>

እነ በረከት ሰምዖን  በአማራ መሀል የተከሉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል መፍረስ አለበት!  (አቻምየለህ ታምሩ)

እነ በረከት ሰምዖን  በአማራ መሀል የተከሉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል መፍረስ አለበት! 

አቻምየለህ ታምሩ
እነ በረከት ሰምዖን ብአዴን የሚባል የግዑዛን ስብስብ በእንደራሴነት ፈጥረው በሰሜኑ አማራ [የአማራ ክልል ላለማለት ነው] መካከል የጭቆና ሰንሰለት ሲዘረጉ የተከሉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን የሚያደርግ የቢሮክራሲና የቁጥጥር ስርዓትን መፍጠር ነበር። እነ በረከት ብአዴንን  እንደራሴ አድርገው አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን የሚያደርግ  የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል  የፈጠሩት አማራው ከተማመነና  አንድ ልብ ከሆነ ምን እንደሚፈጠር ስለሚውቁ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  የምናየውና  ከምናስበው በላይ እየገማን ያለው የጎጥ በሽታ  እዚህ ደረጃ  የደረሰው  እነ በረከት  ቢወገዱም  እነሱ አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን አድርገው የተከሉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል ሳይፈርስ በመቅረቱ ነው። ወደፊትም ቢሆን የእንደራሴው ብአዴን የአገዛዝና የቢሮክራሲ ባሕል ሳይፈርስ [በሌላ አነጋገር  ብአዴን ሳይወገድና  አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን ተደርጎ  የተዘረጋው  የቢሮክራሲ መዋቅሩና የአገዛዝ ባሕሉ ሳይፈርስ] ከምናስበው በላይ የገማው የጎጥ በሽታ እየገለማ መሄዱ አይቀሬ ነው።
በእውነቱ የአማራ ውርደት፣ ግፍና በደል ወደ አማራነት ካላመጣን ምንም ነገር ሊያመጣን አይችልም። የአማራ በደል የሚሰማው ሁሉ እነ በረከት  አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን ለማድረግ በዘረጉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል ውስጥ ተጠልፎ ሊወድቅ አይገባም። የአማራ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ  አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን አስበው እነ በረከት የፈጠሩትን የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል  ከጭንቅላቱ ውስጥ በመጀመር  ብአዴን የሚባል በቁማቸው የሞቱ አጋሰሶች ማኅበር የቆመበትን  የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ  አንድ ባንድ  እየገዘገዘ ያፍርስ።
አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን ለማድረግ  እነበረከት በአማራው መሀል የዘረጉት  የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል ሳይፈርስ የሚተማመን፣ አንድ ልብ የሆነና የአማራው በደል የሚሰማው የአማራ ኅብረት መፍጠር አይቻልም።
Filed in: Amharic