>

እነሱ ዛሬም ስራ ላይ ናቸዉ! ስራ ዉስጥ ያልገባነዉ እኛ ነን!!! (ቹቹ አለባቸው)

እነሱ ዛሬም ስራ ላይ ናቸዉ! ስራ ዉስጥ ያልገባነዉ እኛ ነን!!!
ቹቹ አለባቸው
 
ያልገባኝ ነገር: የሌቦች መያዝ የትግራይን ክብር እንዴት ነዉ የሚነካዉ? ሌባና ወንበዴን ማደንስ እንዴት ነዉ ትግራይን ለማንበርከክ ነዉ ተብሎ የሚታሰበዉ? ይች ትግራይ የምትባል ” አገር” ክብሯ የሚረጋገጠዉ ሌቦቿን አሳልፋ ባለመስጠት ነዉ እንዴ? የአገሪቱ (ትግራይ) ክብርና ዝና በሌቦችና ወንበዴወች መኖር ላይ የተመሰረተ ነዉ እንዴ?!?
ህወሀታዊያን የሚነሳባቸዉን የስርቆትና ሌብነት ወንጀል ለማጣፋትና: የመንግስትንና መላ ህዝባችንን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ትግራይ ዉስጥ: ሁሉም አካላት ማለት ይቻላል (  ካልሆነም አብዛኛዉ ሰዉ  ) ተቃዋሚ ሆነ በተለይም ወጣቱ : ከህወሀት ጎን ተሰልፎ: ” ወንጀለኞቻችንን  ለፌደራል መንግስት አሳልፈን  አንሰጥም” ይሄ ሆነ ማለት የትግራይ ክብር ዝቅ አለ ማለት ነዉ ሲባል እየሰማን ነዉ። እነዚህ ወገኖች: በአሁኑ ወቅት መንግስት ትግራይ ዉስጥ የሚካሄደዉን የሌቦች አደና: ትግራይን ለማንበርከክ የተከፈተ ዘመቻ አድርገዉ ወስደዉታል።
ለሁሉም እንደሰማሁት ከሆነ: በዛሬዉ እለት: መቀሌ ዉስጥ ” ሌቦቻችንን አሳልፈን አንሰጥም: ይሄን አደረግን ማለት የትግራይን ክብር አስደፈርን ማለት ነዉ: መንግስት ሌቦቻችሁን አስረክቡ የሚለን ትግራይን ለማንበርከክ ነዉ” ወዘተ… የሚሉ መልእክቶችን ያነገበ ሰልፍ እንደሚካሄድ ነዉ። ሰልፉ ጥሩ ነዉ:የመሰለፍ መብት ተነፍጎት ለከረመ ወጣት :መሰለፉን እንጅ የሰልፉ ይዘትና ሰልፉ የሚያስከትለዉ ዉጤት አያስጨንቀዉም።
የኛዉ ወጣት ደግሞ የራሱን አጀንዳ ረስቶ: በህወሀት አጀንዳ ተጠልፎ:የሰልፉን ጉዳይ ሲተነትን መዋሉ አይቀርም: ግን እኮ ብዙ የራሳችን የቤት ስራ አለብን።
ግን ያልገባኝ ነገር: የሌቦች መያዝ የትግራይን ክብር እንዴት ነዉ የሚነካዉ? ሌባና ወንበዴን ማደንስ እንዴት ነዉ ትግራይን ለማንበርከክ ነዉ ተብሎ የሚታሰበዉ? ይች ትግራይ የምትባል ” አገር” ክብሯ የሚረጋገጠዉ ሌቦቿን አሳልፋ ባለመስጠት ነዉ እንዴ? የአገሪቱ( ትግራይ  ) ክብርና ዝና በሌቦችና ወንበዴወች መኖር ላይ የተመሰረተ ነዉ እንዴ? እንዲህ ከሆነ ነገሩ እንዴት ነዉ አብሮ የሚኖረዉ? አንዱ ሌባ ደባቂ:ሌላዉ ሌባ አሳዳጅ: ደግሞ ባንድ ድርጅት ጥላ ስር ተሁኖ!
ብቻ በህወሀት ሰበብ የአገራችን ነገር ወደ አሳሳቢ ደረጃ ተሻግሯል። ህወሀት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲሰራበት የኖረዉ አማራን በተለይም ጎንደርን የማዳከም ስልቱ: ከሞላ ጎደል ስርቶለታል። በዚህም መሰረት ሁለቱን ወንድማመች ህዝቦች(ቅማንትና አማራ ) እያዳማቸዉ ነዉ። የኛ ምላሽ ደግሞ: ከዉግዘትና ከሰልፍ አልዘለለም። የትግራይ ወጣቶችም ከነገ ዛሬ ህወሀትን ያስተካክሉት ይሆናል ብለን ስንጠብቅ: ይባስ ብለዉ ህወሀትን አትንኩብን እያሉን ነዉ።
አሁን ወደ መፍትሄዉ ማምራት አለብን። የህወሀትን ሰልፍ ስናዳምቅ ከመዋል: የቅማንትና አማራን ችግር እንዴት እንፍታ? በሚለዉ ጭብጥ እናተኩር። እንዲሁም ከመቸዉም ጊዜ በላይ አንድነታችንን እናጠናክር: በዋና ጠላታችን ላይ እናተኩር:በሆነ ባልሆነ ነገር አንጨቃጨቅ: ጊዜና ጉልበታችንን አናባክን። የትግራይ ወጣቶች የሆዳቸዉን በሆድ አድርገዉ: ወንጀለኛን አሳልፌ አልሰጥም ከሚለዉ ህወሀት ጎን ሲሰለፉ እያየን ነዉ። ህወሀት ይሄንን አጀንዳ በሚገባ ተጠቅማ በተሳሳተ መንገድም ቢሆን:የትግራይን ህዝብ በተለይም ወጣቱን ከጎኗ ማሰለፍ ችላለች። በርግጥ እንዲህ አይነት አካሂያድ ብዙ ርቀት አይሰድም።
ጥያቄዉ- የኛዉ አዴፓ:የኛወቹ አማራዊ ድርጅቶችና መላ የአማራ ወጣት: ይሄንን በህወሀት አስተባበረሪነት ከተለያየ አቅጣጫ: የተደቀነብንን ፈተና በብቃት ለመመከት: ምን ያክል ተዘጋጅተዋል? እንዴዉ ንግግርስ ተካሂዷል? ወጣቱስ የሆዱን በሆዱ ይዞ: የትግራይ ወጣቶች እንዳደረጉት እያደረገ ነዉ? አዴፓስ?
በመጨረሻም- ወቅቱ ለአገራችን ከባድ ፈተና ሁኗል። በተለይም ለአማራ ከባድ እየሆነ ነዉ።ይሄንን እዉነታ እየመረረንም ቢሆን እንጋተዋለን። እየሞትን ደህና ነን ልንል አንችልም። በአሁኑ ወቅት አማራ የገጠመዉ ፈተና በአንድ አቅጣጫ ብቻ አይደለም። የኛ ዝግጁነት ደግሞ በዚህ ልክ ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ። ስለሆነም: ይሄንን ፈተና በአሸናፊነት ልናልፈዉ ከሆነ:አዴፓ: የአማራ ድርጅቶችና የአማራ ወጣት በአንድ መቆም አለባቸዉ። የዉስጥ ጉዳዮቻችን ይቆዩን: አሁን ከሁሉም በፊት አማራንና መሬቱን እናድን። ከዚህ ውጭ እንደተለመደዉ ዘባተሎ ነገር እያነሳን እርስ በርሳችን በመካሰስና በመወቃቀስ ጊዜ ለማጥፉት ከሞከርን: የትልቅ ትንሽ የመሆን እድላችን ፊት ለፊታችን የተደቀነ ስለመሆኑ አትጠራጠሩ። ይሄ እንዲሆን ደግሞ አንፈቅድም: ግን ደግሞ በፍላጎት ብቻ አይገኝም። ወደዚህ አሳፋሪ ደረጃ እንዳንደርስ ከተፈለገ: እንተባበር:እንደማመጥ:እንተሳሰብ : በጋራ እንቁም።
Filed in: Amharic