>

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ጫላ ደጋጋ ተረኛው የኦነግ ሰለባ!!! (ዘመድኩን በቀለ) 

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ጫላ ደጋጋ ተረኛው የኦነግ ሰለባ!!!
ዘመድኩን በቀለ 
★ በ OMN ወይም OBN የማይዘገብ  የኦነግ የርሸና ዜና !!!
ከምርጫው በፊት እነጃዋር ኦህዴድን እያጸዱ ይመስላል። የሚረሸኑት የኦህዴድ ባለሥልጣናት በሙሉ ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው ተብሏል። 
 
 ★  በወለጋ ኦሮሞ ኦሮሞን መብላቱን ቀጥሎበታል። በሬ አርደው ደም እየተቀባቡ ሲማማሉ ቢውሉም ደም መፋሰሳቸውን ግን አላቆሙም። 
•••
ባለፈው ወር የኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገመቺስ ታደሰን በነቀምት ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ በታጠቁ ኃይሎች መረሸናቸው ይታወሳል።
•••
ባለፈው ሳምንት ደግሞ የኦሮሚያ መንገዶች ባለሥልጣን አማካሪ የሆኑት አቶ ቶሎ ገዳ (Tolaa Gadaa) ለመስክ ሥራ በወጡበት በኦነግ ሸኔ ኃይሎች ተረሽነው መሞታቸውም ይታወሳል።
•••
ዛሬ ደግሞ የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ጫላ ደጋጋ “ያልታወቁ ኃይሎች” የሚል የዳቦ ስም በተሰጠው ፍረጃ በዚያው በወለጋዋ ነቀምት በአደባባይ ተረሽነዋል።
•••
የዛሬ ዓመት ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎችንና የራሱ የጃዋር ጓደኛ የሆነ የማዕድን ባለሙያ በዚሁ በኦነግ ጦር ተረሽነው፣ አስከሬናቸው ከነመኪናቸው በእሳት መጋየቱ ይታወሳል።
•••
የኦሮሞ እስላሞች ኔትወርክ ወይም በእንግሊዝኛ አጠራሩ (OMN) ም ሆኑ ለኦሮሞ ባዳ ኔትወርክ ( OBN ) ይህን መሰሉን ዜና አይዘግብቱም። አልዘገቡትምም። ዐቢይ አህመድ ወደ ወለጋ አልሄድም እዚያ ሄጄ ብገደል የኦሮሞ አንድነት ይፈርሳል ያለው ከመሬት ተነስቶ እንዳልሆነ እሙን ነው።
•••
ኦነግ አይደለም ከዐማራው በላይ ኦሮሞዎችን እያረደ የሚገኝ ነፍሰ በላ ቡድን ነው። ኢሊሊ ሆቴል ተቀምጦ እየረፈረፋቸው ነው። ነገርየው ርሸናው የሚቀጥል ይመስላል።
•••
ይሄ ግድያ ግን እንኳንም ዐማራ ክልል ያልሆነ። የጌታ ምፅአት ይመስል እነ ኢቲቪ፣ እነ ራድዮ ፋና፣ እነ ዋልታ፣ እነ ኤልቲቪ ወዘተ ይሄኔ ሀገሪቷን በአንድ እግሯ ባቆሟት ነበር። የመንግሥት ግልበጣም ነው ተብለው በባሌ ገጠር ውስጥ የሚኖር ምስኪን ገበሬ ዘብጥያ በወረደ ነበር። የዐማራ አንቂዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ሁሉ በባትሪ ተፈልገው፣ በወረንጦ እየተለቀሙ በሽብር አንቀጽ በተከሰሱ ነበር። ምድረ አቃጣሪ ሁላም ተደርቦ አፉን በከፈተ ነበር።
•••
በራሱ በኦሮሞ የተረሸኑትን የኦሮሞ ልጆች ነፍሳቸውን ይማር። ለቤተሰባቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን።
•••
ሻሎም !    ሰላም !  
ህዳር 15/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic