>

የመሬት ወረራን በመከላከል ስም ሁለት ወጣቶች በመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ! (ብርሀኑ ተክለ አረጋይ)

የመሬት ወረራን በመከላከል ስም ሁለት ወጣቶች በመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ!

ብርሀኑ ተክለ አረጋይ 
* በቤት ለቤት አፈሳም ብዙ ምእመናን ተግዘዋል! ይህ ሁሉ ቤተክርስቲያን ላይ፤ ግን ለምን????
-ድሆች ቆጥበው የሰሩትን ኮንዶሚኒየም ወሮ የያዘ ዱርዬን ማስለቀቅ አቅቶት ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ መግለጫ የሚሰጠው መንግስት
-“የመሬት ወረራ በአዲስ አበባ ላይ ተጧጡፏል እርምጃ ልወስድ ነው” ካለ በኋላ “ትቼዋለሁ ውረሩት” ያለው መንግስት
-ሀይሌ ጋርመንት የተሰራውን የሌላ እምነት ተቋም ለማፍረስ ሲሄድ ቄሮ እንዳትነካ ሲለው ጭራውን ሸጉጦ የተመለሰው መንግስት

ዛሬ ግን …

-እንደ ጠላት በሌሊት ሸምቆ ገብቶ በኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ላይ ፊት ለፊት እየተኮሰ ነው ።
-እስካሁንም 2 ወንድሞች ሰማእት ሆነዋል። በቤት ለቤት አፈሳም ብዙ ምእመናን ተግዘዋል
– የአለቆችን ፈቃድ ከመፈፀም የዘለለ ስለጉዳዩ እውቀት የሌላቸው ወታደሮች ቅዱስ ታቦቱን መውሰድ አለብን የሚል ድፍረት ላይ ናቸው።

የተያዘው ኦርቶዶክሳውያንን ማጥቃትና ቤተክርስቲያንን ማዋረድ ነው። ከመሬት ወረራ ጋር አታመሳስሉት።

ይኸው ነው!!!
Filed in: Amharic