>
5:13 pm - Tuesday April 19, 6687

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው የተጠረጠሩባቸውን ተጨማሪ ወንጀሎች ለፍርድ ቤት ቀረበ!!! ፋና ብሮድካስቲንግ

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው የተጠረጠሩባቸውን ተጨማሪ ወንጀሎች ለፍርድ ቤት ቀረበ!!!
ፋና ብሮድካስቲንግ
* መርማሪ ፖሊስ ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘውን በተመለከተ እስካሁን በሰራው የምርመራ ስራ አገኘኋቸው ያላቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
🇪🇹
ፖሊስ በዛሬው እለት ግለሰቡን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ካቀረባቸው ማስረጃዎች በተጨማሪነት አዳዲስ ያላቻውን ነው ያቀረበው።
  ❶ በዚህም በ2003 ዓ.ም በሜቴክ ስም ከተለያዩ ተረፈ ምርቶች ወይም ቆሻሻ የናፍጣ ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካን ለመግዛት ያለ ምንም ጨረታ ኬዲቪ ከተባለ የጀርመን ኩባንያ ጋር የ8 ሚሊየን ዩሮ ግዥ ውል በመፈጸም፥ ከዚህ ውስጥ 4 ሚሊየን 800 ሺህ ዩሮ ለኩባንያው እንዲፈጸም በማድረግ እንደጠረጠራቸውና ከዚህ ጋር የተያያዙ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች መሰብሰቡን ጠቅሷል።
🇪🇹
❷በተጠቀሰው ዓ.ም ሜቴክ ከኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በመመሳጠር ከመመሪያ ውጭና ያለ ግዥ ፍላጎት የ22 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 20 ተሽከርካሪዎች ግዥ እንዲፈጸምና ለተፈጸመው ግዥ ክፍያ እንዲፈጸም ለኮርፖሬት ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ማኔጅመንት አላግባብ ትዕዛዝ ሰጥተዋል በሚል የተጠረጠሩ፤
❸ተጠርጣሪው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም የኢምፔሪያል ሆቴል ግዥ በ71 ሚሊየን ብር ከአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እንዲፈጸም በማድረግ፣
❹ባለ አምስት ወለል ህንጻ በ15 ሚሊየን ብር ከያማሉክ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ግዥ እንዲፈጸም በማድረግና በማፅደቅ።
❺ባለ አራት ወለል ህንጻ በ24 ሚሊየን 56 ሺህ ብር ከአቶ አለሙ ደምሴ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣
❻ባለ አንድ ወለል የመኖሪያ ህንጻ በ5 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ጌታቸው አቃኔ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ፣
❼ባለ ሁለት ወለል ህንጻ የመኖሪያ ህንጻ በ8 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከአቶ ሙላቱ ረዳ እና ከወይዘሮ ሄለን በለጠ ግዥ እንዲፈጸም በማድረግ እና ባለ ሶስት ወለል ህንጻ በ12 ሚሊየን 700 ሺህ ብር ከጌት ፋም ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ባለቤት አቶ ጌታሁን በሻህ ግዥ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በመስጠት፥
❽ውሎችን በማፅደቅ ግዥ እንዲፈጸምና የህዝብና የመንግስት ሃብት እንዲባክን በማድረግ የተጠረጠሩ።
❾ከቆሻሻ የጄት ነዳጅ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ከግዥ መመሪያ ውጭ ጨረታ ሳይወጣ ኢ ቪ ጂቲዲሲ ዌስት ቱ ኢነርጅ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር የ347 ሚሊየን 948 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ውል ስምምነት ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤል 2005 ዓ.ም ላይ ውል እንዲዋዋል በማድረግና ውሉን በማፅደቅ፣
❿የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤል ሲ በማስከፈት፣
ለባንክ አገልግሎት የሚውል ክፍያ 5 ሚሊየን 616 ሺህ 648 ብር ከ60 ሳንቲም የግንባታ ስራ ውል ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ ውሉ ባልታወቀ ምክንያት በመቋረጡና ስራው ሳይሰራ ያለ አግባብ የመንግስት ገንዘብ እንዲባክን በማድረግ የተጠረጠሩ፤
⓫ከዚህ ባለፈም ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ እንዲሁም ከፋይናንስ ህግ ውጭ በሆነ ሁኔታ በነሃሴ ወር 2003 ዓ.ም ለአቤራ ኪነ ጥበባት ማዕከል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በስፖንሰር መልክ 536 ሺህ ብር በመስጠትና 306 ሺህ ብር በብድር መልክ መስጠትና የተበደረው ተቋም ገንዘብ ያልተከፈለ መሆኑ፥
⓬የኮርፖሬሽኑ አባላት ያልሆኑትን አባላት እንደሆኑ በደብዳቤ በመግለጽ ለተጠርጣሪ ፍጹም የሽጥላ በቀለ እና ለአቶ ተስፋሁን ሰብስቤ ለ30 ቀን የአሜሪካ ቆይታ 23 ሺህ ዶላር በሃምሌ ወር 2008 ዓ.ም እንዲከፈል በማድረግ፤
⓭እንዲሁም ለአቶ ዝናህ ብዙ ፀጋዬ ለ20 ቀን የአሜሪካ ጉዞና ቆይታ 7 ሺህ 687
ከ50 ዶላር ከንግድ ባንክ እንዲከፈል በማድረግ ወጪው ከኮርፖሬት ፋይናንስ ኢንቨስትመንት እንዲሸፈን ደብዳቤ በመጻፍ፣
 ⓮ለኮሎኔል አታክልት ወልደሚካኤል ልጅ ዮናስ አታክልት የውጭ ሃገር ህክምና 86 ሺህ 889 ሺህ ከ54 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ፣
⓯ለወይዘሮ ንግስቲ ከሰተ የውጭ ሃገር ህክምና 18 ሺህ 454 ሺህ 51 ዶላር ክፍያ እንዲፈጸምና ሌሎችም እንዲጠቀሙ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረግ የተጠረጠሩ፤
⓰በ2004 ዓ.ም የግዥ ዘመን ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ የጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎቹ ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 10 ሚሊየን 670 ሺህ 184 ዶላር በማውጣት፥
⓱ኖሮኮን ከተባለው የቻይና ኩባንያ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት የተጠረጠሩ፤
⓲ከግዥ መመሪያ ውጭ አለም አቀፍ ጨረታ ውድድር ሳይደረግ ከመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የግዥ ውል በማፅደቅ 660 ሺህ ዶላር በማውጣት፥
⓳ዳኑቢያን ኤርክራፍት ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት የአገልግሎት ግዥ በህገ ወጥ መንገድ እንዲፈጸም በማድረግ መንግስት ከጨረታ ውድድር ሊያገኝ የሚገባውን ጥቅም በማሳጣት፤
⓴ሜቴክ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ከ13 በላይ አለም አቀፍ ኩባንያዎችን ያለምንም ጨረታ እና ውድድር በሰላሳ የተለያዩ የውል ስምምነቶች ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግዥዎች እንዲከወኑ ተደርጓል፤
ተጠርጣሪው እነዚህ ውሎች ውስጥ ለጊዜው የተረጋገጠ 15 የሚሆኑ ውሎችን አፅድቀዋል እንዲሁም ተፈራርመዋል።
የእርሳቸው ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘውን የተጠረጠሩባቸውን የሙስና ወንጀሎችም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
በተጨማሪም ፖሊስ ጋዜጠኛ ፍፁም የሺጥላ ላይ መስርቶት የነበረውን የክስ አቤቱታ ለጄነራል ክንፈ አሸጋግሮታል!
 ለራሷና ለአንድ ሌላ ግለሰብ የሜቴክ አባል መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ በመፃፍ አሜሪካን ሄዳ እንደነበር በመጥቀስ ፖሊስ እንዳሰራት ለፍርድ ቤት መናገሩ አይዘነጋም።
ይሄው ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍፁምን ሊወነጅል ያሰበበትን ክስ ክንፈ ላይ ጠቅሶታል “የኮርፖሬሽኑ አባላት ያልሆኑትን እንደሆኑ በማስመሰል ለፍፁም የሺጥላና ለአቶ ጥላሁን ሰብስቤ ደብዳቤ ፅፈዋል” ብሏል
Filed in: Amharic