>
9:01 pm - Tuesday July 5, 2022

ህወሀት ሆይ በዚህ የጭንቅ ሰአት እንኳ እስኪ ልብ ግዢ - ወደ ህሊናሽ ተመለሽ?!? (ውብሸት ማናዬ)

ህወሀት ሆይ በዚህ የጭንቅ ሰአት እንኳ እስኪ ልብ ግዢ – ወደ ህሊናሽ ተመለሽ?!?
ውብሸት ማናዬ
“የትግራይ ሕዝብ እየተደበደበ ነው።የትግራይ ሕዝብ ስጋት አለበት በየትኛው ሥፍራ።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም ክልል የመሥራትና ንብረት የማፍራት መብት በሕገ መንግሥቱ የተሰጠው መብት ነው” ይህች ጩህት ከጣራ በላይ መሰማት የጀመረችው  ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡና የሰው ልጅ እኩል ነው ማለትና ሌቦችንና የሰውን ልጅ ከአውሬ ባላነሰ ሲነክሱና ሲበሉ የነበሩት መያዘ ሲጀምሩ ነው።
የሚገርመው ግን ትናንትና የአማራ፤የኦሮሞ፤የኮንሶ ፤የጋምቤላ ሕዝቦች እንደ ከብት ሲታረዱ፤ እንደሚታደን አውሬ በአጋዚ ስናይፕር ሲረሹን የዛሬውን ዓይነት ጩኽት ከትግሬ አልሰማንም ነበር።
* የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትህን በጠየቀበት ሰላማዊ ስልፍ ሲረሸን መቐለ አላለቀሰችም ነበር።
* የኢረቻ በዓል በቢሾፍቱ ሲከበር ከሰባት መቶ በላይ የኦሮሞ ልጆች ሲገደሉ መቐለ ከበሮ እየተመታ ፈንጠዝያ ላይ ነበረች።
* የአማራ ስም ያላቸው ሁሉ ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ሲፈናቀሉ ጭራቁ መለስ ዜናዊ በፓርላማ “አማራው ሞፈር ዘመት በመሆኑ ደኖችን ስለሚጨፈጭፍ ወደመጣበት መመለሱ መልካም እርምጃ ነው” ሲል መቀሌ ” ሀድጊ አማራ የታባቱ” ትል ነበር።
* “…የኦሮሞው ደም ደሜ ነው፣ የታሰሩት ይፈቱ ፣ ወልቃይት ራያ የአማራ መሬት ነው….” ብሎ የፍትህ ጥያቄ ላነገበው የአማራ ህዝብ የታጠቁትን አራጆችሽን ወደ ባህርዳር በመላክ በአንድ ቀን ከሃምሳ በላይ  ወጣቶች መረሸን ነበር ምላሽሽ።
* ይህ አልበቃሽም በሱማሌው መሪ ተብዬ፤ የራስ ቅል ብቻ ተሽክሞ የሚሄደውን ፤ አብዲ ኢሌንና ሰራዊቱን አስልፈሽ ዘር ተኮር ጥቃት አስፈጸምሽ በጅምላ መቃብር እየረሸንሽ የከተትሻቸው ንጹሀን አስከሬን እየወጣ ነው።
ሌላም ብዙ ብዙ ግፍ…..
መቐለ ሆይ ዛሬ እንኳን ወደሕሊናሽ ተመለሽና የምታደርጊውንና የምትናገሪውን በጥንቃቄ አስቢበት። መግደልን ያስተማርሽ፤ ፍትህን ያደፈረስሽ፤ ሌብነትንና ዘረፋ ያስተማርሽ፤ ዘረኝነትን ያስፋፋሽ፤ ሕዝብን ከየቦታው እንዲፈናቀል ፈቃድ የሰጠሽና በሕገ መንግሥት እንዲጸድቅ ያደረግሽ አንቺው ነሽ።
አሁን ግን ጻድቅ ሆንሽና ሕገ መንግሥት ይከበር ትይናለሽ። ሕገ መንግሥቱ እኮ ሕዝብ የተስማማበት ሳይሆን ለእኩይ ሥራሽ ያዘጋጀሽው የተንኮል መረብ ነበር። አሁንም ወደዚህ መርዘኛ መረብሽ ካልተመለስኩ እያልሽን ነው። ይህ እንኳን ተረት ተረት ነው። አይመለስም። እያለቀስሽ ትኖሪያለሽ እንጂ መረብሽን እንደገና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መዘርጋት አትችይም።
ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው በተሰየሙበት ጊዜ መቐለ ድረስ በመምጣት በራስሽ ቋንቋ መልካም ዜና አበሰሩልሽ። አንቺ ግን በአዲስ አበባ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለሆዳቸው ያደሩትን፤ ሕሊናቸውን የሳቱትን፤ አስተሳሰባቸው ከአፍንጫቸው የማይርቀውን አሰልፈሽ ቦንብ አስፈነዳሽ። ንጹሐን ዜጎችን እንዲገደሉ፤ አካላቸው እንዲጎድል አደረግሽ። ሰላም ፤እኩልነት፤በፍቅርና በአንድነት መኖርን፤መደመርን አልቀበልም አልሽ። ። እርግጠኛ ነኝ ይህ ሁሉ ይታወስሻል።የአራት ኪሎ ቤተመንግሥት ከእኔ እጅ አይወጣም ብለሽ በአዋሳ በተደረገው የኢሕአደግ ስብሰባ ዶ/ር አቢይ አህመድን ከስልጣን ለማውረድ ሞክረሽ ግን ከሸፈብሽ።ይህ ባለመሳካቱ እያለቀስሽ ወደመቐሌ ተመልሰሽ መሣሪያ የታጠቁ ወታደሮች ልከሽ ዶ/ር አቢይ አህመድን ከቢተ መንግሥት ለማስወገድ ሞከርሽ ግን ሊገባሽ በማይችል ሁኔታ ይህም ተኮላሸብሽ።አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ወላጆች ልጆቻቸውን ለከፍተኛ ትምህርት በላኩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የግድያ ሥራ ጀመርሽ።ይህም አትጠራጠሪ ይወድማል።ኢትዮጵያ ከእንግዲህ እንደመቐለ ያለአመራር የመሸከም ፤የማስተናገድ ፤የማባበል ዘይቤ የላትም።ይልቅስ መደመሩ ያዋጣሻል።ሕገመንግሥት ይከበር የሚለው ለቅሶ ይብቃሽ።መለስ ዜናዊን ለመጨረሻ ጊዜ እንደቀበርሽው ሕገ መንግስትሽን ብትቀብሪው መልካም ይሆንልሻል።እርግጥ በምታዘጋጂው ሰላማዊ ሰልፍ፤የጦርነት ጥሪ ሰልፍ፤የለቅሶ ሰልፍ፤ የጭራቁን የመለስ ዜናዊ ምስል ተሸክመሽ እሽከም ትያለሽ።ለዚህ ሁሉ ሰቆቃና ለቅሶ ያደረሰሽ መለስ ዜናዊ ሆኖ እያለ አሁንም ምስሉን ተሸክመሽ ከበሮ ትደልቂአለሽ።
እኔ ግን የምለው እንዲህ ነው።አደብ ግዢና ዶ/ር አቢይ አህመድን፤በአሁኑ ሰዓት የሕዝብ ንብረትና እግዚአብሔር የሕዝቡን ጩኸት ሰምቶ ያመጣውን መሪ የሚልሽን አዳምጭ።ለአንቺም ለልጆችሽም ሰላምና አንድነትን ሊያመጣልሽ የሚችለውን የለውጥ መንገድ ከሌላው ወገኖችሽ ጋር ሆነሽ የኢትዮጵያን መልካም ጊዜ ለመካፈል ብትሞክሪ መልካም ነው።ኢትዮጵያን ነጻ አወጣሁ የምትይውን ባዶ ቀረርቶ አቁሚው፤ ይብቃሽ።የኢትዮጵያዊያ ልጆች ሁሉ ደማቸውን አፍስሰዋል ለዚህ አሁን ለደረስንበት ነጻነት።የአንቺ ልጆች ግን የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት ብቻቸውን በልተውታል፤መዝብረውታል፤በውጭ አገር ባንኮች ቆልለውታል።በየዕለቱ የምታነበንቢልን የትግል ታሪክ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መከራን፤መራብን፤መዋረድን፤መፈናቀልን፤መገደልን፤መታሰርን፤ እንደቋንጣ በማዕከላዊ እሥር ቤት መንጠልጠልን ጥፍር መነቀልን፤ዘራፊዎችንና ሌቦችን ሰጥቶናል።ታሪክ ጉድሽን እስኪያወጣው እታገሳለን። አንቺ ግን በይቅርታ ብትመለሺ መልካም ይሆንልሻል።ለዘረፋ ያሰማራሻቸውን፤ሕዝብን ጨቁነሽ ለመግዛት በመላው አገር ያሰማራሻቸውንና ሲገድሉ የኖሩትን ትግርኛ ተናጋሪዎችን ተገረፉ፤ ተፈናቀሉ፤ተዋረዱ፤ተዘረፉ እያልሽ አታልቅሺ። ዘረፋ የተጀመረው ባንቺው ነውና ብዙም አያስኬድሽም። ይልቅስ በቤንሻንጉል፤ በደቡብ ክልል፤ በአፋር ፤በዩኒቨርሲቲዎች የምታደርጊውን የግድያና የማፈናቀል ተግባርሽን አቁመሽ የሰላም ለውጡን ተቀላቀይ።
Filed in: Amharic