>
5:04 pm - Friday August 19, 2022

በህወሀት ሰዎች ያልተፈጸመ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በምድር ላይ ይኖር ይሆን? (የግፍ ሰለባው ዮናስ በጋሻው)

በህወሀት ሰዎች ያልተፈጸመ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በምድር ላይ ይኖር ይሆን????
 
“የፍትህ ሰቆቃ!” በሚል ርእስ ኢ.ቲ.ቪ ማክሰኞ ምሽት ባቀረበው በህወሀት እና ተላላኪዎቸ በፍትህ ስም ይፈጸሙ የነበሩ  አሰቃቂ  ኩነቶችን በዶክመንተሪ  መልክ አቅርቦታል ይህንኑ ተከትሎ ከህብረተሰቡ የተሰጡ አስተያየቶችን እና የጥቃቱ ሰለባዎችን በእንባ የታጀቡ ልብን የሚሰብሩ የስቃይ ድምጾች አካተናል ሊንኩን ይጫኑ:-
—–
የግፍ ሰለባው ዮናስ በጋሻው 
.
የዚህን ወጣት የግፍና የስቃይ ጥልቀት ምን ቃል ሊገልፀው ይችላል ? …. ለመሆኑ ይህ ወጣት ምን አይነት የጥንካሬ ፀጋ ቢሰጠውስ ነው በይሕወት ቆሞ ይህንን የሰቆቃ ታሪክ የሚተርክልን ?
ዮናስ ፦
ወላጅ አባቱን ከሃገር ሰደዱበት እንዲሁም  ከአብራኩ ክፋዮችና ከትዳር አጋሩ ጋር ሳይገናኝ በባእድ ሃገር ገደሉበት ፤
ባልሽን አምጪ እየተባለች እናቱ ተሰቃየች ፤ ከስራዋ ተባረረች ፤ አሰሯት በመጨረሻም ለሕልፈት ዳረጓት ፤
ታላቅ ወንድሙን መሐል እስፓልት ላይ ጥለው በወታደራዊ ተሽከርካሪ(ኦራል) መኪና ሄዱበት ፤ በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉበት ፤ አጥንቱን ለቃቅሞ ቀበረ
እሱንም አሰሩት ፤ ምግብ እንዲቀምስ ብቻ እያወረዱት ከ7ወራት በላይ ጣራ ላይ አንጠለጠሉት፤
ኮልፌ በሚገኘው የደህንነት ግቢ ውስጥ በዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ሰቅለዉት እንዲሰቃይ አድርገዉታል ፤
ጥፍሮቹን በፒንሳ ነቀሏቸው ፤
ዘር እንዳይተካ አኮላሹት ፤
ሴት መርማሪ ፓንቷን አውልቃ በታሰረበት ሸናችበት ፣
ርቃን እየመጣችም መረመረቺው ፤
በስቅየት በደከመበትና በደነዘዘበት ሰአት በቀኝና ግራ አፍንጫው ውስጥ ሹል እንጨት እየከተቱና እየወጉት እንዲነቃ አደረጉት ፤
” ካሁን በሗላ ገንዘብ ምን ያረግልሃል ! ” እያሉና በግድ እያሰፈረሙት ባንክ ያለውን ገንዘቡን እያሶጡ ዘረፉት ፤
የመልካምና የጤነኛ ቁመናና አካል ባለቤት የሆነው ዮናስ አሁን እጅግ ሕሊናን ሊሰብር በሚችል ሁኔታ ይገኛል ። እግሮቹ መሬት አይረግጡም ፣ ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ ፣ የሚንቀሳቀሰው በከፍተኛ ስቃይ በክራንች አንጠልጥሏቸው ነው ፤ ወገቡ በማቀፊያ ተጠቅልሎ (ታቅፎ) ካልሆነ ሚዛኑን መጠበቅ አይችልም ።
በእውነት እነዚህ ሕወሓታውያን ፣ ጌታቸው አሰፋና ልጆቹ  ከምን አይነት ማሕፀን የበቀሉ ቢሆኑ ነው ….. እንኳን በወገናቸው ቀርቶ በጆሮ ለመስማትም የሚዘገንን ይህን ድርጊት የሚፈፀሙት ?….አንድ ጤነኛ ሰው እንኳን በወገኑ በአውሬስ ላይ ይህንን ግፍ ሳያቋርጥ ለመፈፀም እንዴት ሕሊነው እሺ ይለዋል ?
በሴት ልጅ መደፈር አትደነቁ የወጡበትን ማህፀን እንጨት እየከተቱ የሚሳለቁ አውሬዎች ናቸውና
ድርቤ ኢታና ትባላለች ከወንድሟ ከደርጉ ኢታና ጋር ኦነግ ናችሁ ተብለው ነው ከመኖሪያ ቤታቸው የተያዙት
ከድርቤ ጋር ቃሊቲ ስወርድ ነው የተገናኘነው ስለማዕከላዊ ሲነሳ ዛሬም ከአስር ዓመት በኋላ እንደ አዲስ ያንቀጠቅጣታል ጀምራ አጨርስም እያለቀሰች ጥላኝ ወደ አልጋዋ ትገባለች
ድሮ ከወንድሟ ጋር ከቤት ቀጥታ ወደማዕከላዊ ነው የወሰዷት እዛ ትናንት እንዳየነው ፊት ለፊት ያሉት ክፍሎች ሳይሆን ከጣውላ ቤት በታች ግራውንድ ውስጥ ከአራት ወር በላይ በጨለማ ክፍል ለብቻዋ አሰሯት
በዚህ ግዜ ሰው ላይ ይደርሳል ተብለው ሊገመቱ የማይችሉ አረመናዊ ድርጊቶች ተፈፅሞባታል
•በተፈጨ ጠርሙስ ላይ ባዶ እግሯን እንድትሄድ አድርገዋታል
•ጥፍሮቿ ተነቅለዋል
•ጡቷን በኤሌክትሪክ ቶርች ተደርጋለች
• ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ማህፀኗ ውስጥ እንጨት በመክተት ተሰብስበው ይሳለቁባት ነበር
ከዚህ ሁሉ በኋላ ከነ ወንድሟ ሞት ፈርደውባት ወደ ቃሊቲ አወረዷቸው
ድሮ ቃሊቲ መጥታ በቂ ህክምና ማግኘት ስላልቻለች ከሁለት ዓመት በላይ ከማህፀኗ ደም ከጡቷ ደግሞ ፈሳሽ ይፈሳት ነበር
በሴት ልጅ መደፈር አትደነቁ የወጡበትን ማህፀን እንጨት እየከተቱ የሚሳለቁ አውሬዎች ናቸውና
—-
ገመቹ የት ደርሶ ይሆን?
ፌቨን
በዛሬው ዶክመንተሪ ስሙ የተጠቀሰው #ገመቹ፣ የደረሰበት ያልታወቀው #ገመቹ፣ ልክ የሌለው ግፍ የተፈፀመበት #ገመቹ፤ ናዝሬት ሆቴል ተደብቆ አግኝቼዋለሁ፤ ምሳ አቀብዬው ነበር፤ “እኛ ካልሞትን ነፃነት አይመጣም” ይል ነበር ::
“ስለ ገመቹ ስሰማ እውነት አልረባም ወንድሜ በደንብ አስታውሰዋለሁ ናዝሬት ወባ ማጥፊያ ናዝሬት ሆቴል ተደብቆ አሁን ስም መጥቀስ አልፈልግም እራት ገዝተን ስጥቼዋለው ለዛውም ሽሮ ገንዘብ ይዘን መረዳዳት ያልቻልን በሠአቱ አብረውኝ የነበሩት እንደኔ ይህን መርዶ ሲሠሙ ምን ይላሉ ገሜ ትልቅ ልብ የነበረው” ይህ ነፃነት እኛ ካልሞትን አይመጣም” ይለን ነበር በሠአቱ ወደ ሀገሩ ቤተሠብ ጋር ለመደበቅ ሊሄድ በነበረበት ሠአት ነው ። ያን መለሎ በልተውታል ልቤ ተስብራል ።
ምሽቴ ሀዘን ሆነብኝ የት ይሆን የወደቀው? እጅግም ጎበዝ ተማሪ ነበርክ ! ገሜ ላልቅስ ምን እላለው? እውነት ነው አንተ ተሰውተህ እኔ በነፃነት አወራለው ህውሀት ጨካኝ ናችሁ! እውነት ቀንድ ያለው ጭራቅ! ገሜ ልቡ ምን ልሁን? ተቃጠልኩኝ ! ይዘውኝ የሄዱት ልጃች ያለህን እያሣደዱት ነው ብለው ለ20ደቂቃ አውርተናል ወንድሜን ህመሜ ትልቅ ነው እያንዳንዱ ግርፈትህ ስቃይ ልቤ ላይ ጠባሣ አለ ኡፍ ኡፍ ወንድሜን ኡኡኡ ህወሀትይበልጥ ዛሬ ይበልጥ ኡ!
• ብልታችሁ እድሜ ልኩን እንዳይሰራ ቢደረግም
• እግራችሁ ለ3 ጊዜ እንደ አገዳ ቢቆረጥም
• እናታችሁን ወህኒ አስገብተው ቢገድሉባችሁም
• መላ ሰውነታችሁ ነርቩ እንዳይሰራ ሆኖ መቀመጥና መቆም የማትችሉ ቢሆንም
• 7ወር እግራችሁ በሰንሰለት ተንጠልጥሎ ተዘቅዝቃችሁ ብታሣልፉም
• ግብረ ሰዶም ተፈጽሞባችሁ እራሳችሁን
ጠልታችሁ እራሳችሁን ብታጠፉም
• ጆሯችሁ እንዲደነቁር ቢደረግም
• የሴት ማህጸን እንዳይሰራ ተደርጎ እንዲጎዳ ቢደረግም
• እንጦጦ እርቃናችሁን ከግንድ ጋር ታስራችሁ ብታድሩም
 •  7 ወር ከ15 ቀን አንጠልጥለው ሰቀሏችሁም
• ግብረሶደም እያደረጉ ለአካል እና የመንፈስ ስቃይ ቢዳርጓችሁም
• ሴት መርማሪ ራቆትዋን መጥታ ማሳጅ በአካላችሁ እየተሳለቅች ለስቃይ ብትዳርጋችሁም
• የእስር ስቃዩ አልችል ብላችሁ እዛው ታንቆ መሞት ቢደርስባችሁም!
ይህ ሁሉ ስለ ሀገር ስለወገን ሲባል ለነጻነት የከፈላችሁት ዋጋ ነው እናንተ የዛሬ የስቃይ ሰለባዎች የነገ ባለታሪክ ናችሁ።
_____
አዲስ ነገር አልታየም – ግን እንደ አዲስ ያማል 
ነገር ግን ከተፈቱ ሰባት ወር አልፏቸዋል። ካሜራ ደቅኖ ከማስለቀስ እና የፖለቲካ ቁማር ከመስራት ባሻገር ምን ተደረገላቸው?ምንም። ህክምና አላገኙም። እስካሁን እየተለመነላቸው ነው። በልመናው እንኳ ይሄ ነው የሚባል ብር አልተገኘም። ቤት የላቸውም? ብዙዎች ቦታ ቀይረው ከህመማቸው ጋር እየተሰቃዩ ነው። ድጋፍ ሲገባቸው አልተደረገላቸውም። አሁንም የፖለቲካ ንግድ መስሪያ ሁነዋል።
ውጭ ሀገር ሆነው የሰብአዊ መብት ረገጣ ያልደረሰባቸው ና የምናየውን ግፍ ያልተፈጸመባቸው (የችግሩ ዋነኛ ተጠቂ ያልሆኑት) በየቤተመንግስት ሲበሉ፣ ጋርድ ተመድቦላቸው አምስት እስታር ሆቴል ሲንቀባረሩ እነ ዮናስ አይነት የግፍ ሰለባዎች ስቃይ ላይ ናቸው ። ማንም ዞር ብሎ አላያቸውም።  የሰው እጅ እያዩ ነው። ሰው ደግፎ መጸዳጃ ቤት እየወሰዳቸው ነው።
አሁን የበላይ የስልጣን ሃይል በእጃቸው ያስገቡት ይህ እንደሚደረግ አያውቁም ነበር? ያውቃሉ። ያኔ ‘ስልጣን ስለሌላቸው’ አላስቆሙም እንበል። ዛሬስ? ምንም አላደረጉላቸውም። ተቃዋሚዎች እንኳ ትዝ አላሏቸውም።
አሁንም ፍትህ ቢቀር መንግስት ቢያንስ ቢያንስ ህክምናቸው ይቻል። ማረፊያ ቤት ይስጣቸው። እልፍ አማራ እና ኦሮሞዎች የችግሩ ሰለባ ናቸው። ያልሰማንላቸው ለመናገር ያልፈለጉ!!
የቴሌቭዥን ጣቢያውን አሸባሪ እያለ ሲሳለቅባቸው ነበር። ዛሬ መንግስት ቀይሮ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆነ። ለዚያ ድርጊቱ ይቅርታ ጠይቋቸው ይሆን?
Filed in: Amharic