣ መግለጫ የለ ፣ ያ ሁሉ ወገናዊነት የለ፡፡ሁሉም አንገቱን ቀብሮ ‹‹ምነው ለዛሬ ገዳዩ ከሌላ ብሄር በሆነ ይልልሃል››፡፡እናም የእኛ ነገር ይሄው ነው ፡፡አሳሪው፣ገዳዩ፣አፋኙ፣ረጋጩ ከሌላ ይሁን እንጂ ከእኛው የእኛው ብሄር ከሆነ ብዙም ጣጣ የለውም፡፡
Filed in: Amharic