>

የኦሮሞ ገዳ፡ የቀማኞች ዲሞክራሲ (መስፍን አረጋ)

የኦሮሞ ገዳ፡ የቀማኞች ዲሞክራሲ

መስፍን አረጋ

 

ብያኔወች

በዚህ ጦማር ላይ ኦነግ እና ኦነጋዊ የሚሉትን ቃሎች የምንጠቀመው ሁሉንም የኦሮሞ ጎጠኛ ድርጅቶና ግለሰቦች (ኦፒዲኦ፣ ኦዴፓ፣ በቀለ ገርባ፣ ጃዋር ሙሐመድ፣ ሙሐመድ ሐሰን፣ ወዘተ.) በሚያጠቃልል መልክ ነው፡፡ በጎጠኝነት ተጸንሶ፣ ደቁኖ የቀሰሰው የጎጠኘነቱ ሊቅ መለስ ዜናዊ እንዳለው፣ ኦፒዲኦ ፋቅ ቢያደርጉት ኦነግ እንደሆነ ሁሉ፣ ሌሎቹም የኦሮሞ ጎጠኞች እንዲሁ ናቸው፡፡

ብያኔ (definition)፡ ኦነግ ማለት ማናቸውም የኦሮሞ ጎጠኛ ድርጅት ወይም ግለሰብ ማለት ነው፡፡

እንዲሁም በዚህ ጦማር ላይ አማራ የሚለውን ቃል የምንጠቀመው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ በመሳሰሉ ጥበቶች ራሱን በራሱ ሳያጠብ ጦቢያዊነቱን በማስቀደም በመላዋ ጦቢያ ላይ የሚኖረውን አማረኛ ተናጋሪ ጦቢያዊ በሚያጠቃልል መልኩ ነው፡፡

ብያኔ (definition)፡ አማራ ማለት ጦቢያዊነቱን በማስቀደም በመላው ጦቢያ ላይ የሚኖር አማረኛ ተናጋሪ ማለት ነው፡፡

በዚህ ብያኔ መሠረት አማራ በጦቢያ ውስጥ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛውን ኦሮሞን በሚሊዮኖች ይበልጣል፡፡ በሌላ አባባል በጦቢያ ውስጥ አማራ በከፍተኛ ደረጃ ዐብይቶን (majority) ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ንዑስቶኖች (minorities) ናቸው፡፡
ኦሮሞ በጦቢያ ውስጥ ብዙሃን ነው የሚባለው ትርክት (narration) የኦሮሞ ጎጠኞች በመደጋገም ውነት ያስመሰሉት ኦዳ ውሸት ነው፡፡ በምንም ዓይነት ስሌት ኦሮሞ ዐብይቶን ሊሆን አይችልም፡፡
• በፀራማራነት ላይ የተመሠረቱት ወያኔና ኦነግ ያማራን ምድሮችን በመቀራመት ከፈጠሯቸው ልቦለዳዊ (fictional) ክልሎች ውስጥ አንዱ በሆነው ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ የትላልቆቹ ከተሞች ከተሜወች አብዛኞቹ አልኦሮሞወች (non-oromo) በተለይም ደግሞ አማሮች ናቸው፡፡

• ባዲሳባ ከከተመው ኦሮሞ ውስጥ አብዛኛ በኦዲፒኦ ሹሞች አድሏዊ ትብብር በወያኔ ዘመን የከተመ የቅርብ ሰፋሪ ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ ባዲሳባ የሚኖረው ኦሮሞ ጠቅላላ ቁጥር ባንጻራዊ ደረጃ ሲታይ ኢምንት ነው፡፡ በሌላ አባባል አዲሳቤ ኦሮሞ ኢምንት ንዑስቶን (insignificant minority) ማለትም አናሳ ወይም ህዳጣን ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ አዲሳቤ አማራ ጃምንት ዐብይቶን ነው፡፡ ናዝሬት፣ ድሬዳዋ፣ ደብረዘይት፣ ሐረር፣ ጅማ፣ አጋሮ በመሳሰሉት ከተሞችም እንደዚሁ፡፡

• ያማራ ቁጥር እንጦሮንጦስ ወርዶ የኦሮሞ ቁጥር ሰማይ የነካው በወያኔ ዘመን ነው፡፡ ወያኔ ደግሞ የሐብትና የንብረት ብቻ ሳይሆን፣ የታሪክ እና የቁጥር ሌባ መሆኑን መናገር አያስፈልግም፡፡ ማጋነን ሲሻ የትግራይ ሕዝብ ይሄን ያህል ነው፣ ሐውዜን ይሄን ያህል ተጨፈጨፈ፣ አይደር ይሄን ያህል አለቀ፣ ከጎንደር ይሄን ያህል ትግሬ ተፈናቀለ እያለ የሚያጋንን፣ ማሳነስ ሲሻ ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን አዲሳቤ በግማሽ የሚጎመድ፣ ሲዋሽ ዓይኑን የማያሽ፣ በሐሰት ትርክት ተፈጥሮ በሐሰት ለሐሰት የሚኖር ሐሳዊ ድርጅት ነው፡፡

ኦሮምያ የተሰኘው ካማራ፣ ከጉራጌ፣ ከወላይታ፣ ከጉጅ፣ ከሱማሌ ወዘተ በተለጸቁ (annexed) (ማለትም ተነጥቀው በተቀላቀሉ) መሬቶች አለቅጥ የሰፋው ኢፍትሐዊ ክልል በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ሊሆን ይችላል፣ ለዚያውም ከሆነ፡፡ ይህ ማለት ግን ኦሮሞ በቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡ ዐብይን ሙሐመድንና ለማ መገርሳን ጨምሮ ኦነጋውያን የሚጣጣሩት ግን እነዚህን እየቅል እውነታወች በማምታታ ለማታለል ነው፡፡ ጥረታቸው ደግሞ በሰፊው ተሳክቶላቸው አብዛኛውን ጦቢያዊ አታለዋል፡፡

ስለዚህም የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) የመጀመርያ ሥራ መሆን ያለበት የኦነጋውያንን የቁጥር ቅጥፈት በመረጃ ሰይፍ መቅጠፍ ነው፡፡ ኦሮምያ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት፣ ኦሮሞ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ነው ማለት አይደለም፡፡

የቀማኞች ዲሞክራሲ

ቀማኞች ሲቀማኙ ፍቅረኞች ናቸው፡፡ ዓይናቸውን የሚጥሉት በቅምኝቱ ቱርፋቶች ላይ እንጅ በቅምኝቱ ላይ ስላልሆነ፣ ቅምኝቱን ለማሳካት ማድረግ /የሚገባቸውን/ ሁሉ ባንተ ትብስ መንፈስ በሙሉ ስምምነትና ትብብር ያደርጋሉ፡፡ የቅምኝቱን አመራሮች የሚመርጡት ደግሞ የቅምኝቱን ቱርፋቶች አመርቂ ያደርጋሉ ብለው የሚያምኑባቸውን ግለሰቦች ብቻና ብቻ ነው፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ አመራር አባል ደግሞ የቅምኝት ሚናውን በሚገባ ካልተወጣ /የሚጎዳው/ እሱ ራሱ በመሆኑ፣ ቦታውን ከሱ ለተሻለ ግለሰብ ልቀቅ ሳይባል በደስታ ይለቃል፡፡ ማናቸውም የቅምኝቱ ዐባል ደግሞ ቅምኝቱን አመርቂ ለማድረግ ይበጃሉ የሚላቸውን ሐሳቦች የመግለጽ ሙሉ ነጻነት ብቻ ሳይሆን፣ እንዲገልጽም በእጅጉ ይበረታታል፡፡

ቅምኝቱ ከተከናወነ በኋላ ግን አብዛኞቹ የቅምኝቱ አባሎች በቅምኝቱ ቱርፋቶች ክፍፍል ቅር ይሰኙና በቅምኝቱ ወቅት የነበረው ፍቅር ወደ መናቆር ይለወጣል፡፡ በክፍፍሉ እጅግ የተጎዱት በክፍፍሉ እጅግ በተጠቀሙት ላይ መሣርያ እስከማንሳት ይደርሳሉ፡፡ ተጠቃሚወቹ ደግሞ ጥቅማቸውን የሚያስከብር ድርጅት አቋቁመው በዘረፉት ልክየለሽ ሐብትና ንብረት አማካኝነት የበላይነት ይይዙና በሐብታሞች፣ ለሐብታሞች፣ የሐብታሞች የሆነ መንግሥት ይመሠርታሉ፡፡ የዚህ መንግሥት ዋና ሥራ ደግሞ ለግል ሐብት ከሚገባው በላይ አጽንኦት በመስጠት የዋኖቹን ቀማኞች የቅምኝት ቱርፋቶች መጠበቅና ማስጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ መንግሥቱ የሚጠመደው በቅምኝቱ ክፍፍል እጅግም ያልተጠቀሙት የቅምኝቱ አባሎች እድላቸውን እየረገሙ ከፍፍሉን አሜን ብለው እንዲቀበሉ የሚያስገድዱ ሕጎችን በመሐገግና ሕግ አስከባሪውን ኃይል በማጠናከር ነው፡፡ አስገዳጆቹ ሕጎችና ደንቦች እየሰፉና እየጠነከሩ ሲሄዱ፣ በቅምኝቱ ወቅት የሰፈነው ነጻነት እየጠበበና እየተዳከመ ይሄድና በጊዜ ሂደት ወደ ሙሉ አምባገንነት ይለወጣል፡፡
የሆነ ዓላማን ለማሳካት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል፣ ዓላማው ከተሳካ በኋላ ወደ አምባገነንነት የሚለወጥ ዲሞክራሲ የቀማኞች ዲሞክራሲ ይባላል፡፡ የዚህ ጦማር ዓላማ ደግሞ የኦሮሞ ገዳ የሚባለው ሥርዓት ኦነጋውያን እንደሚሉት እውነተኛ ዲሞክራሲ ሳይሆን፣ ባሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለተከናወነው መጠነ ሰፊ ቅምኝት እንዲያገለግል ብቻ በጊዜያዊነት ከተሠረተ በኋላ ቅምኝቱ /ሲገታ/ ወዲያውኑ የከሰመ የቀማኞች ዲሞክራሲ እንደነበር ማስገንዘብ ነው፡፡

የኦሮሞ ገዳ

ኦሮሞ ከመነሻው ፈልሶ፣ በጦቢያ ላይ ተስፋፍቶ፣ ግብርና ተምሮ በቋሚነት ከመስፈሩ በፊት አርብቶ አደር የነበረ በመሆኑ፣ ከኗኗሩ ምንነት የመነጨ ነጻነት የሚመስል መረን ለቀቅነት ወይም ልልነት ነበረው፡፡ ዘላን የተባለበትም ምክኒያት ባሻው ጊዜ ወዳሻው ቦታ ስለሚዘል ነው፡፡ የከብት ጭራ የሚከተል አርብቶ አደር፣ በሬ እንደሚጠምድ አርሶ አደር ጥብቅ ሊሆን አይችልም፣ መሆንም የለበትም፡፡ አርብቶ አደራዊ ኑሮ የሚኖሩ ወይም ደግሞ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ብሔረሰቦች አኗኗራቸው በተወሰነ ደረጃ ልቅ መሆኑን ለመረዳት ያፋሮችን፣ የኢሳወችን፣ የሱማሌወችን፣ የከረዩወችን፣ የቦረናወችን ልቅ አኗኗር ከደገኛው ጦቢያዊ ጥብቅ አኗኗር ጋር ማነጻጸር ይበቃል፡፡

ሙሐመድ ሐሰንን የመሳሰሉ የኦሮሞ ልሂቆች ግን የኦሮሞን ከዘላንነት የመነጨ መረን ለቀቅነት ከዲሞክራሲ ጋር ሥራየ ብለው ያምታቱታል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከሌላው ጦቢያዊ በተለየ መልክ ዲሞክራቲክ ነበር በማለት በብዙ ረገዶች (በስነቃሎች፣ በጽሑፍነክ ትውፊቶች ወዘተ.) የሚሰማቸውን ባዶነት ለመሙላት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ደግሞ ኦሮምኛ የማያውቀው አስመሮም ለገሰ በኦነጋዊ ባልደረቦቹ የተተረጎመለትን የገዳ ትርክት ተሳስቶ (ወይም ሆን ብሎ) ወደ ዲሞክራሲ ትርክት በመቀየር የጻፋቸው ጽሑፎች ያንበሳውን ሚና ተጫውተዋል፡፡

የገዳ ስርዓት የኦሮሞ መስፋፋትና መንሰራፋትን ለማሰለጥ (make efficient) ብቻና ብቻ የተሰረተ የቀማኞች ዲሞክራሲ ነበር፡፡ በሌላ አባባል የገዳ ስርዓት በዲሞክራሲ የሚያምን ሕዝብ የሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሆን፣ በቀማኛነት ለመስፋፋት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ መስፋፋቱ እስከቀጠለ ድረስ እንዲያገለግል የተሰረተ የተስፋፊ ቀማኞች ዲሞክራሲ ነበር፡፡ የገዳ ስርዓት የተሰረተው 1522 ዓ.ም ገደማ (ማለትም በ 1515 የተጀመረውን የግራኝ ወረራ ተከትሎ) እንደነበር ራሱ ሙሐመድ ሐሰን ‹‹ኦሮሞና የጦቢያ ክርስቲያናዊ ንጉሥጌ›› (Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia) በተሰኘው በራሱ መጽሐፍ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ ትክክል ነው፡፡ የገዳ ስርዓት ከኦሮሞ መስፋፋት በፊትም ሆነ በኋላ አልነበረም፡፡ ስለዚህም የገዳ ስርዓት የኦሮሞን ሕዝብ ዲሞክራሲያዊነት የሚያመለክት ልዩ ክስተት ሳይሆን ቀማኞች ቅምኝታቸውን ለማቀላጠፍ የሰረቱት የቀማኞች ዲሞክራሲ ነው፡፡

በቱርክ ነፍጠኞች የተመራው የግራኝ አህመድ ወረራ አማራ የሚባለውን ጀግንነቱ የተመሠከረለትን ታላቅ ሕዝብ ተቋማት ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ እጅጉን አዳከመው፡፡ የሱማሌን ጅራፍ ይሸሹ የነበሩት የኦሮሞ አርብቶ አድሮች ደግሞ ግራኝ የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ባባ ገዳወቻቸው መሪነት ድንገተኛ አደጋ እየጣሉ፣ በሐይማኖቱ ቀናኢ የነበረውን አማራ ስምንተኛው ሺ ደረሰ እስከሚያስብሉት ድረስ ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አዛውንት ሳይሉ በሰይጣናዊ ጭካኔ ጨፈጨፉት፡፡ የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር ነውና፣ የነዚህ አንድም ቀን ፊት ለፊት ተዋግተው የማያውቁ ቱርቂወች ብትር ከግራኝ ብትር የከፋበት አማራ፣ ከግራኝ ቁስል እስከሚያገግም ድረስ ምርጫ ስላልነበረው እጅግ ሰፊና ለም ከነበረው ርስቱ እየተፈናቀለ ከኦሮሞ አደጋ ጣዮች ራሱን በቀላሉ ለመከላከል ወደሚችልባቸው ተራሮች በመሸሽ ዝንጀሮቴኔ ኑሮ ለመኖር ተገደደ፡፡ አደጋ ጣዮቹም አማራውን እግር በግር እየተከተሉ፣ ያማራውን ምድር በየጎሳቸው በመከፋፈል ወረምንትስ፣ ወረቅብጥርስ እያሉ ሰየሙት፡፡ ላኮመልዛ ወሎ፣ ፈጠጋር አሩሲ፣ አንጎት ወለጋ፣ እናርያ ኤሊባቡር፣ ሸምብራ ቁሬ ዱከም፣ በራራ ፊንፊኔ ተባሉ፡፡

አማሮች ነፍጥንና አነፋፈጥን ከፖርቱጋሎች ተምረው ግራኝን አሸንፈው ካገገሙ በኋላ ፊታቸውን ወደ ኦሮሞ ተስፋፊወች አዞሩ፡፡ አደጋ መጣል እንጅ መዋጋት የማይችለው የኦሮሞ ተስፋፊ ባራት ማዕዘናዊ የውጊያ ጥበብ (ፊታውራሪ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች) በተካኑት አማሮች ፊት መቆም አቃተው፡፡ የነፍጥ ድምጽ ሲሰማ ኦቦው ካቦ ሸማኔ ፈጠነ፡፡ የቱርክ ነፍጠኞች በከፈቱለት ሰፊ በር ያለ ምንም ፊት ለፊት ውጊያ ሰተት ብሎ የገባው የኦሮሞ ተስፋፊ፣ ነፍጥና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃሎች አምርሮ ጠላቸው፡፡ ሰይጣኑ፣ ጭራቁ በነፍጠኛ ተመሰለ፡፡ ራቡ፣ ጥማቱ፣ ማይምነቱ፣ አረመኔነቱ በነፍጠኞች ተሳበበ፡፡
አማሮች ግራኝን ድል ነስተው የኦሮሞን ቅምኝት ሲገቱት፣ ቅምኝቱን ለማቀላጠፍ ሲባል ብቻ የተሰረተው የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ግልጋሎቱን ስለጨረሰ ወዲያውኑ አከተመ፡፡ የገዳ የቀማኛ ዲሞክራሲ ባቀላጠፈው መስፋፋት ይበልጥ የተጠቀሙት ጉምቱ ቀማኞች አባ ጅፋር፣ አባ ምንትስ የሚባሉ አምባገነኖች ሆኑ፡፡ በቅምኝቱ እጅግም ያልተጠቀመው ተራ ኦሮሞ ባምባገነኖቹ ላይ ሲያምጽባቸው ደግሞ ባማራ ማሰበብ ያዙ፡፡

በኦሮሞ ተስፋፊወች እጅጉን የተበደለው አማራ በደሉን ስላስቆመ ብቻ በዳይ ተደረገ፡፡ አማራ ከመስፋፋት ባይገታን ኖሮ፣ አማራ ወደኋላ ባይመልሰን ኖሮ፣ አማራ እንዲህ ወይም እንዲያ ባያደርገን ኖሮ እያሉ ማላዘን ብቸኛ መጽናኛ ሆነ፡፡ ያማራ ጥላቻ ተለኮሰ፡፡ አማራን ካለጠፋነው ያጠፋናል የሚለውን የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ሐሳብ የጦቢያ ፖሊሲያቸው የማዕዘን ዲንጋይ ያደረጉት ምዕራባውያን ደግሞ ነብታሚ ሙሐመድ ሐሰንን በመሳሰሉ የኦሮሞ ‹‹ምሁሮች›› አማካኝነት በእሳቱ ላይ ቤንዚን ጨመሩበት፡፡

የሙሐመድ ሐሰን ምሁርነት ሙሉ በሙሉ የተገነባው ኦሮሞን ቤተኛ ሐበሻን መጤ በሚለው ባዱ ትርክቱ ነው፡፡ ይህን ትርክት ግን ብዙም ሐተታ ሳያስፈልግ አጥቂን በቀላሉ ለመከላከል በሚቻልባቸው በኦሮሞ ወቅያኖስ ውስጥ በሚገኙት ዝቋላንና ዝዋይን በመሳሰሉት ደሴቶች የሚኖሩት ጥንታዊ አልኦሮሞወች ከየት መጡ? በሚል አንድ ጥያቄ ብቻ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ይቻል ነበር፡፡

የነ ሙሐመድ ሐሰን ውሸት በእንጭጩ ሳይጋለጥ ቀርቶ ይህን ያህል ገዝፎ፣ ይህን ያህል ሕዝብ ለማሳሳት በመብቃቱ ዋናወቹ ተወቃሾች የጦቢያ የታሪክ ምሁራን የሚባሉት ግለሰቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ምሁራን በምእራባውያን ታሪክ በመራቀቅ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩ፣ እነ ሙሐመድ ሐሰን በሰፊው የጦቢያ የታሪክ መስክ ላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደ ልባቸው ፏለሉበት፡፡

ዋሾና ውሸቱ አይናቁም፡፡ ተጋጣሚው የቀረ ቡድን በፎርፌ ያሸንፋል፡፡ እነ ሙሐመድ ሐሰን ደግሞ የእስካሁን ግጥሚያወቻቸውን ሁሉንም ያሸነፉት በፎርፌ ነው፡፡ ካሁን በኋላ ግን ፎርፌው መቆም አለበት፡፡ መቆም ያለበት ደግሞ ጋጠወጦቹ የኦሮሞ ጎጠኞች ከፈሪነት በሚቆጥሩት፣ አህያ የበቅሎ አባት በሚባልበት ካህንኛ (politically correct) ዘይቤ ሳይሆን፣ አህያ አህያ በሚባልበት መዕምንኛ (politically incorrect) ዘይቤ ነው፡፡ ጥያቄው የህልውና ጥያቄ ስለሆነ፣ እንትን ብንል እንትና ይቀየማል የሚባልበት አይደለም፡፡ ሐቅ የሚያንቀው ጓጉሮ ይሙት፡፡

እየየም ሲደላ ስለሆነ፣ በሞት ሽረት ትግል ላይ ትህትናና ጨዋነት ቀርቶ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲም ቅንጦት ናቸው፡፡ ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲ ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ያሜሪቃ መንግሥት በሁለተኛው ያለም ጦርነት ወቅት የገዛ ራሱን ዜጎች (እንጥፍጣፊ የጃፓን ደም ስላላቸው ብቻ) ከወንጀለኛ ቆጥሮ ሕፃን፣ ሴት፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ንብረታቸውን ነጥቆ፣ የዜግነት መብታቸውን ገፍፎ ሰብጉረኖ (concentration camp) ውስጥ ማጎሩን መጥቀስ ይበቃል፡፡

ሙሐመድ ሐሰን ምኒልክን ወራሪ ሲል፣ እሱ ራሱ የተስፋፊ ልጅ እንደሆነ ሊነገረው ይገባል፡፡ በቀለ ገርባ ፊንፊኔ ኬኛ ሲል የቆጡን አወርድ ብሎ የብብቱ እንዳይጥል ሊገለጽለት ይገባል፡፡ ሌንጮ ለታ በነፍጠኛ ሊያሾፍ ሲሞክር፣ በዱለኛ ሊሾፍበት ይገባል፡፡ ጃዋር ሙሐመድ በቆንጨራ ሲያስፈራራ በነፍጥ ሊንቀጠቀጥ ይገባል፡፡

ኦነግ ደግሞ ስለ ልቦለዳዊው አኖሌ ሲያላዝን በእውነተኛው አርባጉጉ ሊወነጀል ይገባል፡፡ አንደኛው ወገን ምዕተ ዓመታት ወደ ኋላ ሂዶ ተስፋየ ገብረአብ እና በረከት ስምኦን የተባሉ አማራጠል እኩይ ቧልተኞች (evil comedians) የጻፉለትን ልቦለዳዊ ስቅጠት (fictional trajedy) ቀን ከሌት እያነበነበ፣ ለኻጩን እያዝረበረበ ሲነፋረቅ፣ ሁለተኛው ወገን ግን ባንደኛው ወገን አሁን ትናንትና የተፈጸሙትን በምስል የተደገፉ አረመኔያዊ ጭፍጨፋወች ከናካቴው መርሳቱ ይቅር የማይባል ኀጢያት ነው፡፡ ለልቦለዳዊው አኖሌ ሐውልት ከቆመ፣ ለእውነተኛው አርባጉጉ የሐውልቶች ሐውልት የማይቆምበት ምንም ምክኒያት የለም፡፡
ለማጠቃለል ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ገዳ የሚባል አፍሪቃ በቀል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰረተ ዲሞክራሲያዊነትን የተላበሰ ዲሞክራቲክ ሕዝብ ነው የሚባለው ትርክት ምንም መሠረት የሌለው የቱሪናፎች ባዶ ቱልቱላ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጅ ዲሞክራሲያዊ ሕዝብ የለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የገዳ ዲሞክራሲ ምንጭ ቀማኛነት ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ባህል ቢሆን ኖሮ ራሱ ኦነግ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ነበር፡፡ እነ አቦማ ዋቆ የመሳሰሉትን መሪወቹን የበላው የኦነግ ስግብግብ ጅብ ግን አመራሮቹን መቸም ቢሆን በገዳ ዘዴ መርጦ አያውቅም፡፡

ኦነግ እንደ ገዳ ዘመን አገሬውን እየነቀለና እየፈነቀለ በቀማኛነት ሊስፋፋና ሊንሰራፋ እስካልቻለ ድረስ ዲሞክራቲክ ሊሆን አይችልም፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓይንና ናጫ የነበሩት የኦሮሞ ጎጠኞች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰምና ሙጫ የሆኑት ደግሞ የዘመናችን ግራኝ የነበረው ወያኔ ጦቢያዊነትን ክፉኛ አዳክሞ የመስፋፋት በር ስለከፈተላቸው መስፋፋቱን የሚያቀላጥፍ የቀማኛ ዲሞክራሲ ለመመሥረት ሲሉ ብቻ ነው፡፡
የጦቢያውያን (በተለይም ደግሞ ያማሮች) ወሳኝ ትግል ደግሞ ግራኝ ሙሐመድ ላስራ ስድስተኛ ክፍለዘመን አባገዳወች የቅምኝት በር እንደከፈተ፣ ወያኔ ለኦነጎች የከፈተውን የቅምኝት በር ዐብይ አህመድ ሳይበረግደው በፊት ለመጠርቀም ነው፡፡

የሚቀጥለው ጦማር የሚያተኩረው በቅቤ አፉ እየደመረ በጩቤ ልቡ በሚቀንሰው፣ ኦነጋዊነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነ በመጣው፣ በሣር እባቡ ባብይ አህመድ ላይ ነው፡፡ እስከዚያው የጦቢያ አምላክ አብሔር ይጠብቅዋ፣ ይጠብቀን፡፡ ስላነበባችሁኝ አኮቴ (thank you)፡፡

መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic