>

የቅማንት ኮሚቴ ጀርባው ህወሀት መኖሩ በማስረጃ ተረጋገጠ! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

የቅማንት ኮሚቴ ጀርባው ህወሀት መኖሩ በማስረጃ ተረጋገጠ!
 
–  የውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያ ሁሉ በወያኔ ተከፍቶላቸዋል!
ሙሉነህ ዮሃንስ
‹‹አካባቢውን ለማወክ የሚፈልጉ ኃይሎች ሦስት ቀበሌዎችን ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ በማድረግ ላለፉት አራት ዓመታት የወታራዊ ማሰልጠኛ አድርገዋቸዋል፡፡›› 
የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ፡፡
==========
እንደ ኃላፊው ማብራሪያ በተለይ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ የሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች ለዓመታት በወታደራዊ የማሰልጠኛ ማዕከልነት እያገለገሉ ለአካባቢው አለመረጋጋት ምክንያት ሆነዋል፡፡ ጉባይ ጀጀቢት፣ ሌጫና መቃ የሚባሉ ሦስት ቀበሌዎችን አካባቢውን ለማወክ የሚፈልጉ ኃይሎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ በማድረግ ላለፉት አራት ዓመታት የወታደራዊ ማሰልጠኛ አድርገው መቆየታቸውንም ነው ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ያስታወቁት፡፡
ቢሮ ኃላፊው ‹‹ለሰላም መደፍረስ ሰበብ የሚደረጉት ቀበሌዎች ወደ ቅማንት አስተዳደር እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ የመልክአ ምድር ትስስር የላቸውም፤ በመልክአ ምድር ያልተያያዙ አካባቢዎችን በአንድ አስተዳደር ማካተትን ደግሞ የሀገሪቱ ሕገ-መንግሥትም የዓለም ልምድም አያሳይም›› ብለዋል፡፡
እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ባለ መረጃ በቅማንት ሰበብ የተደራጁ ቡድኖች በጥቅም በመደለልና ከሌላ አካል ተልዕኮ በመቀበል ከሰሞኑ በቀሰቀሱት አለመረጋጋት በጭልጋ አካባቢ በሰባት ቀበሌዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤የሰው ህይወትም ጠፍቷል፡፡
እንደ ቢሮ ኃላፊው መረጃ  በማሰልጠኛ ማዕከልነት ሲያገለግሉ የቆዩትን ቀበሌዎች ወደ መንግሥት መዋቅር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
======
ባለፉት ሰሞናት ከመትረጌስ እስከ ክላሽ በመኪና እየተጫነ በመተማ መስመር ሊገባ ሲል ሲያዝ የነበረው ከማን ተልኮ ለማን እንዲደርስ መታለሙን ስንሰማ ቆይተናል። ስለሆነም ወያኔ የሚጭረውን እሳት በማጥፋት ጊዜ ከማባከን እንዳንረከበው የፈለጉትን ወልቃይትን ወደ መረከብ አቅጣጫ ብናስተካክል ይበጃል።
Filed in: Amharic