>

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የ3 ቀን ሱባኤ እንዲይዙ ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች!!! (አደባባይ ሚዲያ) 

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የ3 ቀን ሱባኤ እንዲይዙ ቤተ ክርስቲያን አሳሰበች!!!
 
      አደባባይ ሚዲያ 
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሦስት ቀን ሱባኤ እንዲያዝ መንግሥትን ጠየቀች
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገራችን የተከሠተው በሳይንስ መድኃኒት ያልተገኘለት ኮቪዲ-19 ኮሮና ቫይረስ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን ቃል ኪዳን ከአገራችን እንዲወገድ የነነዌ ሰዎች ከንጉሡ ጀምሮ ከዙፋን ወርደው፣ ሕፃናት ጡት ከመጥባት፣ እንቦሶች ከእናታቸው ከመገናኘት ተከልክለው ለሦስት ቀን በመጸለያቸው የሚያቃጥል እሳት ከሰማይ ከወረደ በኋላ ከኃጢአት መመለሳቸውን ዓይቶ እንደተመለሰ በአገራችን የተከሠተው ወረርሽኝ እንዲወገድ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጀምሮ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሩን ዘግቶ የሦስት ቀን ሱባኤ እንዲይዝ መንግሥትን ጠየቀች።
ዘገባው  የማኅበረ ቅዱሳን መገናኛ ብዙሃን ነው
Filed in: Amharic