>
6:33 am - Wednesday December 7, 2022

አማራን የሰደቡ እየመሰላቸው ራሳቸውን እየሰደቡ መሆኑን የማያውቁት ግብዞቹ ኦነጋውያን ሰዳቢዎቻችን!  (አቻምየለህ ታምሩ)

አማራን የሰደቡ እየመሰላቸው ራሳቸውን እየሰደቡ መሆኑን የማያውቁት ግብዞቹ ኦነጋውያን ሰዳቢዎቻችን!

አቻምየለህ ታምሩ
በፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ ዘመን በአማራ ላይ የተጫነውን ብአዴን የሚባል የሕወሓት  ነውረኛ ድርጅት ስንተች ይሰድቡንና ከብአዴን ሆዳም ካድሬዎች በላይ ብአዴንን ይከላከሉት የነበሩት የፋሽስት ወያኔ ቀንደኛ ተከፋይ ካድሬዎች ነበሩ። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ከተተካ በኋላ ደግሞ ተለውጫለሁ ብሎ ኦዴፓን ለመምሰል ስሙን የቀየረውን ነውረኛውን ብአዴንንና የተሸከማቸውን ጉዶች ስንተች በቀዳሚነት የሚሰድቡን  ባለጊዜዎቹ የኦሮሞ ብሔርተኞችና ኦነጋውያን ሆነዋል።
የፋሽስት ወያኔም ሆነ የኦዴፓ/ኦነግ ሰዳቢዎቻችን የኮልኮሌዎችን ማኅበር ብአዴንን እየተከላከሉ የአማራ ልጆችን የሚሰድቡት  ነውረኛውን ብአዴንና በውስጡ የተሸከማቸው እንደ ንጉሡ ጥላሁን፣ ዳግማዊት ሞገስና ብናልፍ አንዷለም  አይነት ጉዶች የሚሰጧቸውን ጥቅም እያሰሉ ነው። እንደ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ አይነት በአማራ ቁስል ላይ እንጨት የማይሰዱ ሰዎች ሲፈጠሩ ግን ለማውገዝና ለመስደብ እነዚህን ተሰዳቢዎቻች የሚቀድም የለም። በጃዋር ቴሌቭዥን ሳይቀር እየወጡ «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተደረገ ቃለ ምልልስ» ፣ «ጋዲሳ ራባዶሪ» ወዘተ እየተባለ ጥላሸት ለመቀባትና ለማውገዝ የማይደረግ ክፋት የለም።
ባጭሩ በኦዴፓ/ኦነግ ካድሬዎች የሚብጠለጠል የብአዴን ሰው ካለ ያ ሰው ለአማራ የሚቆረቆር ስለመሆኑ አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፤ ሁለትም የሰዎቹ ጥላቻ የተለመደው የኦሮሞ ብሔርተኞች የጥንብ አንሳ ፖለቲካ ማሳያ ነው። ከዚህ በፊት እንዳልነው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ የጥንብ አንሳ ፖለቲካ ነው። ጥንብ አንሳ የሚባለው አሞራ ከሌሎች የወፍ ዝርያዎች የሚለየው እድሜ ዘላለሙን የሚኖረው ሌሎች ጠልተው የጣሉትን እየሰበሰበ በመብላቱ ነው። እንደ ጥንብ አንሳው ሁሉ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካም አማራ ይጠላዋል ብለው የሚያስቡትን መውደድ ነው። ዳግማዊ ምኒልክን አምርረው የሚጠሏቸው የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ በቀለ ገርባና ሕዝቅኤል ገቢሳ የእስር ቤቱን ቋንቋ ኦሮሞኛ አደረገው፤ ዶክተር መረራ «ወያኔ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ሒትለር በአይሁዶች ላይ ከፈጸመው ጭካኔ የማይተናነስ ጭካኔ [በኦሮሞ ልጆች ላይ] ፈጽሟል» ሲሉ የገለጹትን የጭካኔ ክብረ ወሰን የሰበረውን የፋሽስት ወያኔን ግብዣ ተቀብለው መቀሌ ሽር ብትን ሲሉ የሰነበቱት የወያኔ ጭካኔ ጠፍቷቸው ሳይሆን አማራ የሚጠላውን ወያኔን መውደድ ፖለቲካቸው ስለሆነ ነው።
ግብዞቹ ኦነጋውያንና ደቂቆቻቸው በአማራ ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ሲጽፉና ሲናገሩ የማየው አንድ ስድብ አላቸው። ይህም «ቆማጣ» የሚል ስድባቸው ነው። ኦነጋውያኑና ደቂቆቻቸው ግብዞች ስለሆኑ አማራን «ቆማጣ» እያሉ በባለጌ አፋቸው ሲሳደቡ ራሳቸውን ስለማያውቁ ራሳቸውን አዙረው የሰደቡ አይመስላቸውም። ቁምጥናን በሚመለከት እስቲ ዶሴው ይውጣና እውነቱ ምን እንደሚመስል ይታይ።
የስጋ ደዌ ሆስፒታል የሚገነባው የሕመሙ ተጠቂዎች በብዛት በሚገኙበት አካባቢዎች ነው። ይህንን ቅቡል አድርገን ታሪክ ስንመረምር በኢትዮጵያ ታሪክ ከአንድ እስከ አራት ድረስ የተገነቡትን የስጋ ደዌ ሕክምና መስጫ ሆስፒታሎችንና ሆስፒታሎችን መገኛ ስንመረምር በሙሉ በሙሉ ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና ኦሮሞ በብዛት በሰፈረባቸው አካባቢዎች ውስጥ ሆኖ እናገኘዋለን።
የመጀመሪያው የስጋ ደዌ ሆንፒታል የተገነባው ሐረር ውስጥ ነው። የሐረሩ የስጋ ደዌ ሆስፒታል እ.ኤ.አ. በ1901 በፈረንሳይ ሚሽን የተቋቋመው የቅዱስ አንቶንዮስ የስጋ ደዌ ሆስፒታል [Léproserie Saint-Antoine] ነው። የዚህ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስጋ ደዌ ሆስፒታል የመጀመሪያው ሜዲካል ዳይሬክተር የነበረው ፈረንሳዩ ሐኪም Dr. Jean Féron በጻፈው ማስታወሻ የስጋ ደዌ ሆስፒታሉ ታካሚዎች የኦሮሞ ሕጻናትና አዛውንቶች መሆናቸው ገልጾ እዚህ ላትመው የማልችለውን የሕሙማን ፎቶ ግራፍ ጭምር አትሞ የሆስፒታሉን ታካሚዎች የሕመም ሁኔታ አቅርቧል። ይህ የሐረሩ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስጋ ደዌ ሆስፒታ የተቋቋመው በዳግማዊ ምኒልክ ነው። ግብዞቹ ኦነጋውያን ግን ኦሮሞ የስጋ ደዌ ተጠቂዎች እንዲታከሙ በመንደራቸው ሆስፒታል ያቋቋሙላቸውን ዐፄ ምኒልክን «ቆማጣ» እያሉ ይሰድቧቸዋል፤እነ ቀመር የሱፍ ሳይቀር እየተሳደቡ ዘፈን አውጥተዋል።
ሁለተኛው የስጋ ደዌ ሆስፒታል በ1934 ዓ.ም. ከሆለታ ወደ አዲስ አበባ ተዛውሮ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የልዕልት ዘነበ ወርቅ ሆስፒታል ወይንም ALERT(All Africa Leprosy Education and Rehabilitation Training Centre) ነው። ሆስፒታሉ ዛሬ ወደሚገኝበት በሰበታ/ጅማ በር ወይም አየር ጤናና ቶታል መካከል ከመዛወሩ በፊት ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ሆለታ አካባቢ አንድ የስጋ ድዌ ተጠቂዎች ማገገሚያ ማዕከል ነበር።
በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመው ሶስተኛው የስጋ ደዌ የሕግምና ማዕከል ሻሸመኔ ውስጥ ኩዬራ በሚባለው ቦታ እ.ኤ.አ. በ1954 ዓ.ም. የተቋቋመው ማዕከል ነው። በተመሳሳይ ዓመት አንድ ሺ፣ አንዲ ሺ ሰው የሚያክሙ አዲስ ሕይዎትና አዲስ ተስፋ ሕይዎት የሚባሉ ማዕከላት ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ተቋቁመዋል። Ethiopian National Association of Exleprosy Patients የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2001 ዓ.ም. ባሳተመው ጥናት መሰረት የሻሸመኔው ማዕከል ስራ ሲጀምር 3000 የስጋ ደዌ ሕሙማን በማከም መሆኑን ነግሮናል።
በኢትዮጵያ ታሪክ አራተኛው የስጋ ደዌ ማዕከል እ.ኤ.አ. በ1959 ዓ.ም. በግንደ በረት የተቋቋማው የሕክምና መስጫ ማዕከል ነው። በተመሳሳይ ዓመት አርሲ ውስጥ ጋምቦ በሚባል ቦታ፤ ሐረርጌ ውስጥ ደግሞ ቢሲዲሞ በሚባል ስፍራ ተጨማሪ የስጋ ደዌ የሕክምና መስጫ ማዕከላት ተቋቁመዋል።
በመሰረቱ አንድ በሽታ አንድን ነገድ ወይም አንድን ቋንቋ ተናጋሪ ለይቶ አያጠቃም፤ የአንድ ነገድና ቋንቋ ተናጋሪ በሽታም የለም። ሆኖም ግን 1951 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የስጋ ደዌ ሆስፒታልና የሕክምና መስጫ ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ተገነቡት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና ኦሮሞ በብዛት በሰፈባቸው አካባቢዎ ውስጥ ነው። በሌላ አነጋገር የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የስጋ ደዌ ሕክምና ሆስፒታል ሐረር ውስጥ ከተቋቋመበት ከ1893 ዓ.ም. እስከ 1951 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ ምድር የተገነቡት አራቱም የስጋ ደዌ ሕክምና መስጫ ማዕከላትና ሆስፒታሎች ሙሉ በሙሉ የሚገኙት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና ኦሮሞ በብዛት በሰፈረባቸው አካባቢዎች ነው። እስከ 1951 ዓ.ም. ድረስ አማራ ክልል በሚባለውና አማራ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ ግን አንድም የስጋ ደዌ ሕክምና መስጫ ማዕከል አልነበረም። ይህን የማያውቁ ግብዞቹ ኦነጋውያን ግን አማራውን የሰደብን መስሏቸው «ቆማጣ» እያሉ ራሳቸውን ሲሳደቡ ይውላሉ።
Filed in: Amharic