>

እልፍ አጀንዳ ሰጥቶ፤ በሺህ መረጃ አወናብዶ  ለመሰወር የተደረገው ርብርብ አልተሳካም። (ሀብታሙ አያሌው)

ከሞጣ ባሻገር !!

ሀብታሙ አያሌው
እልፍ አጀንዳ ሰጥቶ፤ በሺህ መረጃ አወናብዶ  ለመሰወር የተደረገው ርብርብ አልተሳካም።  እውነትን ይዘህ ትግልህን ቀጥል…!!   ከዚህ ተማር …
                            * * *
በሞጣ መስጊዶች  መቃጠል እራሱ የአማራ ህዝብ ተጎጂ ሆኖ ሳለ ለኦነግ ፖለቲካ ወገባቸውን ያከራዩ ጥቂት የፖለቲካ ቁማርተኞች የአሊሞቹን አገር፣ የሼሆቹን አገር  የኡላማዎቹን አገር ሙስሊም ጠል እያሉ ከበሮ ሲደቁ ሰነበቱ።  የአማራን ህዝብ ማጀት የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ከጅማ ከባሌ ጦራቸውን ሰብቀው ተነሱ።  በሁለት ቀናት 85 ዜጎች ያሳረደውን፣ 31 አብያተክርስቲያናት በእሳት እንዲጋዩ ያደረገውን፤ የቡራዩን ጭፍጨፋ የመራውን ቄሮነኝ የሚል መንጋ እየነዳ የሰው ልጅ ዘቅቅቆ ያሰቀለውን ጃዋርን በየመድረኩ እያነገሱ በሞጣ ታክከው አማራ ህዝብ ላይ የጦርነት አብዮት ለመለኮስ እንቅልፍ አጥተው ባዘኑ።  ግን አልተሳካም ያም በትግል ከሸፈ። የአማራ ህዝብ እስላም ክርስቲያኑ የተጋመደ ታሪክ ይዞ እልፍ አመታት የዘለቀ ነውና ሴራውን አምክኖ መስጊዱን ሊገነባ ችቦ ሆኖ ተነሳ።
     ከዚህ ተማር …
ይህም ነገ ይጋለጣል።  እስልምናን ለኦነግ ፖለቲካ መታገያ አድርጎ በአደባባይ “ፊንፌኔ ኬኛ” እያለ፤  “የኩሽ ምድር አብዮት መሪ ነኝ ብሎ በይፋ እያወጀ፤  ናዝሬት መስጊድ ሲቃጠል፣  ሙስሊም በቆርቆሮ ሲታረድ፣፣  አብያተ ክርስቲያናት ሲጋዩ፣ ካህናት በመሰዊያው ስር ደማቸው እንደ ጎርፍ ሲወርድ፣ በቡራዩ ጋሞዎች እና ወላይታዎች ተመርጠው ሲጨፈጨፉ፣  ከአንድ ሚሊዮን በላይ ጌዴዎዎች ተፈናቅለው ሲበተኑ ትንፍሽ ያላሉት  የአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ለማወጅ፣ ሙስሊም ጠል ለማለት የቀደማቸው የለም።  እመነኝ የዚህ ክፉ አላማ ጥንስስም ሚስጥሩ ተጋልጦ የዓለም መነጋገሪያ መሆኑ አይቀርም።
      ከዚህ ተማር…
በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለት የምስራቅ ጎጃም የአማኑኤል አካባቢ ተወላጆች ታላቅና ታናሽ ወንድማማቾች በደቡብ ሚዛን ቴፒ ታርደዋል።  በመንግስት አራጁ (ያልታወቀ ቡድን) ተባለ።
ኦሮሞ የሆኑ ክርስቲያኖች ተለይተው እየተገደሉ ንብረታቸውም እየወደመ ነው።  ይህም ከሞት ባመለጡ አራስ እናቶች በይፋ እየተነገረ ነው።  የመንግስት ምላሽ (ያልታወቀ ቡድን) 
የአማራ ልጆች ተማሪዎች ተለይተው ታገቱ የመንግስት ምላሽ ( ያልታወቀ ቡድን) 
ጃዋር መሐመድ እና መረራ ጉዲና በይፋ ደብረ ሊባኖስ ገዳምን ውረሱ፣  ኦሮሞ ያልሆነ አባርሩ ሲሉ በአደባባይ መመሪያ ሰጡ። በዚያው መድረክ  ጃዋርን የማትቀበል ኦርቶዶክስ አታስፈልግም ተብሎ በይፋ ታወጀ።  (መንግስት ዝምታን መረጠ)
        ከዚህም ተማር …
ካሚል ሸምሱ እና አህመዲን ጀበል እንዲህ ካለው አደገኛ ቡድን መሪ ከጃዋር ጋር ምን አጣበቃቸው ??  ትላንት በመከራቸው ከጎናቸው ያልተለየ ህዝበ ክርስቲያን ምን በድሎ ጠላታቸው ሆነ ?  31 ቤተክርስቲያን እንዲጋይ መደረጉ እንዴት አልሰማቸው አለ ?  “ጃዋርን የማትቀበል ኦርቶዶክስ ትውደም” ሲባል ይህ ነውር ነው ማለት ለምን ከበዳቸው ??  እንጠይቃለን
Filed in: Amharic