>

ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን:-  መንግሥት ራሱ ቤተክርስቲያንን እያፈረሰ ነውና ዝም አትበል!! (መምህር ታሪኩ አበራ)

ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን:-  መንግሥት ራሱ ቤተክርስቲያንን እያፈረሰ ነውና ዝም አትበል!!
መምህር ታሪኩ አበራ
**መንግሥት በአደባባይ እየሸነገላ በጎን  ግን ከአሸባሪዎች ጋር እየተባበረ የውንብድና ተግባር እየፈጸመ ነውና አጥብቀን እንቃወም!!**
**ቅዱስ ሲኖዶስና ጠቅላይ ቤተክህነት በአስቸኳይ የመንግሥትን የውንብድና ተግባር በጠንካራ አቋም በማውገዝ ተቃወሙ!! **
———–
አሸባሪው ጃዋር መሐመድ ያሰማራቸው ቄሮዎች አሁንም ቤተክርስቲያን ላይ ዘምተዋል ።
♦️አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 9 እና 11 ልዩ ስሙ ኮዬ ፈጬ  እና  ገንደ ሽበሺ በሚባል አከባቢ  የኦሮሞ  መሬት ላይ ነው የተሰራው በማለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን አፍርሰዋል ።
♦️የጃዋር መሐመድ ስራ አስፈፃሚ ቄሮ የተባለ ፀረ ኦርቶዶክስ መንጋ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት እና ገንዘብ  በማለት በቀን 22/2/2012 ዓ.ም. ማታ 12፡30 ላይ በመንግስት ፒካፕ መኪና  ጭነው ዘርፈዋል። ሌሎቹን ንዋያ ቅድሳት  ውጪ ጥለው ሊሆዱ ሲሉ በህዝበ ክርስቲያኑ ትብብር ሊተርፍ ችሏል ።
የአዲስ አበባ ስብሰባ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከመንግሥት ጋር በመተሻሸት መልመጥመጡን አቁሙና ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን አሳፋሪና ነውረኛ ድርጊት ወጥቶ እንዲቃወም በተደራጀ መንገድ አስተባብሩ።
ቅዱስ ሲኖዶስና ጠቅላይ ቤተክህነት ይህንን መንግሥታዊ ሕገ ወጥ የውንብድና ተግባር ፊት ለፊት መቃወምና መንግሥትን ተጠያቂ ማድረግ ከምንም በላይ ተቀዳሚ ተግባር አድርጉ።የእስከ ዛሬው ዝምታን ትዕግስት ይበቃል!!!
Filed in: Amharic