>
5:13 pm - Thursday April 19, 5190

"አማራ ክልል ብዙ መንቀሳቀስ አልቻልንም!" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

“አማራ ክልል ብዙ መንቀሳቀስ አልቻልንም!”

 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ዮናስ አበራ
እስኪ መጀመሪያ ቄሮ አርሲ አካባቢ እንዳትደርሱ ብሎ ስላባረራችሁ ነገር አጫውተን።
እስኪ በቀደም ቄሮ ስለዘጋባችሁ ቢሮ ንገረን።
እስኪ ባለፈው ቃሊቲ ላይ እናንተ የጠራችሁት ስበሰባ ላይ ቄሮ ቀድሞ መጥቶ እቃችሁን ሰባብሮ ስላባረራችሁ ነገር ንገረን።
እስኪ ኤርትራ በረሃ መጋዘን ውስጥ በትነህ ስለመጣኸው የወገኖቻችን አፅም ንገረን።
አንዷለም አራጌና ናትናኤል ፈለቀ ከዚህ ከከሰረ ፖለቲከኛ ጋር ምን ሲያደርጉ እንደገጠሙ ግርም ይለኛል።
ኮሽ ባለ ቁጥር መግለጫ አናወጣም”
ብርሃኑ ነጋ
ከኢህአፓ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 45 ዓመታት ያልተሳተፈበት የፖለቲካ መስክ የለም !! አንዱም አልተሳካለትም !! ሁሌ ኪሳራ ብቻ !! ዛሬ ደግሞ ብርቱዎቹን አንዷለምን እና ናትናኤልን ይዞ ገደል ሊገባ ተንደርድሯል። ብርሃኑ አካሄዱ ሁሉ አብይ ስር ተለጥፎ ስልጣን ለመጋራት እያደባ ያለ ይመስላል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቃል ተገብቶለታል የሚሉ ሰዎችም አሉ። አያገኛትም !!
አብይ አህመድ “በሚወዱት ነገር ምጣባቸው፥ ከዚያ ገደል ወስደህ ጣላቸውና “አያ በሬ ሆይ ገደሉን ሳታይ” ብለህ ተርትባቸው” ብሎ ስልጣንና መንበር የተሰኘው መፅሐፉ ላይ የፃፈውን ብርሃኑ ነጋ ላይ ተገበረው !
“ባላደራ ምናምን የሚባለው ነገር እኔ ብዙ አይመቸኝም”
ብርሃኑ ነጋ
አንተ የሚመቹህንማ አብረሃቸው ተቀምጠህ አሳየኸን አኮ። ከዳውድ ኢብሳ ጋር ተቀምጠህ አየንህ እኮ። ህገወጡን ከንቲባ “ታከለ ኡማን አትተቹት ፥ አሻጋሪያችን” ነው አልክ እኮ !
አብይ 5 መፅሐፎች ፅፎ ያሳተመ ምሁር ነው”
ብርሃኑ ነጋ
“እኔ እራሴ የአብይ አህመድ ያህል ኢትዮጵያዊ አይደለሁም”
ብርሃኑ ነጋ
በየሄደበት እስክንድርና ኤርሚያስ ለገሰ ላይ ሴራ ሲጎነጉን ይውላል።  ኢሳትን በአምሳሉ አሽመደመደው። በእሱ ትዛዝ ሲሳይ አጌና ፥ መሳይ መኮንን እና ጓደኞቻቸው ነፃነታቸውን ሽጠው አብይን ሲያወድሱ ውለው እንዲያድሩ አደረገ። የኢሳት ተመልካች ቁጥር (viewers rate) ባስደንጋጭ ሁኔታ አሽቆልቁሏል ።
በቀደም የዋልታ የቲቪ ጋዜጠኛ ከሆነው ከስሜነህ ባይፈርስ ጋር ውይይት ሲያደርግ አይቼ ሰውዬው ፖለቲካ እንዳለቀበት በደምብ ያስታውቃል።
ብርሃኑ ነጋ ሆይ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ!! በቃህ !! ከእንግዲህ በኋላ ላንተ ብሎ ጎዳና ላይ የሚወጣልህ የደሃ ልጅ የለም !
Filed in: Amharic