>
11:19 am - Sunday May 22, 2022

‘’የበረከት ስምኦን የጣረ ሞት ቁልቁለት!!! ’’ (መላኩ ከበደ)

‘’የበረከት ስምኦን የጣረ ሞት ቁልቁለት!!! ’’

 

መላኩ ከበደ

 

ፍርሀቱን በጨካኝነት ካባ ሸፍኖ በህወሀት ጓዷ የሚልከሰከሰው አዲሱ ለገሰ!

ኢህኣፓን በመሰሪ ስራዉን ያፈራረሰ  ኣምበርብር ፣ሕወሓትን በምላስነት የሚያገለግል ኣፈቀላጤው ጆሴፍ ጎብልስ ወደ ማይቀረው መዳረሻ እየዋሸ ሊዘልቀው ነው፡፡

ኣቶ በረከት ስምኦን  ኣይደለም በሕወሓት ቤት ራሴን ጠፍጥፌ ያነፅኩት ፓርቲ ነው ብሎ የሚፎክርለት ብኣዴን የኣሁኑ አዴፓ ተፍቶ  እንዳባረረው  ግልፅ ሆኖ ሳለ ‘’ጅብ ያለ ሃገሩ ሄዶ ቁርበት ኣንጥፍሉኝ ኣለ‘’ የሚባለዉን ተረት እዉን ሊያደርገው ለራሳቸዉም መግብያና መዉጫ ካጡ ሙታን መሃል ለመደበቅ የሚያደርገዉን ጥረት ዉሃ ኣይቋጥርም፡፡

ኣቶ በረከት ስምኦን የዶክተር ኣብይን ኣመራር ለመተቸት ኣቅሙም ሞራሉም የለዉም፡፡ በረከት ማለት እኮ የሃገራችን ኢትየጵያ  የታሪክ ጠላትዋ ከሆነው ከለገሰ (መለስ) ዜናዊ  መምርያ እየተቀበለ ሃገራችን ለማተራመስ ብሎም ለመከፋፈል 27 ዓመት ሙሉ የዳከረ ነገር ግን ከዉርደትና ሽንፈት ዉጭ ያልተሳካላለት  ተንቀሳቃሽ ሬሳ ማለት ነው፡፡

ላለፉት 27  የእርግማን ዓመታት ኣማራው በብሔሩ ምክንያት ሲጨቆን ፣ ሲታሰርና ሲገደል  የነበረው በነ በረከትና በነ መለስ መሆኑን ግልፅ ሆኖልን እያለ ኣቶ በረከት ግን  ኣሁን ነፃ ለወጣው ብኣዴን የኢትየጵያ ችግር ሁሉ ምንጭ ኣድርጎ ለማቅረብ  የሞከረዉን ምናልባት ኣቦይ ስብሓትና ጀሌዎቻቸው  እንዲታደጉት መማፀኛ ካልሆነ በስተቀር  ኣማራ የረገጠበትን መሬት እሳት እስከሆነበት ድረስ የጌቶችህን ፍቃድ ለሟሟላት የተጓዝክበትን ርቅት ተመልስህ ብታስበው  ባፈርክ ነበር ፣ ነገር ግን የሞኝ ሰው  ክብሩ ዉርደቱ ሆነና ትላንት የገደሉን ሕወሓቶች ዛሬ ተገልብጠህ  ንፁሓን እንደጲላጦስ እንደሆኑ ፣ ለዉጦች በሕወሓት እንደተቀየሰ ለማስመሰል  ያደረግከው ዲስኮር ‘የኣመል እንጂ የገንዝብ  ድሓ የለም’ እንዳለን ወጣቱ ቴዲሻ እዉነትም ቀጣፊ ባሕሪህን እንደተነሳብክ ልናሳስብሕ ወደድን፡፡

በረከት ሆይ!

የስበሰባ ጥማትህን ማወራረጃ ያደረግከው የመቀሌው ዲስኮር የክስረትህና የሽንፈትህ ምልክተ እንጂ ኣንዳችም ሃገራዊ ፍቅር የሚባል ነገር የለህም፡፡ ትላንት ያልነበረህን ዛሬ ኬት ታመጣዋለህ፡፡ተበታትና ማየት ለምትናፍቃት ኢትዮጵያ እግዚኣብሔር በመረጠ መሪ እጀ  ገብታለች፡፡ትላንት በናንተው ዘመን የምትጠሉት ህዝብና የምትጠልዋት ሃገር እጀ ገብታ በነበረችበት ወቅትም በፈጣሪ ልዩ ጥበብ ኣልፈረሰችም፡፡ከነ  ሙሉ ክብራ በመዳፋችን  ስር ገብታለች፡፡ምናልባት በህይወት ዘመንህ የምትቆጭበት ኣጋጣሚ  ሳይሆን እንደማይቀር ከእብደትህ እያየነው ነው፡፡

ኣንተና መሰሎችህ ልዩ ችሎታችሁ ማበጣበጥ ፣ ሃገር ማፍረስና እርስበራሳችን ማባለት ብቻ ነው፡፡ከዚሁ ዉጭ ለመልካም ነገር ኣልታደላችሁም፡፡ የኢኮኖሚ ፣ ፓለቲካዉና ማሕበራዊ ዕድገት ያልከው የቱ ነው? እነ ስብሓት ነጋ የወጡት ከፍታ ወይስ እኛ ኢትዮጵያዊያን የተዘፈቅነው ዕዳ ? እነ ክንፈ ዳኘው የዘረፉት ሃብት ወይስ መሬት የመታው የህዝብ ድህነት ? የቱ ነው ኣምበርብር፡፡

ኣንተኮ ትግራይ ኣይደለህም ፣ኣማራም ኣይደለህም ፣ኦሮሞ ፣ደቡብ ፣ ዓፋር ጋምቤላ  ፣ሶማል ሃረሪ ባጠቃለይ ኢትዮጵያዊ ኣይደለህም፣ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን እርሰ በራሳችን እንድንገዳደል ኣድርገሃል፡፡የገዛ ሃገርህ ኣርትራና ፕሬዝዳንትዋን ኢሳያስ ኣፈወርቅን ከምትተች ምን ኣለበት ትላንት በዉሸት  ያሰርካትን  ኤርትራ ትዉልድ ኣገርህ ዛሬ በነጋላት ፀሓይ ተጠቅማ ህዝቦችዋን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለማላቀቅ በምታደርገው ትግል ድርሻህን ብትወጣ ?ትላንት በገዛ ወንድሞችህ ፣ በገዛ ቤተሰቦችህ ኣቅፋ ላኖረችው ኤርትራ የዓለም ጭራ ለማድረግ ከወያኔዎች ተመሳጥረህ ወገብህን እስኪቀጥን ላይ ታች ያልክበትን ኣካሄድህ ኤርትራዉያንም የሚረሱት እንዳይመስልሀ? እንዴት ብለው ይረሱታል፡፡ በህይወትህ ሶስት ሰዎች እንዳትረሳ ይላል፡፡ ኣንደኛው በችግርህ ግዜ የደረሰልህ ሰው ፣ሁለተኛው ችግር ዉስጥ የከተተህን ሰው ፣ ሶስተኛው በችግር ግዜህ ጥሎህ ለሄደ ሰው፡፡ ኣንተ  ለወንድሞችህ ለኤርትራዉያን ‘ችግር ዉስጥ የከተትካቸው ሰው ስለ ሆንክ ’ መቼም ቢሆን ኣይረሱትም፡፡ ኣንተ ከሃዲ ነህ፡፡ ወንድሞችህ ክደሃል ፣ቤተሰቦችህ ክደሃል ፣ሃገርህም ክደሃል፡፡ ኣንተ የክህደት ጌታ ነህ፡፡ኣንተ የስምህ ተቃርኖ በረከት ሳትሆን እርግማን ነህ፡፡

በረከት ሆይ!

ኣማራ በየመንገዱ በወጣበት ሲቀር ፣ደሙ ደመከልብ ሆኖ በየመንገዱ ሲፈስ ፣መግቢያዉና መዉጫዉን ሲጠብበት በዚያን ግዜ  ኣንተ  በኣማራ ስም  የተደራጀዉን ፓርቲ ብኣዴን ሊቀ መንበር ሆነህ ትመራ እንደነበርክ የቅርብ ግዜ ትዉስታችን ነው፡፡ እየመራህ ታስገድለን ነበር፡፡ ነብሰ ገዳዮች ቤታችን እየመራህ ኣምጥተህ ታስገድለን ነበር ፡፡ ቋንቋ እንዳይቸግራቸው ኣስቶርጋሚ ሆነህ ኣስገደልከን፡፡ ኣለን የምንለው ባሕለዊ ትዉፊቶቻችን በሙሉ ኣወደምከው፡፡ በምትመራው ህዝብ ጨከንክ፡፡ ግነ ለምን ኣቶ በረከት ? ለምን ይህን ሁላ ጭካኔ በኣማራ ላይ እንዲዘንብ ፈቀድክ ? ምን ያስቀመንህ ነገር ቢኖር ነው እንደዚሁ ለጠላት ኣሳልፈህ የሰጠሀን? ‘ኣማራ ጠላቴ ነው ብሎ ከተነሳ ወንበዴ ’ተባብረህ  ኣስጨፈጨፍከን ? ‘ኣማራና ኦርቶዶክስ ዳግም ላይነሱ ኣከርካሪያቸዉን ሰብረናቸዋል’ ብሎ ህልዉናችን ከሚፈታተን ድርጅት በስማችን ገብተህ ለምን ኣማራ የጣረሞት ማዕከል እንድትሆን ፈቀድክ? ይህንን ምጠይቅህ ለነብስ መንገድ እንዲሆንህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እኛ እነደሆነ  ባንተ ኣንጀታችን ጨክኖዋል ፡፡ ይህ ማወቅ ኣለብህ ፡፡

ኣቶ በረከት በመቀሌ ላይ ያነሳሃቸው ቃላቶች ታስታዉሳቸዋለህ ? ‘ኣዲሲቷ ኢትዮጵያ  በፖለቲካ ፣በኢኮኖሚው እና ማሀበራዊ መስከ የምታስጎመጅ ፣ባለ ከባድ ሚዛን የኣፍሪካ ነብር ነበረች’ብለሀናል፡፡ ጥሩ፡፡

በናንተው የስልጣን ዘመን የምታስጎመጅ ኢትዮጵያ ያየ ሰው ይኖራል ? ምናልባት ግለሰቦች ታስጎመጃቸው ነበረች፡፡ ስለ ሚጎመጁም ስልጣን በእግዚኣብሔር እሰከመነጠቅ ደረሱ፡፡ ከስልጣን ላለመነሳት ንፁሃንን ገደሉ ስለ ጎመጁ፡፡ ሚልዮኖች በየቀኑ በሚያለቅሱባት ሃገር ታስጎመጅ ነበር ያልከን ለሌቦች ለሙሰኞች እንጂ ለኛማ በገዛ ሃገራችን ሲኦል ሆናብን ነበር፡፡

ነብር ነበረች ብለሓል!

የናነተው ነብር እኮ  በግ ለሆነው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ኣንቃ ገድለዋለች፡፡ ያንተው ነብር በዝርፍያ የተሰማራች ፣ ግብረሰዶማዊ ፣ብልት የምታኮላሽ ፣የዘር ፍሬን ቀጥቅጣ መሓን የምታደርግ ፣በወንዶች ፊት ሽንትዋን የምትሸና  ልጃ ገረድ የፈጠረች ኣዉሬ እኮ ናት፡፡ያንተው ነብር እኮ ብሔር ለብሔር የሚያጋጭ ፣የሚበልጠዉን የሚያሳድድ ፣ ሓይማኖተ ቢስ ጭራቅ እኮ ነው፡፡

ያንተው ባለ ከባድ ሚዛን  በሰነዘረችው ቡጢ የሰው ልጅ መንጋጋ የሚያጣምም  ጥርሱን የሚያወልቅ ፣ቀና ባልንበት ሰዓት ኣነገታችንን ያስደፋን ፣ በገዛ ሃገራችን የናንተው ከባድ ሚዛነ መቋቋም ኣቅቶን ገሚሶቻችን ለስደት ገሚሶቻችነ ደግሞ ለሞትና ከባደ ኣካላዊ ጉዳት ኣድርሶብናል፡፡

በኣሁኑ ሰዓትና በኣሁኑ ስርዓት ከመለስተኛ ግጭቶች በዘለለ ኣገራችነ ሰላም ናት፡፡እኛ ለሃገራችን ኣለንላት፡፡ ለኢትዮጵያ ትግራይ ፣ኣማራ ፣ዓፋር ፣ኦሮሞ ፣ጋምቤላው ፣ ደቡቡ ፣ሶመሌ ፣ሃረሩ ፣ባንሻንጉሉ ኣለንላት፡፡ ኣንተና ግብረኣበሮችህ ግና ማንንም ብሔር ኣትወክሉም፡፡ኣሁን  ያጠራቀማችሁት ገንዘብ እስኪያልቅባቸሁ እረሰበራሳችን ገንዘባችሁ ተጠቅማችሁ እያባለችሁን ነው፡፡በረከትና ወንድሞቹ ዕድሜ ይስጣችሁ እንጂ ሰላማችን በሺ እየተባዛ ዕድገታችን  ከከፍታ ወደ ከፍታ እየተሸጋገረ በዓልም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሃገር እናደርጋታለን፡፡

ቅናት የትም ኣያደርስም፡፡ እናንተው ብር ይዛችሁ ዶክተር ኣብይ ህዝብን ይዞ በቅናት ኣቃጠላቹ፡፡ ተንኮልና ምቅኝነት እንደካሮት ወደታች ያወርዳችሃል እንጂ የህዝቦችዋና የሃገራችንን ኢትዮጵያ የቁልቁለት ጉዞ ኣክትሞዋል፡፡

” የወንድ ሜን ደም እበቀላለሁ” ብሎ ገብቶ አሽከር ሆኖ የቀረው በረከት!
 
የበረከትን ታላቅ ወንድም ትሓት  አባል የነበረ  በስብሃት ነጋ ትዕዛዝ እንደ ዶሮ አራውጠው እንደፍየል አስጩኸው ነበር የረሸኑት በረከት የወንድ ምን ደም እበቀላለሁ ብሎ ገብቶ ነው አሽከር ሆኖ የቀረው!
  በረከት እድሜ ልኩን የመለስ   ዜናዊ  አገልጋይ አድር ባይ ከነ ስብሃት ነጋ በላይ ሕወሓት ነው ።
ፍርሀቱን በጨካኝነት ካባ ሸፍኖ በህወሀት ጓዷ የሚልከሰከሰው አዲሱ ለገሰ!
 
  ሕወሓት በተኮሳት ቁጥር በረከት ስምዖን እና አዲሱ ለገሠን  ነው የሚያስነጥሳቸው ፍቅር እስከመቃብር እንዲሉ ይመስላል የበረከት እና የአዲሱ ባሕርይ  አንድ ነው  በረከት የሕወሓትን  ሤራ ጎንጉኖ የሚያቀርብ ሲሆን  አቃጣሪ እንስትም ይመስላል ።
  አዲሱ ለገሠ ፈሪ ግን ጨካኝ በወገኑ ላይ
 የሕወሓት የአፈና መዋቅርን ተቋም  በበላይ  ሁኖ የሚመራ   መለስ ከሞተም በኋላም የቀጠለበት ” “አማራውን በተመለከተ ለኔ ተውት” የሚል ከኢህአፓ ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ቆላ አሙሲት መቀመጫውን አድርጎ ያገር አውራ አዛውንቶችን እያደኑ የጨረሱበትን እኔ ራሴ ምስክር ነኝ አዲሱ ለሕወሓት  የአማራ ጭፍጨፋን  በሞዴልነት ያቀረበው ምዕራብ ሐረርጌን ነው ተወለድኩበት በሚለው ቀዬ
የሕወሓት ተለጣፊ  ሁነው የበታችነቱ የሚሰማቸው ትግሬ አይደለንም አይቀበሉንም ብለው ካሰቡ  የመጡበትን ባደጉበት አካባቢ የተወለዱበትን የአማራ ምድር አሳለፈው ምድሩን ለገፀ በረከት ሕዝቡን በደንቃራነት ለሕወሓት ገብረዋል።
በረከት እና አዲሱ ለገሠ  ክንፈ ገብረ መድህን የወገራ አውራጃን ለትግራይ  ልዩ ምዕራባዊ ዞን   ( የልማት ኮሪደር)  ተብሎ የሚጠራውን ለሕወሓት ያስረከቡት እኒሁ  ናቸው  ሌሎችም ቢኖሩ ዋነኛዎቹ ናቸው።

ታለቁ ቅዱስ መፅሓፍ እንዲህ ይላል

‘’ሙታን ሙታንን ይቅብርዋቸው ዘንድ ተዋኣቸው’’

እኛም ከሙታን መንደር ህያዋንን የምናፈላልግ ሞኞች ኣይደለንም

‘’ሞት ለጨቋኞች’’

‘’ It is founding of black cat in a dark room where the cat is not there’’[

Filed in: Amharic