>
10:48 am - Thursday July 7, 2022

መቀሌ ሀገር ሆናለች! - በውድቀት ዋዜማ ላይም ትገኛለች!!! (አዲስ ፋሽን መጽሄት)

መቀሌ ሀገር ሆናለች! – በውድቀት ዋዜማ ላይም ትገኛለች!!!
አዲስ ፋሽን መጽሄት
በፖለቲካ እይታ
ገና ወደ መቀሌ ስትገባ አስጨናቂ ፍተሻ ይጠብቅሀል። የማትጠየቀው ፓስፖርት ብቻ ነው። አዲስ ሰው ከሆንክ “ከየት ነው የመጣኸው? ለምን ሥራ ነው የመጣኸው? እስኪ መታወቂያ” …. በቃ ምን አለፋችሁ የሀገራችን ክልል ሳይሆን ሌላ አዲስ ሀገር የምንገባ ነው የሚመስለው።
ሰሞኑን በትግራይ ክልል ከአላማጣ መቀሌ፣አዲግራት፣አድዋ፣ አክሱም፣ሽሬ እንደስላሴን አልፌ ተከዘኔን አቋርጨ በሊማሊሞ አማራ ክልል እስግገባ በነበረኝ ቆይታ የታዘብኩትን በአራት እይታ ከፍየ ላቅርብ. ( በሚዲያ፣በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በሕዝቡ ሁኔታ)
ወደ ሰማእታት ሀውልት ዝቅ ብሎ የሚገኘው ዋን ፕላኔት ሆቴል የህወአት ታዳኝ አውሬዎች ገዳማቸው አድርገው የሚዶሉቱበት ስፍራ በመሆኑ ሲቪልና ሚሊቴሪ በለበሱ ጠባቂዎች ታጥሯል። በዚያ ስታልፍ ግልምጫውና ክትትሉ የጉድ ነው……እኔ እስር ላይ እንዳሉ ያህል ነው የተሰማኝ። እስር ማለት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እና ሰው በነፃነት መንቀሳቀስ አለመቻሉ በመሆኑ።
የመቀሌ ነዋሪ በእጅጉ ሽብርና ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው። ኢትዮጵያ እየፈረሰች ትግራይ ብቻ ሰላም ሆኗ ያለች መሆኑን እርግጠኛ ሁነው ያወሩሀል። ይህ ብቻ በቂ ነው ሌላ ቦታ አተራማሿ ህወአት ስለመሆኗ ምንድነው ከተማው ድባቡ ብለህ ከጠየክ ትግሬና አማራ ተጣልተው ይሉሀል። ልብ አድርጉ አሁንም ህዝብ ለህዝብ ጦርነት ፈጥረው ህወአት ነፃ ልትሆን የዘየደችውን ዘዴ የሕወሃት ታማኝ ካድሬዎች በየቀበሌው ዘመቻ ወርደው ግልፅ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ “ንቁ ፣ አማራ ዳግመኛ ሊጮቅናችሁ፣ መሬታችሁን ሊወስድ ነው፣ ስለ እናንተ ከህወአት ውጭ ማንም ሊሆናችው አይችልም” በማለት ከፍተኛ የወንጀል ሥራ ሕዝብ ለሕዝብ ለማጋጨት ሴራ ተጀምሯል። መቀሌ በህወአት ጭፍራ ፖለቲከኞች ሽብር እየተነዛባት በተዘረፈ ብር እየጠጡ፣ በቃ ስድብ ነው የምትሰማው። ዶ.ር አብይ እዚያ ስሙ ደንቆሮ መሪ የሚል ነው።
ልብ አድርጉ ፣ ምእራባውያን ሳይቀሩ ፀሀይ በምእራብ የመውጣት ያክል ነው፤ ልዉጥን ይመጣ ያሉለትን መሪ፣ አንድ እንከፍ እራያና ጊዮርጊስ ቢራ ይዞ አፉን ይከፍታል፡፡
በጣም የገረመኝ ይህ በተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የማንነትና ወሰን ማስከበር አጥኝ ቡድን ሥራ ጀምሯል ቢል ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በቃ ትፈርሳለች ማለት ነው እየተባባሉ የአቋም መግለጫ ሲያወጡ ፣ የህወአት ጭፍሮች በየ መጠጥ ቤቱ ሲዝቱ መስማት የተለመደ ነው። እንኳን ለኢትዮጵያ ቀርቶ ከኤርትራ ጦር መንጋጋ ያወጣቸው የኢትዮጵያ ወጣት መሆኑን ዘንግተውታል።
በጣም የሚገርመው ገና ሽሬ ገብተህ ከመቀሌ መጣው ስትል፣ “ምን ሌቦች ሀገር ዘርፈው ተደብቀው ህዝቡን ያሰድባሉ፣ እነዚህ ውሾች ” ይሉሀል። እውነትም የኃየሎም አርአያ ልጆች …….ከህወአት ውጭ መንግስት የለም አይኖርም የሚለው ደግሞ ሲሞግትና በዚህ ደንቆሮ መሪሽ አንመራም በማለት የህወአትን ጨው እየላሰ የሚያላዝን ጋለሞታ ታያለህ።
ፍተሻዉና ትርምሱና ውክብያው ግን መቀሌ ላይ ያበቃል። ወጣ ስትል ሕዝቡ በፀጥታ ሲወጣ ሲገባ ስታይ ያስቅናል። መቀሌ ላይ በየ ቅያሱ ትፈተሻለህ። በየሰአቱ ፈንጅ ተያዘ እየተባለ ህዝቡን እያሸበሩት በቃ የፖለቲካ ከተማ ሆኗል። ህወአት ለራሷ ነገ ትታሰር ከነገ በስትያ ተቦቃብቃ ሕዝቡን እያሸበረች ነው ቱ……ቱ…….እንዲህስ ሆነው ከሚኖሩ ለምነው ቢታሰሩ ይቀላቸው ነበር። ሽንታሞች ወንድ ሁላ አይመስሉህም።
ብቻ ምን አለፋችሁ የትግራይ ህዝብ በተለይ መቀሌ በወሮበላ ባልተማሩ ሆድ አደር ፖለቲከኞች ውጥረት ውስጥ ትገኛለች።
በኢኮኖሚ እይታ
እንደሚታወቀው ልክ እንደ እሩስያ መቀሌ ገዝቶ ከሚበሉት እንጅ አምርቶ ከሚሸጡት ተርታ አትሰለፍም። የወልድያ፣ጎንደር መንገድ በመዘጋቱና ዞሮ በአፋር በኩል በመግባት በመቻሉ ባይታጣም፣ በውድም ቢሆን ታገኛለህ። ሽሮ ከ40 እስከ 50 ብር በጣም ዝቅተኛ የተባለ ቤት በልተህ ትከፍላለህ። 1ቢራ 17 ብር ጀምሮ 1ሊትር ውሃ 14 ብር ትከፍላለህ።
በተቃራኒው ተከዜን እልፍ ብለህ አማራ ክልል ስትገባ ሽሮ 25 ብር ብቻ ትከፍላለህ። ቢራ በ13 ብር 1ሊትር ውሃም በ10 ብር ትገዛለህ።
ግን ይህ ለምን ሆነ ብለህ መቀሌዎችን ስትጠይቅ “ያ ደንቆሮ መሪ ወደ ኤርትራ እንዲጫን ፈቅዶ ነው” ይሉሀል። የቢራ ማከፋፈያዎች ግን ዋጋ አለመጨመራቸው እየታወቀ ህወአት መሀል አገር ላይ ስታደርግ እንደነበረው ህዝቡን በኑሮ ውድነት እያስመረሩትና ለውጡ ያናጋው ለማስመሰል የዘየዱት መሆኑን ትገነዘባለህ።
መቀሌ ላይ ባሉት የንግድ ቤቶች በVAT ደረስኝ የሚገበያይ የለም። የትኛውም ሆቴል በልተህ ጠጥተህ ስትከፍል ያለ VAT ደረሰኝ ነው። ምነው እነ ህገ መንግስት፣ህግ ይከበር ምናምን ይህን የሀገር እድገት ግብር የዜግነት ግዴታ መሆኑን ዘነጉትሳ ? ገቢዎች ሆይ ከወዴት አለህ?
መቀሌ ከተማ ከሮማናት አደባባይ ቁልቁል ወርደህ ወደ ቀኝ ታጥፈህ ቀጥታ ስትሄድ፣ የማይጨው ጫት ተዘጋጅቶ አንዱ እስር በ200 ብር ሂሳብ አንድ ሚኒባስ ላይ እውስጡና ከላይ 200 እስር ጭና 40 ሺህ ብር ድረስ ከፍለው ወደ አስመራ ይጭናሉ በል እንግዲህ ወዲ አፎም ንቃ ህዝብን ሳያደንዙት በሱስ የመቀሌ ንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ ተዳክሟል።
እኛ ያረፍንበት ሆቴል ወደ 30 መኝታ ኖሮት በቀን ብዙ ካከራየ 5 ወይም 6 መኝታ ብቻ ነው። ባለቤቱ ምሬታቸውን ሲገልፁ ሌቦች ሰርቀው መተው በተደበቁት እኛ እንቸገራለን አሉን። ወዳጄ ድሮ በህወአት አስገዳጅነት ለ1ቀን ስብሰባ ሀገር አቋርጠህ እዚያ እንድትሰበስብና ብርሃን እንድታፈስ ትገደድ ነበር አሁን ወፍ የለም
በደህናው ግዜ ምግብ ለስራ በማለት በትንሽ ስራ ብዙ እየከፈሉ ህዝቡን አስተኝተው በመቀለብ ድህነትንና ልመናን እንዲለማመድ ህወአት አድርጋ አልፎ አልፎ ትንሽ የሙከራ መሳይ ሰብል እርሻ ላይ ልታይ ትችላለህ ይህ ደግሞ ኢኮኖሚውን በእጅጉ ይጎዳዋል የመቀሌ የንግድ ጡዘት የዋጋ ንረት ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን ሳይ ለካ ህዝቡ መልሶ መልሶ ሰልፍ ሰልፍ የሚለው ይህ ጡዘት አማሮት እንደሆነ መገመት አያዳግትም።
በሚዲያ እይታ
በትግራይ ክልል መቀመጫቸውን መቀሌ ያደረጉ ወደ 4 የሚደርሱ የቴሌቪዥን ጣቢያዋች አሉ ሥራቸው ህዝብን ለአመፅ መቀስቀስ፣የጦርነት ሙዚቃ መክፈት ፀረ-አብይ፣ ፀረ -ለውጥ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ በቃ ግልፅ ስድብ አስቡት ምን ያህል ወጭ ለእነዚህ ሚዲያዎች ክልሉ ከመንግስት ካዝና እየከፈለ ጋዜጠኛ አይሏቸው መሀይሞችን ቀጥሮ ብር ያፈሳል ለፕሮፖጋንዳ ህዝቡ ድግሞ በሌላ መልኩ ሲቸገር ስታይ ያስቅሀል ኢሳትን ኢቲቪን መክፈት እንደ ነውር የሚቆጥርበት ነው አልፎ አልፎ ህወአት ጠል የሆኑና የነሱ ፕሮፖጋንዳ የሰለቸው ኢቲቪን ከፍተው ይሰማሉ
በመጨረሻም ዶ.ር አብይ የትግራይን ህዝብ ከእነዚህ መሰሪዎች ነፃ አውጣቸው እኛ ያየነውን ነፃነት አሳያቸው ህዝቡን አደናግረውታል መጥፎ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ሳይከቱት ዶ.ር ልትደርስላቸው ይገባል። ሰፊው ሕዝብ በጥቂት ሆዳም መሀይሞች ተጋርዷል መጋረጃውን ቅደድላቸው።
ለትግራይ ፀልዩላት – ( ትግራይን ከጎበኘ ዜጋ)
Filed in: Amharic