>

ዜና ርሸና ትግራይ ...!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

ዜና ርሸና ትግራይ …!!!

 ዘመድኩን በቀለ

• ግድያው የተፈጸመው ቅዳሜ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም ናዕዴር አዴት ወረዳ ውስጥ ልዩ ቦታው ጅራ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን፤ ምክንያቱም በወጣው አዋጅ መሰረት ፖሊስ በመጠጥ ቤት ነበሩ ሰዎች እንዲበተኑ በማድረግ ላይ በነበረበት ጊዜ በተፈጠረ አለመግባባት እነደሆነ ተገልጿል።

ሟች ሃጎስ ንጉሥ የሚባል ወጣት እንደሆነና በአንድ የፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ወዲያው ህይወቱ ማለፉን የወረዳው ጽህፈት ቤት ሕዝብና የመንግሥት ግንኙነት ገልጿል።

•••
ድሮ ድሮ በመላው ኢትዮጵያ ዜጎችን አግአዚ በተባለው ቅልቧ ዜጎችን በየአደባባዩ አናታቸው በስናይፐር እየበጠረቀች ታጋድም ትረፈርፍ የነበረችው እሜቴ ህወሓት በፋኖ ነፍጥና በቄሮ ፍልጥ ከመሃል ሃገር ተባራ ጠቅልላ በስሙ ስትነግድበት ወደ ነበረው የትግራይ ህዝብ ጉያ መሸጎጧ ይታወቃል።
•••
እናም ይህቺ ደም ጠጪ የኢትዮጵያ ነቀርሳ እንደድሮው ለሰይጣኗ የምትገብረው ደም ብታጣ እዚያው በተወሸቀችበት በትግራይ ክልል ፖሊስ በወረዳ በናዕዴር ዓዴት ነባራይ ጣብያ ጅራ ዝሆነ መንእሰይ ሓጎስ ንገስ ገ/ሄር ብቐሊል ውጥጥ ምኽንያት ገይሩ ተኲሱ ከም ዝቐተሎ ተገሊፁ ኣሎ ተብሏል።
•••
በመላ ትግራይ ጅምላ መግደሉን እስክትጀምር አጅሪት ህወሓት ወጣት ሓጎስ የተባለውን ምስኪን ወጣት በመግደል በችርቻሮ መግደል መጀመሯ ነው የተነገረው። በኮሮና ምክንያት ከቤት አትውጡ የሚል ዐዋጅ ያወጀችው አጅሪት ህወሓት እሷ መቀለ አክሱም ሆቴል ተቀምጣ በውስኪ እየታጠበች ውኃ የሌለውን ወጣት ውኃ ፍለጋ ወጣህ ብላ መግደሏ ምን ዓይነት ጨካኝ እንደሆነች ያሳያል የሚሉ አሉ።
•••
ህወሓት በቀጣይ በኮሮና ሰበብ የዓረና፣ የብልጽግናና የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን በሙሉ ረራ በተራ እንደልማዷ፣ ፀረ የሚል ታርጋ እየለጠፈች፣ ደብዛ ማጥፋት፣ መረሸን፣ ማሳደድና ማሰር እንደምትቀጥል ስነግራችሁ ከኢዩ ጩፋና ከእስራኤል ዳንሳ በበለጠ መገለጥ ተሞልቼ ነው። ቱ ምን አለ በሉኝ።
•••
ከጥቂት ቀናት በኋላ የትግራይም የኢትዮጵያም ህዝብ ይርበዋል፣ ይጠማዋልም። ከዚያ የራበው ህዝብ ደግሞ መሪዎቹን ይበላል። አሁንም ወሬህን ትተህ ለሃኪሞች ቁሳቁስ አሟላ። በጀቱን ሁሉ አጥፈህ የህክምና ቁሳቁስ አስገባ። ተናግረናል።
•••
አደይ የትግራይ እናት፣ የሟቹ የለግላጋው የሀጎስ እናት አይዞሽ። ወገብሽን ታጠቂ በገመድ። የአክሱሟ ጽዮን የመቀሌውን ደብረ ጽዮንና ፓርቲውን በጊዜ ብን አድርጋ ድራሽ አባቱን ካላጠፋችልሽ ልክ እንደ ወለጋዋ እናት የተገደለ ልጅሽ አስከሬን ላይ ተቀምጠሽ እንድታለቅሺ ያደርጉሻል። እነዚያ መላዋን ኢትዮጵያን ሲገድሉ የከረሙት ነፍሰገዳዮች ከነሙያቸው፣ ከነመሳሪያቸው፣ ከነ ልምዳቸው ትግራይ ከገቡ ከራርመውልሻል። እግዚአብሔር ይሁንሽ አደይ መዓረይ።
•••
ንሓውና መንግስተ ሰማያት የዋርሶ። ስድርኡን መሓዝቱን ድማ ፅንዓት ይሃብኩም። አሜን።
•••
 ~ የተረሻኙን ወጣት ሓጎስን ነፍስ ይማር ሳትሉ እንዳታልፉ ጓደኞቼ።
ሻሎም  !   ሰላም  !
መጋቢት 22/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic