>
5:13 pm - Saturday April 18, 9778

የምስጋና መልዕክት (ኤርሚያስ አመልጋ)

የምስጋና መልዕክት

(ኤርሚያስ አመልጋ)
ባልፈጸምኩት ወንጀል ወህኒ ከወረድኩበት ዕለት አንስቶ እየተመላለሳችሁ የጠየቃችሁኝ፣ ለአንድ አመትከሁለት ሳምንታት ያህል ያለመሰልቸት በመገናኛ ብዙሃንና በማህበራዊ ድረገጾች ስለእኔ ድምጻችሁን ከፍአድርጋችሁ ያሰማችሁ፣ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ፍትህ እንዳገኝ ስትወተውቱ የነበራችሁ የማውቃችሁምሆነ የማላውቃችሁ ወዳጆቼ ሆይ፣ እነሆ ከልብ የሆነ ምስጋናዬን ተቀበሉኝ!….
ተፈጥሮዬ ሆኖ በብዙዎች ዘንድ ስሜትን የሚረብሽ፣ ምቾት የሚነሳ ወይም መጥፎ ተደርጎ የሚታይ ነገርሲያጋጥመኝ፣ ነገርዬውን ስለቀጣዩ የተሻለ ለውጥ በጥሞና የማሰቢያና የማብሰልሰያ መልካም አጋጣሚለመለወጥ ነው የምተጋው፡፡ በእስር ላይ በቆየሁባቸው 14 ወራት የእስር ቆይታዬ በንዴት እና በቁዘማአልያም ራሴን ደካማና ተሸናፊ አድርጌ እያየሁ በመብሰልሰል ያሳለፍኩት አንድም ቀን የለም!
በእስርበቆየሁባቸው ጊዚያት ሁሉ፣ ከውስጤ አውጥቼ ዙሪያዬን የምረጨው በጎ ሃይልና ቀና ስሜትን ነበር፤በዚህም በቂሊንጦ ግቢ ውስጥ ቀና መንፈስና የንቃት ስሜት ከፍ እንዲል ማድረግ ችያለሁ። ከታራሚዎችአንስቶ እስከ ጥበቃ እና የአስተዳደር ሰራተኞች፣ በዙሪያዬ የነበሩት ሁሉ ያለአግባብ እንደታሰርኩ የተረዱእና የእኔ ቀና አመለካከትና የንቃት ስሜት የተጋባባቸው ነበሩ፡፡
ታላላቅ ስራዎቼን አቋርጬ በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ብታጎርም፣ አእምሮዬ አንድም ቀን ስራ ፈትቶአያውቅም ነበር፡፡ በእያንዳንዷ ቀን 8 ሰዓታትን ያህል በንባብ ነበር የማሳልፈው፡፡
በእስር ቤት ቆይታዬበየሳምንቱ የታተሙትን ሁሉንም የ“ዘ ኢኮኖሚስት” መጽሔት ቅጾች እና ያነበብኳቸውን ከ30 በላይመጽሐፍት ጨምሮ፣ በሳምንት ቢያንስ 200 ገጾች ያህል አነብብ ነበር፡፡ በየዕለቱ ለአንድ ሰዓት ያህልስፖርት እሰራ ነበር፡፡
የማላውቃቸውን ሰዎች ጨምሮ ሊጠይቁኝ የሚመጡ ስፍር ቁጥር የሌላቸውጎብኝዎችን ማስተናገድም ሌላኛው የዕለት ከዕለት ህይወቴ አካል ነበር፤ በየዕለቱ ከ3 ሰዓታት በላይከጠያቂዎች ጋር አሳልፍ ነበር፡፡
በተረፈ ግን፣ ለምን ታሰርኩ ብዬ በመብሰልሰል አልያም መቼ ይሆን የምፈታው እያልኩ በመጨነቅያጠፋሁት ግዜ አልነበረም፡፡ በመታሰሬ ምክንያት ስለተሰናከሉብኝ ስራዎቼም ሆነ ከንቱ ስለቀሩብኝ ግዙፍ የቢዝነስ ፕሮጀክቶቼ በማሰብና በመጨነቅ ያባከንኩት ግዜ አልነበረም፡፡
እያንዳንዱን ቀን በጸጋ እናበመልካም ስሜት እየተቀበልኩ፣ የራሱን መልካም ነገር እንዲፈጥር በማድረግና በበጎ ተሞክሮነትበመውሰድ ነበር የምሸኘው፡፡ መረጋጋቴን የሚነጥቀኝም ሆነ ፍጹም የሆነ ሰላሜን የሚነሳኝ ምክንያትናሃይል ስላልነበረ፣ እንቅልፍ ሲወስደኝ እንኳን እንደ ህጻን ልጅ ነበር – ለ8 ወይም 9 ያህል ሰዓታት፡፡
ያለፈውን አመት ዘወር ብዬ ስመለከተው፣ ብዙ ነገር በውስጤ ይመላለሳል፡፡ በመታሰሬ ደስተኛ ነበርኩ
ለማለት ባልደፍርም፣ መጥፎውን አጋጣሚ ወደ መልካም ዕድልነት በመቀየር ለንባብ፣ ለማሰላሰልና ለላቀእድገት ፈር በመተለም ልጠቀምበት በመቻሌን ደስ ይለኛል፡፡ የእስር ቤት ቆይታዬን ለጥሞናና እናለማሰላሰል ስለተጠቀምኩበት፣ የህይወት ዓላማና ግቤ ከመቼውም በላይ ከፍ ሊል ችሏል፡፡
 ባልታሰር ኖሮ በተለመደው የዕለት ከዕለት የኑሮና የቢዝነስ ግርግር ተጠምጄ አሳልፈው ነበር… በጥልቀት የማሰብናሁሉንም ነገር በጥሞና አሰላስዬ፣ አዲስ ግንዛቤና የተሻለ አቋም ለመያዝ አልችልም ነበር፡፡
ለተራዘመ ጊዜ በእስር መቆየቴ ሁሉንም ነገር ከጫጫታው ተነጥዬ በጽሞና ለማሰላሰል፣ የበርካታኢትዮጵያውያንን አሳዛኝ ዕጣ ፋንታ፣ አገሬ የምትገኝበትን አደገኛ ሁኔታና አስፈሪ አካሄድ በጥልቀትለመገምገም የምችልበትን መልካም ዕድል ፈጥሮልኛል፡፡
ቂሊንጦ በነበርኩባቸው ጊዚያት ሁሉንምበእርጋታ ካሰላሰልኩ በኋላም፣ እንደ አንድ ዜጋ አገሬን ከገባችበት ችግር ለማውጣት የራሴን አስተዋጽኦማበርከት እንዳለብኝ ጽኑ እምነት ይዣለሁ፡፡
የአገሪቱ ኢኮኖሚ ተንኮታኩቶ ለመውደቅ በተቃረበበት
በዚህ አደገኛ ወቅት ላይ፣ በተለመደው መልኩ መጓዝ አዋጭ እንዳልሆነ ተገልጾልኛል፡፡ ቀጣይ ጉዞዬምይህን እውነታ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት ወስኛለሁ፡፡
በእስር ላይ በነበርኩበት ጊዜ “ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ” የሚል ርዕስ ያለው እና አገሪቱንከተጋረጠባት የውድቀት አደጋ በምን መልኩ ማዳን እንደሚቻል ምክረ ሃሳቦችን ያቀረብኩበትን መጽሐፍጽፌ ያጠናቀቅኩ ሲሆን፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ታትሞ በገበያ ላይ ይውላል፡፡
በጅምር የቀሩ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶቼን ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ፣ በቀጣይ በማህበራዊ ድረገጾች
አማካይነት በተለይ ለወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እውቀት ለማካፈል፣ ህይወትን ለማሻሻል የሚያስችልአቅጣጫ ለማመላከትና ድጋፍ ለማድረግ አቅጃለሁ፡፡
ብታውቁኝም ባታውቁኝም፣ በችሎት አዳራሽ እየተገኛችሁ አጋርነታችሁን ስታሳዩኝ፣ በማህበራዊ ድረገጾችስለእኔ ፍትህ ስትጮሁ፣ ስለእኔ በትጋት ስትጽፉና ስትዘግቡ የኖራችሁ እንዲሁም ቂሊንጦ ድረስእየመጣችሁ ስትጎበኙኝ የማውቃችሁም የማላውቃችሁም በሙሉ…
እነሆ ከ14 ወራት በኋላ በደልና ጥቃትቅስሙን ሰብሮት ተስፋ የቆረጠ ሳይሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ ልብ፣ ከምንጊዜውም የተሻለ ጽኑመንፈስ የተላበሰ ኤርሚያስ ሆኜ መጣሁላችሁ!
ከወራት በፊት “የማይሰበረው” የተሰኘው የህይወት ታሪኬን የያዘ መጽሐፍ በተመረቀበት ዕለት እስር ቤትሆኜ የላክሁት ደብዳቤ፣ እስር ቤት ያለው ኤርሚያስ በደል እየቆጠረ የማይቆዝም፣ ጥቃትን ፈርቶየማይረበሽ ልብ የታደለ፤ በተመታ ቁጥር የሚጠነክር፣ በተገፋ ቁጥር የሚጸና፣በታጠፈ ቁጥር የሚቀና፣የማይበገር መንፈስ የተሰጠኝ ሰው እንደነበር ይመሰክራል፡፡
አሁንም ከቂሊንጦ ቅጽር ግቢ የበለጠ ጠንክሮ የወጣ፣ ከመቼውም በላቀ ተስሎ አዲስ ታሪክ ለመስራትየሚያኮበኩብ የበለጠ ጠንካራና ደስተኛ ኤርሚያስ ነው ከእስር ተፈትቶ ወደ እናንተ የመጣው!…
ውድ ወዳጆቼ…
በቅርቡ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ብቅ ብዬ ስለሁሉም ነገር በስፋት የምለው ይኖረኛል፡፡ እስካሁን ከጎኔየነበራችሁ ሁሉ፣ አደጋ ላይ በወደቀው ኢኮኖሚ ሳቢያ ፈተና ውስጥ የገቡ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ህይወት ለማሻሻል በማደርገው ቀጣይ እንቅስቃሴ ውስጥም ከጎኔ
እንደምትቆሙ ተስፋ አለኝ፡፡
በስተመጨረሻም…
በእስር ባሳለፍኩት ጊዜ ሁሉ የተፋጠነ ፍትህ አገኝ ዘንድ ስለእኔ ድምጻችሁን ከፍአድርጋችሁ ላሰማችሁና አጋርነታችሁን ላሳያችሁኝ በሙሉ፣ በድጋሜ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬንለማቅረብ እወዳለሁ!!!
ኤርሚያስ አመልጋ
መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
Filed in: Amharic