>

"ትግራይ ትግርኚ" የምትባል አገር የመመስረት ክፉ ቅዠት!!! (ናትኤል አስመላሽ)

“ትግራይ ትግርኚ” የምትባል አገር የመመስረት ክፉ ቅዠት!!!
ናትኤል አስመላሽ
 
መ/ር ገብረኪዳን እና  ኤርትራዊው ተስፋጽዮን
ህወሓት ከስልጣን መባረርዋ አይቀሬ መሆኑ ስታወቅ፣ የተንኮል አባት አቶ ስብሓት ነጋ፣ አግአዝያን የሚባል ድርጅት በድብቅ መስርተው ነበር። የዚህ ቡዱን ዋና ተልእኮ፣ ትግርኛ ተናጋሪ የትግራይ ተወላጆች እና የኤርትራ ተወላጆች አንድ አገር እንዲመሰረቱ እና ከፊል የኤርትራ መሬት እና የትግራይ መሬት ለሁለት በመሰንጠቅ፣ ትግራይ ትግርኚ የምትባል አገር መመስረት ነው።
በትግራይ በኩል
አድዋ፣ሽሬ፣አኽሱም፣ዓድግራት
በኤርትራ በኩል
ሓማሴን፣ሰራየ፣ አኮሎጉዛይ
ከትግራይ በኩል እንደርታ፣ራያ፣ማይጨው፣ እና ከእንደርታ ቦሃላ ያሉት እዚህ ውስጥ አይገቡም፣ ምክንያቱም እነሱ ትግርኛ ተናጋሪ ተብለው ስለማይታሰቡ እና፣ ስሜታቸውም ከትግራይ ይልቅ ለኢትዮጲያ ስለሚቀርብ ነው ብለው ስለሚያስቡ ነው። ለምሳሌ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ የትግርኛ ንግግሩ እንደ መ/ር ገበረኪዳን እና ኤርትራዊው ተስፋጽዮን አባባል አማርኛ ይበዛበታል ብለው ስለሚያስቡ፣ ወይንም ደግሞ ጥርት ያለ ትግርኛ ስለማይናገር ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው። ተስፋጽዮን የማነ ናግሽ ትግርኛ አይናገርም አይችልም ሲል በተደጋጋሚ ተናግረዋል። https://www.facebook.com/story.php?story_fbid=10210110357379718&id=1361304503
ወደ ዋና ነጠብ ስንመጣ፣ ስብሓት ነጋ ህወሓት መውደቋን ስለገባው፣ በልጁ አማካኝነት፣ እስራኤል አገር ውስጥ የመጀመርያው የአግ አዝያን ስብሰባ አድርገዋል። ይህ ማለት ደግሞ፣ ከኤርትራ በኩል ሻዕብያን በማጥላላት በተለይ ደግሞ እስላም ወንድሞቻችንን በማጥላላት፣ የተረት ተረት ታሪክ በማምጣት፣ ሻእብያን ማዳከም፣ ከዛም አልፎ ከተሳካ፣ሻእብያን ከስልጣን ማውረድ እና፣ ትግራይን  ገንጥሎ፣ ምስራቅ አፍሪቃ ውስጥ አንዲት የትግራይ ትግርኚ አገር መፍጠር ነበር። ይህ ሳይሳካ ቀረ፣ ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረዉ እስላም ክርስትያኑ ማለያየት አልቻሉም።
አሁን ፎትውን ተመልከቱት አንደኛው ለክፋት የተፈጠረው መ/ር ገብረኪዳን ነው፣ የመ/ር ከብረኪዳን ዋና ተልእኮ የአጼ የውሃንስ ታሪክን በማንሳት፣ ምኒሊክ የትግራይ ህዝብ ዋና ጠላት እንደሆነ ለአዲሱ የትግራይ ትውልድ ታሪክ ማስተላለፍ እና፣ ኢትዮጲያ የምትባል አገር እንደ ጠላት እንዲቆጥር ማድረግ። ከዛም አልፈው አንቀጽ 39ኝ አሁን መተግበር ያለበት አንቀጽ ነው በማለት የትግራይን የመገንጠል መብትዋን እንዲከበር ህዝቡን ማሳመን፣ ማንቃት ነበር።
 ከዛም አልፎ መ/ር ሙሉወርቅ የተባለ ተመሳሳይ ተልእኮ ተሰጥቶት ባለ ታሪክ እስኪመስል ድረስ ድርሰት ደርሶ፣ ተመሳሳይ መልእክት ማስተላለፍ ወጣቱን ማሳመን ነበር። የትግራይ ህዝብ ዋናው ጠላቱ ህወሓት ሆኖ እያለ፣ የተረት ተረት ታሪክ ፈጥረው፣ ወይንም ደግሞ የዛሬ መቶ አመት ታሪክ አስታውሰው፣ የትግራይ ወጣት ጸረ ህወሓት እንዳይታገል በተቻላቸው መጠን ሰርተዋል ግን አልተሳካም።
በነገራችን ላይ መ/ር ሙሉወርቅ የአጼ የውሃንስን ሃወልት ለማሰራት ለስብሓት ነጋ ሲነግረው፣ ስብሓት ነጋ እንዲህ ሲል መልሶለታል፣ “የትግራይ ህዝብ ታሪክ የሚጀምረው ከደደቢት ነው፣ ስለሆነም የኛን ታሪክ ለማጥፍታ ብለህ የአጼ የውሃንስ ታሪክ ከመሬት ለመቆፈር አታስብ፣ ሁለተኛም ይህንን ጥያቄ እንዳትጠይቅ” የሚል ማስፈራርያ የያዘ መልስ ተሰጥቶታል፣ ከዛ ቦሃላ ጥያቄ መጠየቅም የለም፣ የአጼ የውሃንስ ሃወልትም እሳካሁንዋ ሳአት ድረስ አልተሰራም።
ኤርትራዊው ተስፋጽዮን፣ ዋናው ተልእኮው፣ አማራ የትግርኛ ተናጋሪ ህዝብ ዋና ጠላት መሆኑን፣ ትግርኛው ተናጋሪ ወጣት ማሳመን፣ በተለይ ክርስትያን አማኙ ጠላቱ የእስልምና ተከታዮች መሆናቸውን በተደጋጋሚ መንገር፣ እንደምሳሌ ጀብሃን ያነሳል፣ ጀብሃ የክርስትና እምነት ተከታዮች ጠላት እንደሆኑ እና፣ በትግሉ ውስጥ ጸረ ትግርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ይንቀሳቀሱ እንደነበሩ መጻፍ፣መናገር ዋናው ተልእኮ ነው። አማራ ጠንቃይ ነው በማለትም ይናገራል፣ ንግ ግሩ ከዚህ በፊት ለጥፌው ነበር።
በነሱ ሂሳብ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት፣ ትግራይ ተገንጥላ፣ በኤርትራ በኩል ከትግርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ጋር ተደምራ አንድ አገር መፍጠር፣ ከዛም አልፎ፣ ቀይባህር እና ምጽዋእን ድምበር ማድረግ፣ ቀሪው የኢትዮጲያ ህዝብ ግብር እየከፈለ ወደቦችን እንዲጠቀም ማድረግ ነበር፣ አሁን ዶ/ር አብይ ደርግ ነው የሚለን፣ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪም ዋና አቀንቃኝ ነበር። ከጀርባው ስብሓት ነጋ እንዳለ ሲያቅ ጥሎ ወጥተዋል።
መጨረሻው ምን ሆነ? መጨረሻው፣ ህወሓት ተሸነፈ፣ ወዲ አፎምም ከዶ/ር አብይ ጋር ፍቅር በፍቅር ሆነ፣ እነ አግአዝያን ያሰቡት ሳይሳካላቸው ቀረ፣ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ትግራይ ሸሹ፣ ታሰሩ። ፎቶ ይህንን ተልእኮ የተሰጣቸው ትግራይ ተገናኝተው ሲመካከሩ የሚያሳይ ነው። የስድሳ አመቱ የአግ አዝያን አቀንቃኝ፣ እነ መምህር ገብረኪዳን እና መ/ር ሙሉወርክ ልጁን የምታክል የትግራይ እህታችን ድረውታል፣ በትግራይ እህቶቻችን ሳይቀር በነ መምህር ገብረኪዳን እና መምህር ሙሉወርክ ይህን ያክል ግፍ ይደርሳል፣ ጊዜው ሲደርስ ሂሳብ እናወራርዳለን።
Filed in: Amharic