>
5:09 pm - Thursday March 3, 7549

ህውሃት የወንጀለኞች ቡድን ለመሆኑ የወንጀለኛነት መረጃዎች አሉን፤ (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ)

ህውሃት የወንጀለኞች ቡድን ለመሆኑ የወንጀለኛነት መረጃዎች አሉ

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመመንፈሳዊ
 

ያ፡ሳቡ፥ሳቡ፡መጣ፡ወይ፡ደሞ፥

እንዲያ፡ሲርበን፡ሲጠማን፡ከርሞ።

ሳቡ፥ሳቡ፥ሳቡ፡መሸብን፤

የዦቢራ፡እራት፡ግብር፡አለብን።

ስንኳን፡ዐሽከሩን፡ፈረሱን፡ከፋው፤

ሠርክ፡የደም፡ሸማ፡እያስከረፋው። ሕዝብ  ግለሌ። (ከግል፡ማኅደር፡የተቀዳ)፡

በምንም  ሆነ እንዴት የኢትዮጵያ ሕዝብ በዐይኑ ባየው ምክንያት ህውሃት የዛሬ ሃያ ሰባት ዓመታት የመንግሥት ስልጣኑን ያዘ፤”እኔ እንደወታደራዊው መንግሥት አልገድልም፤”የገበሬው ልጆች ነን ብሎ ብዙ ተገዘተ።መጀመሪያ የደርግ መንግሥት ገዳዮችን ከያሉበት ለቃቀመ ፣ጅምላ ግድያዎችን ለመረጃነት እያስቆፈረ ራሱ አስወጣ፤ግፍ የተፈፀሙበትን ቦታዎች እያነፈነፈ አከማችቶ የደርግ ሠይጣናዊ ተግባሮችን በየፈርጃቸው አስቀምጦ ዓለምን አሳየ።የኢትዮጵያ ሕዝብ:-የደርግን የአሥራ ሰባት ዓመታት ጥሩምባ በገዳይነት ደምድሞ አዲስ የሰላም እና የዕድገት ምዕራፍ ተጀመ ብለን ነበር።
               እንደጠበቅነው ሁሉም አልሆነም፤እንደውም የተረገምን እስኪመስለን ከውርደትም በላይ ተንቀንንና ተዋርደን፣በአደባባይ የዓለም ሕዝብ እያየን ሰላሳ ኢትዮጵያውያንን አሳረድን፤ የሚያሳዝነው መታረዳቸው ብቻ አይደለም፤ያገባኛል የሚል መንግሥት  ጠፍቶ “በተጻራሪው አበጁ እንኳን ተገደሉ” የሚል መንግሥት ነኝ ባይ ቡድን ማየቱ ደም-ዕምባ የሚያስወጣ ክስተት አየን።የግፎቹ ዓይነቶች ተዘርዝረው አያልቁም፤ፍናፍንታዊነቱ፣ቤተሰቦችን መበተኑ፣በዘር-አምክን መርፌ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ እናቶችን ማስወጋቱ፣ ከጅምላ ግድያው ጎን የሰዎችን ሬሳ በመሰወርና በየቤተ ክርስቲያኑ የቀብር ቦታዎች በጨለማ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ፣በአደባባይ ሴትና ሕፃናትን ሳይቀር ባነጣጣሪ መሳሪያ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ጭንቅላትን ቦርቅሶ መግደል ፈሪነት  መነ ሺህ ተግባሮች አንዱ ነውቁምነገሩ ግን ከላይ የተዘረዘሩትን ወንጀሎች ጨምሮ የሕዝብ ገንዘብ በሚሊዮን መዘረፉ ሳያንሰን፣ጭልፋና ዘነዘና ሳይቀር ከየፋብሪካዎቹ ጥፍጥሬን ጨምሮ መጅ እንኳ አልቀረም መሳሪያዎቹን እያስነቀሉና ካቻቢቴና ጉጠት እየሰረቁ ሲያግዙ።ለሃያ ሰባት ዓመታት ወንጀሎች ሲፈፅም የነበረን ቡድንም ሆነ የቡድኑን አባል ወንጀለኛ መሆኑን ደጋግመን ብንገልፅም፣በተግባር ሳይወገዝ በዕርቀ-ጉባኤ ሥም  ዕርቁ ዘግይቶ ጉባኤ ሳይደረግ እስከዛሬ ድረስ ምንም አለመደረጉ ሳያንስ ሹመቶች መፈንዳት ጀምረዋል፤አስመላሽ ወልደ ሥላሴ የመጀመሪያው እና ተመላሹ/ቀልባሹ ባለሥልጣን የተሾመ አንዱ መረጃ ነው። 
           ይህ እየታወቀ ለወንጀለኞች እንደአዲስ ሥልጣን መስጠት መጀመሩ የዶክተር ዐቢይ አህመድ ጅማሮ በአቶ አስመላሽ ወልድ ሥላሴ አያበቃምና:-መጀመሩ ወደክህደት ጉዞ እንዳያመራን ሊ.ገ.ታ ይገባዋል፤አለበለዚያ ሕገ-መንግሥቱ ቢኖርም በአንፃራዊነት ሕገ-ሕዝቡን አሁን በውሳኔ-ህዝብ ልናፀድቅ ይገባናል።እስከመቼ ድረስ፣መንግሥት በሕገመንግሥት እያማካኘ የሕዝቡን ነጻነት በመሸራረፍ እንደልቡ በመፈንጨት የፈለገውን ሲሾም እና ሲሽር ሕዝቡ ተመልካች ብቻ ይሆናል?አለበለዚያ በሕገ-ሕዝቡ አናቱን ይቀጠቅጠዋል፤ ይጠልዘዋል።ለነገሩማ፦ዶክተር ዐቢይ አህመድ የጊንጦችን ራስ እንደረገጠልን ተሰምቶን፤ወደ ትንሳኤ አውድማ ተሰባሰብን፤እርሱም በልቡ እግር ከሕዝቡ ጋር ዓለም ተጉዞ በያንዳንዳችን ህሊና ውስጥ ሰርፆ በትዕግስት የጥላቻችንን ስሜት በፍቅር እሳት አቃጠለ ብለን እንጂ፤  ለኢሃድግ ብለን እንዳልሆነ ራሱ ሕውሃት ያውቀዋል የነገም ምርጫችን እሱን ብቻ ይሆናል እንጂ፤እንደተጠቀለለ መርዝ ከውስጡ ህውሃት የሚሉትን የወንጀለኛ ቡድን ይዞ ከሆነ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለቴ ሊያስብ ይገባዋል
           ስለዚህ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሕውሃት በፍፁም አያራምድዎትምና ወደ ሕዝባዊ መንግሥት ምሥረታ ያረማምዱን፤አያሸጋግሩን ምክንያቱም ከብብትዎ ውስጥ ያለው የእባብ መንጋ አንድ ቀን ባገኘው አጋጣሚ ይነድፍዎት ይሆናልና ነው።ለማጠቃለል ለእነ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በትረ-ሥልጣኖችን ማደል ከጀመሩ፣ህውሃት የወንጀለኞች ቡድን ለመሆኑ ማረጋገጫ መረጃዎች ንና  ፤መጀመሪያ በግልፅ ህውሃት ሊወገዝ ይገባዋል።
 
“አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ያዢ።”
Filed in: Amharic