
የፈለገ በየወንዙ ሲማማሉ ቢከርሙም

ብጥብጡ እንደሁ አይቀሬ ነው!!!
ዘመድኩን በቀለ
• ከሳሽና ተከሳሽ ጉዞ ጀምረዋል !
•••
እኔ በበኩሌ (ኦፒዲኦ ፣ ኦዴፓ ፣ ፒፒ) ሰገጤ ይመስለኛል እንጂ 27 ዓመት ከተማ ስለኖረ እስከዚህ ድረስ ብዙም ዥልጥም፣ ዥልም አይመስለኝም። (ኦፒዲኦ ኦዴፓ ፒፒ) እኛ ሁላችን እንደምናስበውም ለዳውድ ኢብሳው ኦነግና ለጃዋር መረራ ገርባው ኦፌኮ ማርማላታ፣ ሹካሬ የሆነች የሥልጣን ዙፋኑን እንዲሁ እንደዋዛ በብላሽ በከንቱም ይለቅላቸዋል ተብሎም ባይታሰብ መልካም ነው።
•••

•••
ኦነግ፣ ኦፒዲኦ ኦዴፓ ፒፒ እና ኦፌኮ በገዛ ሜዳቸው ላይ እርስ በእርሳቸው በኃይለኛው ይጣለዛሉ። ሁሉ በእጁ፣ ሁሉ በደጁ የሆነው የኦፒዲኦ ካድሬም ለራሱ ህልውና ሲል፣ በኦፌኮና በኦነግ የተራቡ ጅቦችም ላለመበላት ሲል እስከደም ጠብታ ድረስ ይፋለጣታል። በኦሮሚያ የዝሆኖቹ የእርስ በእርስ እርግጫ ግን ለሳሮቹ ይተርፋል ተብሎም ይጠበቃል። ታዲያ አዳሜና ሔዋኔ መጠንቀቅ ይህን ጊዜ ነው።
•••
ወዳጄ ሌባ ሲሰርቅ እኮ አይጣላም። ደም የሚፋሰሰው የሰረውቀውን፣ የዘረፈውን ለመከፋፈል ሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ ብቻ ነው። ኦፒዲኦ ኦዴፓ ፒፒ ደግሞ ህወሓት ስትበላ ኩራዝ ያዥ የነበረ ደንገጡር ነበር። ሥልጣኑን በያዘ በሁለት ዓመቱማ ገና ምኑንም ሳያይ ለሌላ ጅብ አሳልፎ የሚሰጥ አይመስለኝም። ገና መች ዓለሙን ቀጨና። ገና መች መርከብ አውሮጵላን ሰረቀና። አሄሄ ሞተዋታላ።
••• እኔን የሚያሳዝኑኝ ቀውሲ በላይና ሆዶ ኃይለ ሚካኤል ብቻ ናቸው። ያ ገመቹ አዱኛ አንተ ታውቅላቸዋለህ እንግዲህ !!
ሻሎም ! ሰላም !
ጥር 23/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።